Skip to main content
x

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት ውድመት ሪፖርት እየተጠናቀቀ ነው

በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ምክንያት የደረሰውን ውድመት የሚያጣራው ቡድን ሪፖርት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከሁለቱም ክልሎች ከ900 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ መጠኑ የማይታወቅ ንብረት ወድሟል፡፡

ኢንቨስተሮችን የሚያስደነግጡ ድርጊቶች በፍጥነት ይቁሙ!

ከሰሞኑ በዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅና በሁለት ሠራተኞች ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ለሦስት ዓመታት ያህል ከዘለቀው የፖለቲካ ቀውስ በማገገም አንፃራዊ መረጋጋት በተፈጠረላት በዚህ ወቅት ግድያው መጸፈሙ፣ አሁንም ለሥጋት የሚጋብዙ መፍትሔ ያልተገኘላቸው ችግሮች እንዳሉ ያመላክታል፡፡

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

በጋምቤላ ክልል በማዣንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ለ79 ሰዎች ሞት፣ ለ27 ሰዎች ከፍተኛና ዝቅተኛ የአካል መጉደል፣ ለ273 መኖሪያ ቤቶች መቃጠል፣ ከ13,000 በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ላይ የተጠናቀረውን ሪፖርት ለማቅረብ የፓርላማው ጥሪ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ባጋጠመው የዜጎች መፈናቀል ወቅት የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ያጠናከረውን ሪፖርት ይፋ ለማድረግ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪን እየጠበቀ እንደሆነ ዋና ኮሚሽነሩ አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር)  አስታወቁ፡፡

በሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ደረሰ

ከወራት በኋላ እንደገና ባገረሸው የሞያሌ የሰላም መደፍረስ መጠነ ሰፊ የሆነ ግጭት ተከስቶ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡ ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር በተመሳሳይ በዚሁ የድንበር ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት፣ ዘጠኝ ንፁኃን ተገድለው ሌሎችም መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡

በካፋ ዞን ጎጀብ በተነሳ ተቃውሞ ንብረት መውደሙ ተሰማ

በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ አካባቢ ሐሙስ ሚያዚያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተቀሰቀሰ ግጭት፣ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ በርካታ ንብረት መውደሙን የሪፖርተር ምንጮች አስታወቁ፡፡ የግጭቱ መነሻ የሆነው ጉዳይ በጎጀብ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች፣ የጎጀብ እርሻ ልማት ይዞታ ተከፋፍሎ ይሰጠን በማለት ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሳይገኝ በመቆየቱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ቆይታ ገደብ የተወሳበት የሐዋሳው ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተሰየሙ በኋላ፣ እጅግ በጣም የተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳ ይዘው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በአዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተጓዙ ሲያወያዩና ንግግሮችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳምንት ክራሞት

ከተመረጡ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣናቸውን በተረከቡ በቀናት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሥራ ጉብኝት በማድረግ፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ለበጎ የታሰበው ክፋት እንዳያበላሸው!

በመላ አገሪቷ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ተሞልተው የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እያከናወኑ መሆናቸው፣ አገሩን ለሚወድ ማንኛውም ሰው ዕፎይታ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለጋራ ዓላማ አብረው ለመሠለፍ የሚያስችላቸው ጅማሬ እየታየ በመሆኑ፣ ብዙዎች መጪውን ጊዜ በብሩህ ተስፋ ተሞልተው ቢጠብቁ አይገርምም፡፡