Skip to main content
x

ጤፍን ወደ ሜካናይዝድ እርሻ የሚያሸጋግሩ ማሽኖች አገር ውስጥ ገቡ

ማሽኖቹን አገር ውስጥ ለማምረት ታስቧል በኢትዮጵያ ከ50 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በቋሚነት የሚመገበውን ጤፍ ከኋላቀር አስተራረስ አላቀው ወደ ዘመናዊ ግብርና ያሸጋግራሉ የተባሉ ማሽኖች አገር ውስጥ ገቡ፡፡ እነዚህን ማሽኖች አገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማድረግ የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

በአማራ ክልል የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ቱለፋ ከተማ የተቋቋመው የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡ በቻይና ባለሀብቶች የተቋቋመውና ሒዩማን ዌል ፋርማሲዩቲካል በተሰኘው ድርጅት አማካይነት በአማራ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው ‹‹ሒዩማን ዌል›› የተሰኘውና የመጀመርያ የሆነው የመድኃኒት ፋብሪካ፣ እሑድ ኅዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይኼነው ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ አይኖርም

ኢትዮጵያ ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከአዋሽ-ወልዲያ-መቀሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ እያካሄደች ቢሆንም፣ ዘንድሮ አዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደማይጀመር ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አገሪቱ ሁለት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ቢሆንም ዘንድሮ የሚጀመር ፕሮጀክት የለም፡፡ ከመቼ ጀምሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደሚጀመር አይታወቅም ብለዋል፡፡

በተቃውሞ ጉዳት የደረሰበት የቻይናው ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታው መጀመሩ ተነገረ

የአካባቢው ነዋሪዎች አዲስ አበባ በመምጣት ይቅርታ ጠይቀዋል በሰሜን ሸዋ ዞን አረርቲ ከተማ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በቻይናው ሲሲሲሲ አማካይነት ሲገነባ የነበረውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በደረሰበት መጠነኛ ጉዳት ግንባታው ተቋርጦ ቢቆይም ከሰሞኑ ሥራው መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመር 106 ኮንቴይነሮችን በማጓጓዝ የሙከራ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ

የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ የሚገኘው አዲሱ የአዲስ አበባ ጂቡቲ ምድር ባቡር መስመር 106 ኮንቴይነሮችን በአንድ ጊዜ ከጂቡቲ ወደብ በመጫን የሙከራ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ፡፡

የቻይና ልዑካን ቡድን ከፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊዎች ጋር በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ተነጋገረ

የቻይና የመንግሥት ምክር ቤት የአማካሪዎች ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን፣ ከፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊዎች ጋር በፖሊሲ ጥናት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አደረገ፡፡ የሁለቱ አገሮች የፖሊሲ አማካሪዎች ከፍተኛ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል አዳራሽ ውይይት ሲያደርጉ፣ የቻይና የመንግሥት ምክር ቤት የአማካሪዎች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሚስተር ዛሆ ቢንግ የቻይናን ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡

ግዙፎቹ የቻይና ፊልም ስቱዲዮዎች

 የቻይናዋ መዲና ቤጂንግ ምሽት ላይ ከሚደምቁ ከተሞች አንዷ ነች፡፡ በየጎዳናው በሥራ የተጠመዱ ፍራፍሬ ሻጮች ገበያተኞችን ያስተናግዳሉ፡፡ በቅርብ ርቀት የቻይናን ባህላዊ ምግቦች የሚሸጡ ሰዎች በሠልፍ የሚጠብቋቸውን ተመጋቢዎች ፍላጎት ለማርካት ተፍ ተፍ ይላሉ፡፡

ቱሪዝምን ብቸኛ መተዳደሪያዋ ካደረገች ሊጂያንግ ከተማ መማር 

በቻይና ከሚገኙ ግዛቶችና ከተሞች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ጎሳዎች በሚኖሩበት የዩናን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ሊጂያግ ከተማ አብዛኛው ገጽታዋ ከኢትዮጵያ ሁኔታ ተቀራራቢነት አለው፡፡ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ፣ የአየር ንብረት ሁኔታዋ በአብዛኛው ደጋና ወይናደጋዊ በመሆኑ አብዛኛው ጊዜ ዝናብ አያጣትም፡፡

በኦሞ ኩራዝ 5 ፕሮጀክት ላይ 12.1 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ኃላፊዎችና ደላሎች ተከሰሱ

በብድር ከተገኘ 10.1 ቢሊዮን ብር ላይ 15.9 ሚሊዮን ብር ኮሚሽን መከፈሉ ተገልጿል የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክትን በጨረታ አወዳድሮ መስጠት ሲገባቸው፣ በሕገወጥ መንገድ በደላሎች አማካይነት ለቀረበው ጃንዚ ጃንግሊያን ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ በ12,119,913,986 ብር በመስጠት፣ በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል