Skip to main content
x

ለሕዝብ ፍላጎት መታዘዝ ያስከብራል!

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸው ከመሰማቱ በፊት  በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ፖለቲከኞች ተፈተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲደረግ በማሰብ ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸው፣ አገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ችግር ያመለክታል፡፡ ላለፉት 27 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ኢሕአዴግ ከፊቱ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ተደቅነውበታል፡፡ አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሁሉንም ወገኖች በሚያግባባ ሰው መተካትና የተሻለ ምኅዳር መፍጠር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እንደካሁን ቀደሙ በነበረው ሁኔታ የሚያስቀጥል አምጥቶ ቀውሱን ማባባስ ነው፡፡

የሰው ሕይወት ሳይጠፋ መፍትሔ ይፈለግ!

የሰው ሕይወት በከንቱ እየጠፋ አሁንም ችግር በችግር ላይ እየተደራረበ የአገር ህልውናን እየተፈታተነ ነው፡፡ ሰሞኑን በሐረር ከተማ ሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያህል በተቀሰቀሱ የተለያዩ ግጭቶች በርካቶች ሞተዋል፡፡ በፌዴራል ደረጃም ሆነ በክልል የደረሱ አደጋዎችን መፍትሔ ፈልጎ ማስቆም ሲገባ፣ በፖለቲካ አመራር ውድቀት ምክንያት ከፍተኛ ጥፋት ደርሷል፡፡ በተለያዩ ግጭቶች ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ንፁኃን ዜጎች ደም ሳይደርቅ ሌላ እየተጨመረ ሕዝብ እየተሳቀቀ ነው፡፡

ለብሔራዊ መግባባትና አንድነት የሚረዱ ዕርምጃዎች ይፋጠኑ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረው እስረኞችን የመፍታትና ክስ የማቋረጥ ዕርምጃ ሰሞኑን ቀጥሎ፣ 746 እስረኞችና ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ እንደተወሰነ ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ሲል በፌዴራል 115፣ በደቡብ ክልል 413፣ በኦሮሚያ ክልል 2,345፣ እንዲሁም በአማራ ክልል 2,905 ታሳሪዎች መፈታታቸው አይዘነጋም፡፡  በተገባው ቃል መሠረት የእስረኞች መፈታት እንደ አንድ ትልቅ ዕርምጃ ሊቆጠር ይገባል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈርዶባቸው የታሰሩና ክስ የተመሠረተባቸው ዜጎች ከእስር መለቀቃቸው ለአገር ዕፎይታ ነው፡፡ ጅምሩ ተጠናክሮ በመቀጠል ሌሎች ታሳሪዎችና ተከሳሾችም ይለቀቁ ዘንድ መንግሥት በብርቱ ሊያስብበት ይገባል፡፡

ለውጥን መሸሽ አያዋጣም!

በማያቋርጥ የለውጥ ሒደት ውስጥ በሚገኝ ዓለም መንቀርፈፍ መገኘት ካለበት ጥቅም ጋር ያቆራርጣል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለውጥ በፍጥነት ስለሚከናወን ከበረከቱ መቋደስ የሚቻለው ራስን ከፍጥነቱ ጋር ማስተካከል ሲቻል ብቻ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ በረከቶች በየቀኑ በአራቱም የዓለም ማዕዘናት በብርሃን ፍጥነት ከአንዱ ወደ ሌላው መሸጋገር የቻሉት፣ በማያቋርጠው የለውጥ ሒደት ውስጥ በማለፍ ነው፡፡ በሥልጣኔ እየገፋ ያለው የሰው ልጅም ዘመናትን ተሻግሮ እዚህ የደረሰው፣ ዓለምን እንድትመቸው አድርጎ መለወጥ በመቻሉ ነው፡፡

መደማመጥ ጠፍቶ መተራመስ አያዋጣም!

‹‹የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል››፣ ‹‹ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል››፣ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም፣ ‹‹ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ››፣ ‹‹ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው››፣ ‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል››፣ ወዘተ. ዕድሜ ጠገብ ምሳሌያዊ አባባሎች ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጠቀሱ ጠቃሚ ምክሮችን የያዙ ጽንሰ ሐሳቦች ናቸው፡፡ ከግለሰባዊ የዕለት ተዕለት ስንክሳሮች በመውጣት በግዙፍ አገራዊ ዘርፈ ብዙ ምህዋር ውስጥ ስንቃኛቸው፣ ለሚያጋጥሙ ውስብስብ ችግሮችም ሆነ መልካም አጋሚዎች መሠረታዊ የሆነ ጭብጥ ያስይዛሉ፡፡ በተለይ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ቆም ብለን ራሳችንን እንድንመረምር ይጋብዙናል፡፡

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና የአኅጉሪቱን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኝነት ማጣት

የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት፣ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተቋቋመው በ1955 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ነው፡፡ ድርጅቱ ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው በ32 የአፍሪካ አገሮች ነው፡፡ ኅብረቱ ደቡብ አፍሪካ አባል እስከሆነችበት እ.ኤ.አ 1994 ድረስ 53 አገሮችን በአባልነት የያዘ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት 55 አገሮችን ያቀፈ አኅጉራዊ ድርጅት ቢሆንም፣ ከእነዚህ መካከል በኅብረቱ ንቁ ተሳትፎ የሌላቸው አገሮች ይገኙበታል፡፡

ጽንፈኝነት ለማንም አይበጅም!

ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አገር ናት፡፡ ከብሔር ማንነት ጀምሮ ቋንቋ፣ ባህል፣ እምነትና የመሳሰሉ በርካታ መገለጫዎች ባሉባት በዚህች ታሪካዊ አገር ውስጥ የአንድ ጎራ ኃያልነት ወይም የበላይነት ከቶውንም ሊኖር አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ዘመናት በተነሱ ገዥዎች ሥር ቢተዳደርም፣ ደጉንና ክፉን ጊዜ ያሳለፈው ግን ተሳስቦና ተደጋግፎ መሆኑን ፈጽሞ መካድ አይቻልም፡፡ ይህ ጨዋና አስተዋይ ሕዝብ አገሩን ከወራሪዎችና ከተስፋፊዎች በአንድነት ሲጠብቅ ዘመናትን ያሳለፈው፣ ከልዩነት ይልቅ ለአንድነት ትልቅ ግምት በመስጠቱ ነው፡፡

ሕይወት ሳይጠፋ ችግሮችን መፍታት ለምን ያቅታል?

ሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የጥምቀት በዓል ሲከበር በተቀሰቀሰ ግጭት የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በርካታ ዜጎች በተለያዩ ሥፍራዎች በደረሱ ግጭቶች ሞተዋል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እያቃተ፣ ክቡር የሆነው የሰው ሕይወት በከንቱ እየተቀጠፈ ነው፡፡ ሕይወት ሳይጠፋ ችግሮችን መፍታት ለምን እንደሚያቅት ግራ እያጋባ ነው፡፡ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ወይም ብስጭታቸውን ሲገልጹ፣ የፀጥታ ኃይሎች ኃላፊነታቸውን መወጣት ያለባቸው መረጋጋት በመፍጠር ነው፡፡ ችግር ባጋጠመ ቁጥር ጠመንጃ መተኮስ ሕይወት ከማጥፋት በተጨማሪ፣ በአገር ሰላምና መረጋጋት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡

ለሕዝብ ፈቃድና ፍላጎት መገዛት ባህል ይሁን!

የኢትዮጵያን መልካም ስምና ዝና ከሚያጎድፉ ረሃብ፣ የከፋ ድህነትና ኋላቀርነት ባልተናነሰ በእልህና በቂም ላይ የተመሠረተው የፖለቲካ ገመድ ጉተታ፣ አገሪቱንና ሕዝቡን ለዓመታት ጭንቅና መከራ ውስጥ መክተቱ መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት በበጎውም ሆነ በክፉ ጊዜ እርስ በርሱ እየተደጋገፈ ከወራሪዎችና ከተስፋፊዎች የጠበቃት አገሩ፣ በገዛ ልጆቹ መቅኖ እንድታጣ ሲደረግና የባዕዳን መዘባበቻ ስትሆን እንደማየት የሚያም ነገር የለም፡፡

የአገር ችግር የሚፈታው በኢሕአዴግ ብቻ አይደለም!

ኢትዮጵያ ለገጠማት ችግር የማያዳግም መፍትሔ ያለው ሕዝቧ ዘንድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጠረፍ እስከ ጠረፍ በአገሩ ጉዳይ ተሳታፊ ሆኖ ሐሳቡን በነፃነት መግለጽ ሲችል፣ አሁን ላጋጠመው አገራዊ የጋራ ችግር ሁነኛ መፍትሔ ያመነጫል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከአገር ህልውና በላይ ምንም ነገር የለም፡፡ ግለሰብም ሆነ ቡድን ከአገር በላይ መሆን አይችሉም፡፡