Skip to main content
x

ከዓሳ አስጋሪነት እስከ አምስት ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት

የእንቦጭ አረም ለጣና ሐይቅ ህልውና አስጊ ስለመሆኑ መወራትና መረባረብ የተጀመረው በቅርቡ ነው፡፡ አረሙ ለሐይቁ ብቻም ሳይሆን፣ ለህዳሴው ግድብም ያሠጋል የሚለው ፍራቻ እያየለ በመውጣቱ አረሙን የማጥፋት ጥረቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ ተገለጸ

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጉባዔውን ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት የአተት በሽታ በአገሪቱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰም በጉባዔው ተጠቁሟል፡፡

የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦችን ያገናኘው መድረክ ለምን አስፈለገ?

ለአምስት ቀናት የተካሄደው የኦሕዴድ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ በተጠናቀቀ ማግሥት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ባህር ዳር አቅንቶ ነበር፡፡ በዚህ የልዑካን ቡድን አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ፣ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ ሌሎች የቢሮ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ድምፃዊያን፣ ምሁራን፣ ደራሲያንና ሌሎች ግለሰቦች ወደ ባህር ዳር አቅንተው ነበር፡፡

የነፍስ ወከፍ የጤፍ መዝሪያ ማሽኖች ግዥ የሙስና ጥያቄ አስነሳ

ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች አንዳንዶቹ ከአገር ወጥተዋል ለሦስት ክልሎች የተከፋፈሉ 30 ሺሕ ያህል የነፍስ ወከፍ የጤፍ መዝሪያ ማሽኖችን በመግዛት ያከፋፈለው የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ ከማሽኖቹ ግዥና ሥርጭት ጋር የተያያዘ የሙስና ጥያቄ ተነሳበት፡፡

የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ የማሽን ግዥ ጨረታ ሊወጣ ነው

በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ የማሽን ግዥ ጨረታ ሊወጣ መሆኑ ታወቀ፡፡ የአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አየለ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የአንቦጭ አረም በዘላቂነት ለማስወገድ የማሽን ግዥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ሊወጣ ነው፡፡

የኦሕዴድ ኮንፈረንስ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማውጣት ተጠናቀቀ

በአዳማ ከተማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ኮንፈረንስ፣ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ተጠናቀቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሪፖርተር እንደተናገሩት የክልሉን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ የአሥር ዓመት የድርጅቱ ስትራቴጂ ይፋ ሆኗል፡፡

በኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ አደረጃጀት አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

የአማራና የሶማሌ ክልሎች መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ‹ልዩ ኃይል› የሚባል የፖሊስ አደረጃጀት እንደሌለው፣ ይህ ስም ለአድማ ብተና ኃይል እንደሚሰጥ የክልሉ ፖሊስ ገለጸ፡፡ የአማራና የሶማሌ ክልሎች መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ስምንት ሰዎች እንደ ሞቱ ክልሉ አስታወቀ

ሌሎች ምንጮች ቁጥሩን ከፍ አድርገዋል ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ በተነሳው ግጭት ስምንት ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ አስታወቀ፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ቴሶ የሟቾች ቁጥር ስምንት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስምንት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሞተዋል

240 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞንና በአምቦ ከተማ በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሲሞቱ፣ 37 ያህል ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቡኖ በደሌ ዞን በገቺ፣ በደሌ፣ ጮራና ዴጋ ወረዳዎች ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ግጭት መቀስቀሱ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገልጿል፡፡