Skip to main content
x

ጉሬዛ

ጉሬዛ ዛፍ ላይ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ በግንባሩ፣ በጉንጮቹና በአገጩ ላይ ነጭ ፀጉር አለው፡፡ በጅራቱ ጫፍና በጎኑ ነጭ አለው፡፡ በተረፈ ፀጉሩ ጥቁር ነው፡፡ ዋነኛ ምግቡ ቅጠላ ቅጠሎችና፣ በተጨማሪም ፍራፍሬዎች ነው፡፡ ጉሬዛዎች ብዙውን ጊዜ የሚበሉት ቅጠል ሲሆን፣ አንዳንዴ ያልበሰሉ ፍሬዎችና እንቡጦች ሲያገኙም ይበላሉ፡፡

የእንቁራሪት አምሳያ ዝርያ

ሳላማንደር ይባላሉ፡፡ ረዥምና ሸንቃጣ አካል ሲኖራቸው አካላቸው ላይ ምንም ቅርፍ አይገኝም፡፡ እግርና ጅራትም አላቸው፡፡ እግራቸውም እንደ እንሽላሊት ዓይነትና በደንብ ያልዳበረ ነው፡፡ በአመጋገባቸው ሥጋ በል ናቸው፡፡ ርባታቸው እንደ ሴሲሊያን ውስጣዊ ፅንሰት በማካሄድ ነው፡፡ የዕጭ ዕድገት ደረጃቸው በውኃ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

ጥቁር ግስላ

ያ ጥቁር ግስላ ደም ሸቶታል›› ዕውቁ ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ ከአራት አሠርታት በፊት ያቀነቀነው ነበር፡፡ በዘይቤያዊ አገላለጹ ጀግናውን ከጥቁር ግስላ ጋር ያቆራኘበት ነው፡፡

ዐዞ እና መንጋጋው

ዐዞ የባሕር አውሬ ሆደ መጋዝ ጋድሚያ እንቅልፋም፤ ያገኘውን ሰውና እንስሳ በዥራቱ እየጠለፈ ወደ ባሕር ይዞ የሚገባ ብሎ የሚፈታው የአለቃ ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ነው፡፡ ልጇን ዐዞ የበላባት እናት ‹‹ግባተ መሬቱን አትድገሙ እናንተ፤ ታዞ ሂዷል እንጂ ልጄ መቼ ሞተ›› ስትል እህት ደግሞ ‹‹ላንድ ቀን ትእዛዝ ሰዉ ይመረራል፤ የኔ ወንድም ታዞ ዓባይ ላይ ይኖራል፤›› ብላ አንጎራጉራለች፡፡

የአፍሪካ ጎሽ

የአፍሪካ ጎሽ እስከ ሦስት ሜትር ርዝማኔና 1.7 ሜትር ከፍታ ያለው ሣር ተመጋቢ ግዙፍ አጥቢ እንስሳ ነው፡፡ በአፍሪካ ሣራማ ሥፍራዎች የሚገኘው ይህ ግዙፍ እንስሳ እስከ 900 ኪሎ ግራም ክብደት አለው፡፡

አውራሪስ

አውራሪስ ከታላላቆቹ አጥቢ እንስሳት መሀል ይመደባል፡፡ በብዛት በአፍሪካና በእስያ ታወቂ የሆነው ይህ እንስሳ በዓለም ላይ አምስት ዝርያዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ ከእነዚህ አምስት ዝርያዎች ሦስቱ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡

‹‹አርዘ ሊባኖስ››

አርዝን መዝገበ ቃላት ሐዲስ ዘኪወክ ታላቅ ዛፍ ወፍራም ደንዳና ረዥም ገናና እንደ ጥድና እንደ ዝግባ ያለ ሲል ይፈታዋል፡፡ እስከ 20 ሜትር የሚረዝመው ዝግባ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በደጋማ አካባቢ ይበቅላል፤ ብዙ ቅጠልና ዐጽቅ አለው፡፡ በሊባኖስ ምድር የሚበቅለው ረዥሙ ዛፍ ‹‹አርዘ ሊባኖስ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡

ሰስ

ሰስ በተራራማ አካባቢ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ ከአጥቢ እንስሳ የሚመደቡ ሲሆን፣ ምግባቸውም አበባ፣ ሰፋፊ ቀጠል፣ ፍራፍሬና እፀ ተክል ናቸው፡፡ ሰሶች ሳር አይበሉም፡፡ አንድ ሴት ሰስ ከ11 እስከ 16 ኪሎ ግራም ስትመዝን፣ ወንዶቹ ከዘጠኝ እስከ 12 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ የሁለቱም ቁመት እስከ 82 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡

ልዩዎቹ የዘንባባ ዛፎች

ከብዙ ዓመታት በፊት በውኃ እየተገፋ የመጣ አንድ በጣም ትልቅ ዘር በሞልዳይቪስ እና በኢንዶኔዢያ ደሴቶች ዳርቻ ላይ ሲያርፍ የብዙ ሰዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። የዚህን ዘር መነሻ በሚመለከት የተለያዩ አፈ ታሪኮች ይነገሩ ጀመር። አንዳንዶች በባሕር ውስጥ የሚበቅል ዛፍ ዘር እንደሆነ ስለተሰማቸው ኮኮ ደ ሜር ወይም የባሕር ኮኮናት ብለው ሰየሙት።

ድምፅ አልባ አጥፊው

ምስጦች ድምፅ አልባ አጥፊዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ ስም የተሰጣቸው ዛፎችን፣ የዛፍ ስሮችንና ተክሎችን እንዲሁም የእንጨት ውጤቶችን ከላይ ሳይሆን ከሥር ገብተው ውስጡን ቦጥቡጠው ስለሚበሉና ቅርፊት ብቻ ስለሚያስቀሩ ነው፡፡ ምስጦች ለ24 ሰዓት ሳያቋርጡ የሚመገቡ ሲሆን፣ የተመቻቸ ስፍራ ካገኙ እዚያው መጠለያቸውን ሠርተው ይሰፍራሉ፡፡