Skip to main content
x

ናይጄሪያዊው ሰባት ዓመት ፅኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት

እንዳይመረትና እንዳይዘዋወር ክልከላ የተጣለበትን አደንዛዥ ዕፅ (ኮኬይን) ይዞ ለማለፍ ሲሞክር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ የተመሠረተበት ናይጄሪያዊ፣ በሰባት ዓመታት ፅኑ እስራትና በ15,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጠ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት፣ ቅጣት የጣለበት ናይጄሪያዊ ሚስተር አማቺ ስቲቭ ነው፡፡