Skip to main content
x

የ “መብቴ ነው!” የመጀመርያ ምዕራፍ

‹‹አንዲት አገር ጋዜጣ አልባ መንግሥት ይኑራት ወይስ ጋዜጦች ኖረው መንግሥት አልባ ትሁን የሚለውን ጉዳይ የመወሰን ምርጫው ለእኔ የተተወ ቢሆን፣ ሁለተኛውን ስመርጥ ለቅጽበት እንኳ ባላመነታሁ ነበር፡፡›› ከአሜሪካን መሥራች አባቶችና ፕሬዚዳንቶች አንዱ የነበሩት ቶማስ ጀፈርሰን፡፡

ማሳሰቢያ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር

በቅድሚያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ የተሰማኝን ጥልቅ ደስታ ልገልጽልዎት እወዳለሁ፡፡ መልካም የሥራ ዘመን፡፡ ለሁሉም የአገራችን ሕዝቦች የዕድገት፣ እንዲሁም የመልካም ለውጥ ዘመን እንዲሆን ያለኝን ምኞቴን በተጨማሪ እገልጸላሁ፡፡

ነፃ መውጣት የሚያሻቸው የፍትሕ አካላት!

በቁጥር ለበዙ የአገሬ ወጣቶች የተስፋ ብርሃንን የፈነጠቁት ጎልማሳ መሪ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በመሆን ሲሰየሙ፣ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ያደረጉትን ንግግር የሚረሳ ኢትዮጵያዊ ወጣት ያለ አይመስለኝም፡፡ ጠቅላያችን ከሌሎች አገራዊ ጉዳዮች እኩል የአገሪቱ ባለብዙ ቁጥር አካል ሆኖ ሳለ ተረስቶ የቆየውን የኅብረተሰብ ክፍል በተመለከተ ቃል ገብተው ነበር፡፡

ለውጡና   የአገራችን  የመገናኛ ብዙኃን  ንፍቀ ክበብ            

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የኢሕአዴግን የተካረረ የብሔር አጀንዳ ወደ አገራዊ አንድነት፣ አገራዊ ችግሩንም ከመልካም አስተዳዳር ዕጦት ነው ከሚለው እሳቤ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት መጓደልና የሕግ የበላይነት መዳከም አስፍቶ የመመልከት ዝንባሌ መታየት ጀምሯል፡፡

ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ መነሻ ካፒታል ብቻውን መፍትሔ አይደለም

የማንኛውም የንግድ ሥራ የመጨረሻ ግብ ሀብት ማካበት  እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ ለዚህም ሲባል አዋጭ በሆነ የንግድ ሥራ መሠማራትና  በየጊዜው ትርፋማ  መሆን፣ አንዳንዴም በረጅም  ጊዜ  የበለጠ ትርፋማ ለመሆን የአጭር ጊዜ ኪሳራን መቀበል ሊገጥም እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ይኼንን አሠራር ተረድቶ በዕቅድ በመመራትና ሥራን በአግባቡ በማከናወን ያሰቡት ቦታ መድረስ ይቻላል፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በብሩህ ተስፋ ውስጥ

ከመጋቢት ሦስተኛው ሳምንት 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር አዲስ የፖለቲካ አየር በመንፈስ ላይ ነው፡፡ ይህ መልካም እስትንፋስን የሚያስተናግድ ንፍቀ ክበብ የተፈጠረው ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች እንደሆነ ዕሙን ነው፡፡ በአንድ በኩል ለወራት ያህል የዘለቀው ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ አመፅና ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ያደገ የሰላም መደፍረስ፣ በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተግበሩ ጋብ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ መንግሥትንም ለተሻለ ለውጥ እያነሳሳው ነው፡፡

ዕድገት በሒደት የሚገለጽ የሥራ ውጤት ነው

‹ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?›› በሚል ርዕስ ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በአንድ ጋዜጣ አራት ባለሙያዎች ለመነሻነት ጥሩ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ የዓለም ባንክ የአገራችን ምጣኔ ሀብት በ8.3 መቶ ማደጉን ገልጿል፡፡ ይህንንም ዕድገት ከጎረቤት አገር ከኬንያ ጋር ያነፃፅራል፡፡

 በታዋቂ ግለሰቦች ማንነት መነገድ

ሰዎች ያዩትንና የተገነዘቡትን በተፈጥሮ ባገኙት የተፈጥሮ ዕውቀት፣ ወይም በትምህርት በቀሰሙት ጠቅላላ ዕውቀት፣ ወይም በልዩ ሥልጠና በተማሩት ሙያዊ ዕውቀት አስድግፈው ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ በሦስቱ ዕውቀቶች አማካይነት የሚነገሩ ነገሮች ልዩነት ያለመርቀቅ ጥሬነትና የመርቀቅ ብስለት ደረጃ ብቻ ነው፡፡

ታሪካዊ አጋጣሚውና ሰዋዊ ስሜቶቻችን

ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ማግሥት ጀምሮ ስለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ብዙ ተብሏል፡፡ በተለይም እንደ አሜሪካዊው ዶናልድ ሌቪን የመሳሰሉ የጥናትና የጽሑፍ አትኩሮታቸውን በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያደረጉ ‹‹የመከኑት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዕድሎች›› የሚሉ ሐተታዎችን ብዙ አንብበናል፡፡

የምግብ ዋስትናችን ለከተማም ለገጠርም እኩል ትኩረት መስጠት አለበት

ኢትዮጵያ በምግብ እህል ራሷን መቻሏን ለአገሯና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካወጀች ሦስት ዓመታት አልፈዋል። 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሲከበር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባሰሙት ንግግር፣ ‹‹ዛሬ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ሕዝባችን ባደረገው እንቅስቃሴ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም.