Skip to main content
x

በወልዋሎ አዲግራት ክለብና መሪው ላይ የተጣለው ቅጣት ሲፀና የአራት ተጫዋቾች ቅጣት ተነሳ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ፣ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ላይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ተጥሎ የነበረው ቅጣት ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡ የክለቡ የቡድን መሪ ቅጣት ሲፀና፣ በአንድ ተጫዋች ላይ ተጨማሪ ቅጣትን አስተላልፏል፡፡ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመካላከያ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ የተቋረጠው ጨዋታ ይጠቀሳል፡፡

የፌዴሬሽኑ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝርዝር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተሰየመው የፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴ ግንቦት 26 ቀን በአፋር ሰመራ ለሚደረገው ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚቀርቡ ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ግንቦት 14 ቀን ይፋ ባደረገው ዝርዝር መሠረት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአዲስ አበባ፣ የትግራይና የጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የወከሏቸው ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ፣ አቶ ተስፋዬ ካህሳይና ኢንጂነር ቶል ቤል በተደረገው ማጣራት መሠረት ከዕጩነት ዝርዝር ውጪ ተደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ የአገሮች ደረጃ በነበረበት ቆሟል

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በየወሩ የሚያወጣው የኮካኮላ የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎች) ከነበረበት አንድ ደረጃ ቀንሶ 146ኛ ሆኗል፡፡ የውጤትም ሆነ የአሰልጣኝ ቆሌ የራቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ከመደበኛው አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቻ ሳይሆን፣ ነጥብ ሊያስገኝ ከሚችል የወዳጅነት ጨዋታ ከራቀ ወራትን አስቆጥሯል፡፡ ቡድኑ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከሌላቸው ጥቂት የዓለም አገሮችም አንዱ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የምርጫ ጨረታ

በካምቦሎጆ ዙሪያ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የደራና የጦፈ የድለላ ሽሚያ የሚስተዋልበትን ክስተት ከመጋረጃ ጀርባ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ ምርጫ ባልተከናወነበት በዚህ ወቅት፣ ጉዳዩ ለጨረታ የቀረበ እስኪመስል የተቋሙ የዋና ጸሐፊነት ቦታና ሌሎችም በንዑስ ኮሚቴ የሚመሩ ልዩ ልዩ ክፍሎች በእነማን እንደሚመሩ ከወዲሁ ለእነማን እንደሚሆን መቃወቅ የጀመረ ይመስላል፡፡

ክልሎች የዕጩዎቻቸውን ሰብዕናና ብቃት እንዲያጤኑ ተጠየቀ

ገላጋይ ሕግ አጥቶ ለወራት ሲያወዛግብ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ለመጨረሻ ጊዜ በተባለለት ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ ይደረጋል፡፡ ክልሎች ለምርጫው ዕጩ የሚያቀርቡበት ቀነ ገደብ ከነገ በስቲያ ዓርብ ግንቦት 10 ቀን ያበቃል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አከናውኖ፣ ምርጫውን በሚመለከት ተፈጥሮ የቆየውን ብዥታ እንዲጠራ በማድረግ፣ አዲስ የአስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ አይዘነጋም፡፡

ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት ኢዩቤልዩ ክብረ በዓሉን በሩጫ አጠናቀቀ  

በቅርቡ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድኑን በይፋ ያፈረሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የተመሠረተበትን 75ኛ ኢዮቤልዩ በዓሉን በሩጫ ውድድር አክብሯል፡፡ ተቋሙ ለአሸናፊ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 75 ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡ እሑድ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. መነሻና መድረሻው አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ባደረገውና በግንባታ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዘመናዊ ሕንፃ ዙሪያ በተደረገው የሩጫ ውድድር 13ሺሕ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፉ መድረክ ያበቋት ወጣት ቦክሰኞች

በሞሮኮ ካዛብላንካ ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ቦክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅና በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ በውጤት ተመልሳለች፡፡ በመጪው ዓመትም በዓለም አቀፉ መድረክ በወጣቶቿ ትወከላለች፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያዎች ከመድረክ ጫጫታ ያለፈ መፍትሔ ይሻሉ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታዎች የሚዘወተሩባቸው ቦታዎችም ሆነ ከውድድር ሜዳዎች ውጪ የሚፈጸሙ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶች ላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ስብሰባዎች እስኪያሰለቹ ድረስ ተካሂደዋል፡፡ እየተካሄዱም ናቸው፡፡ መግለጫዎች ተሰጥተዋል፡፡ ማስጠንቀቂያዎችና የቅጣት ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ችግሮቹ ግን እየባሰባቸው መጥተዋል፡፡

ከብዙ ንትርክ በኋላ ውድድሩ እንዲቀጥል የተወሰነበት የፌዴሬሽኑና የእግር ኳስ ዳኞች ፍጥጫ

የውዝግቡ መነሻ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም በመከላከያና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለቦች መካከል የተካሄደው 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ነው፡፡ ዋናው ዳኛ በወልዋሎ ክለብ ቡድን መሪና ተጫዋቾች መደብደባቸው ተከትሎ የእግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች እስከ ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ምንም ዓይነት ጨዋታ እንደማይዳኙ አስታውቀው ነበር፡፡

ፌዴሬሽኑና የዳኞቹ ማኅበር በስብሰባ ቀነ ቀጠሮ አልተስማሙም

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ እየጠና የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት መደፍረስ ተከትሎ ዳኛዎቹ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት የአቋም መግለጫ በማውጣት ከብሔራዊ ፌደሬሽኑ ጋር ሊያከናውኑት የነበረውን የስብሰባ ቀነ ቀጠሮ ላይ መስማማት አልቻሉም፡፡ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. መከላከያ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ባደረጉት 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ በመሀል ዳኛው ኢያሱ ፈንቴ ላይ የደረሰውን ደብደባ ተከትሎ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የጠራው የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማኅበር ሊስተካከሉ ይገባል ያላቸውን ስምንት የአቋም ነጥቦች አስቀምጧል፡፡