Skip to main content
x

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ ነው

ሰላሳ ስድስት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሰባ፣ በአገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደጠቆሙት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ የተጀመረ ሲሆን፣ በዋናነት አገሪቱ ባጋጠማት የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ደም አፋሳሽ ግጭቶች የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤት አለመሆናቸውን ለመተንተን ውይይት ተጀመረ

በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ‹‹የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤቶች ናቸው›› ለሚሉ አካላት ምላሽ ለመስጠት፣ መንግሥት የፖለቲካ አመራሩንና ሠራተኞችን ማወያየት ጀመረ፡፡ በፌዴራል መንግሥት ደረጃ 80 ገጾች ያሉትና በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለአወያይ አመራሮች ተበትኗል፡፡

ከ660 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ለመርዳትና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ አለች

በመስከረም ወር በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተቀሰቀሰ ግጭት ለተፈናቀሉ ከ660 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ እገዛ ለማድረግ ፍላጎቱ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መማር ማስተማር ሥራቸው የመመለስ ፈተና

ማዕረግ ሞላ (ሙሉ ስሟ ተቀይሯል) ተወልዳ ያደገችው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ካሉ ወረዳዎች አንዱ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ እናቷ ጠላ እየጠመቁና እየሸጡ በሚያገኙት ገቢ እንዳሳደጓት፣ አባቷ በሕይወት ቢኖሩም ከእናቷ ጋር ከመለያየታቸው ባሻገር ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደማያደርጉላት ታስረዳለች፡፡ የእናቷን ውለታ ለመክፈል በማሰብም ለትምህርቷ ትኩረት በመስጠቷና በማጥናቷ ጥሩ ውጤት በማምጣት ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ አግኝታለች፡፡ ዘንድሮ በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የአካውንቲንግ ተማሪ መሆኗንም ትገልጻለች፡፡

አገርን መታደግ የሚቻለው ዘመኑን በሚመጥን መፍትሔ ብቻ ነው!

በአገሪቱ በሥራ ላይ ያለውን ፌዴራላዊ ሥርዓት ያፀናው ሕገ መንግሥት 23ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. የፀደቀው ሕገ መንግሥት አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚረዱ በኩረ ሐሳቦችን የያዘ ሲሆን፣ በፊት የነበሩ የተዛቡ ግንኙነቶችን በማረም አዲሷን ፌዴራላዊት አገር ዕውን ለማድረግ ዓላማ የሰነቀ ነው፡፡

‹‹መንግሥት እንኳን የሰው ሕይወት ይቅርና የውሻ ደም መፍሰስ የለበትም ብሎ ነው እየሠራ ያለው›› ነገሪ  ሌንጮ (ዶ/ር)፣  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ስለህዳሴ ግድቡና አገሪቱ ስላለችበት የፀጥታ ሁኔታ የመግለጫቸው የትኩረት ነጥቦች ነበሩ፡፡

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡

በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ ተጋላጭነትን የሚቃኝ ቡድን ተንቀሳቀሰ

የተረጂዎች ቁጥር ከ8.5 ሚሊዮን ሊቀንስ ይችላል ከኦሮሚያና ከሶማሌ የተፈናቀሉ ዜጎች ለማቋቋም የሰላም ኮንፈረንስ ይጠበቃል እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 1 ቀን 2018 በኋላ በድርቅ ምክንያት የሚኖረው የተረጂዎች ቁጥር ለማወቅና የሚያስፈልገውን በጀት ከወዲሁ ለመመደብ፣ የመጨረሻውን ቅኝት የሚያካሂድ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሁለቱ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየክልሎቻቸው እንዲመደቡ የተደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እንጂ በክልሎች ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

በመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት መስክ ለውጦችን ያመላከተው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት በርካታ ጉድለቶች እንዳሉ ጠቆመ

በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት በሚመደብ በጀት ሲተገበሩ በቆዩት የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በየጊዜው ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በርካታ ጉድለቶች እንደሚታዩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት አመላከተ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ረገድ አፋርና ሶማሌ ክልሎችና የድሬዳዋ አስተዳደር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡