Skip to main content
x

የአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ለግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ፈተና ሆነዋል

ከጥቂት ዓመት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየተገነቡ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሕንፃዎቹ ራሱን ችሎ ፈቃድ የሚሰጥበትም ሆነ የሚቆጣጠርበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰ ተመለከተ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ 26 ሺሕ ሕንፃዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን፣ በዚህ ዓመት በማዕከል ደረጃ ለ500 ፕሮጀክቶች የግንባታ ፈቃድ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር ውይይት ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር፣ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያቋረጠውን ውይይት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የከተማውን ደረቅ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ የገነባው የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ምክንያት ሥራ በጀመረ በሰባት ወሩ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ይታወሳል፡፡

የወረገኑ ተፈናቃዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ሕገወጥ የመሬት ወረራ አካሂደዋል” በማለት ያፈናቀላቸው የወረገኑ አባወራዎች ጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መፍትሔ እንዲሰጧቸው  አቤቱታ አቀረቡ፡፡ የወረገኑ ተፈናቃዮች ያቋቋሙት ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ማክሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በላከው ደብዳቤ፣ በአጠቃላይ የተፈናቀሉት ከ25 ሺሕ በላይ ናቸው ብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ግዙፍ የመዋቅር ለውጥ ለማካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታ ይጠበቃል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በፖለቲከኞችና በባለሙያዎች የሚሠራውን ሥራ ለመለየት፣ ካቢኔውንም በአንድ ከንቲባና በአምስት ምክትል ከንቲባዎች ብቻ ለማዋቀር የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ታወቀ፡፡

በግንባታ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች የዋጋ ንረት ሳቢያ ይጠናቀቃሉ የተባሉት የ40/60 ቤቶች ችግር ገጥሟቸዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም እየተገነቡ የሚገኙ 17‚737 ቤቶች በሚቀጥለው ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቁ ቢገልጹም፣ ዋጋቸው እየናረ ለሚገኘው የግንባታ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች ዋጋ በጀት ባለመኖሩ ዕቅዱ የሚሠራ አለመሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡ ከንቲባ ድሪባ ከሳምንት በፊት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት የ2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በ40/60 ፕሮግራም ከሚገነቡት 38‚240 ቤቶች ውስጥ 17‚737 ቤቶች በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቁ ገልጸው ነበር፡፡

የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ተቋቋመ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አቋቋመ፡፡ በከተማው ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው ይህ ኤጀንሲ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም የፈጠራ ባለሙያዎች የተካተቱበት አማካሪ ምክር ቤት ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲው ተጠሪነቱ በቀጥታ ለከተማው ከንቲባ ሲሆን፣ ኤጀንሲውን እንዲመሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ኃይለ ሥላሴ ፍሰሐ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡

አዲሱ የመሬት ኮርፖሬሽን ለልማት ተፈናቃዮች ይጠቅማል የተባለ ዕቅድ አዘጋጀ

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በመሀል አዲስ አበባ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን እንዲያለማ ሥልጣን የተሰጠው ‹‹የአዲስ አበባ ማዕከላትና ኮሪደሮች ኮርፖሬሽን››፣ ከነበሩበት ቦታ የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደነበሩበት ተመልሰው የሚቋቋሙበትን መንገድ እንደሚከታተል ተመለከተ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደገለጹት፣ የመልሶ ማልማት ሥራ የሚካሄድበት የአካባቢ ነዋሪዎችን አፈናቅሎ ሳይሆን አካቶ መሆን ይኖርበታል፡፡