Skip to main content
x

ሕገ መንግሥቱን እንደገና መተርጎም አስፈላጊ መሆኑ የተብራራበት የውይይት መድረክ

ወ/ሮ ዓለሚቱ ገብሬ ነዋሪነታቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በከፋ ዞን በጊንቦ ወረዳ ነው፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት ሁለት ሔክታር መሬታቸውን አቶ ጫኔ ደሳለኝ ለሚባል ግለሰብ ለአምስት ዓመት እንዲጠቀምበት ያከራዩታል፡፡ አቶ ጫኔ ኪራዩ 50 ዓመት ነው በማለት በይዞታው ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በማውጣት ይዞ እንደተገኘ፣ ወ/ሮ ዓለሚቱ ያቀረቡት አቤቱታ ያስረዳል፡፡ በዚህም መሬቴን ይልቀቅልኝ ሲሉ ለጊምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ይመሠርታሉ፡፡

በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ለቀረቡ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች የኢሕአዴግ ምላሽ እየተጠበቀ ነው

አሥራ አምስት አገር አቀፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አራተኛ የመደራደሪያ አጀንዳ በሆነው የፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 ላይ ተከታታይ ድርድር ሲያደርጉ፣ ፓርቲዎቹ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ እንዲሰረዙ፣ እንዲሻሻሉና እንዲጨመሩ ብለው ላነሷቸው ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች የኢሕአዴግ ምላሽ እየተጠበቀ ነው፡፡

ለቂሊንጦ ቃጠሎ ዓቃቤ ሕግ የቆጠራቸው 28 ምስክሮች እንዳይሰሙ ትዕዛዝ ተሰጠ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ዓቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ዓቃቤ ሕግ ክስ ለመሠረተባቸው እስረኞች በምስክርነት ከቆጠራቸው 85 ምስክሮች ውስጥ 28 ሳይሰሙ እንዲታለፉ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የፓርላማው አዳዲስ ጅምሮችና አንድምታዎች

በሥራ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በሚከተለው የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የዲሲፕሊን (ሥነ ሥርዓት) መመርያ ምክንያት፣ ከሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ጋር የፖሊሲ ክርክር ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋስትናው አንድነቱ ብቻ ነው!

‹‹አንድ ከሆንን ፀንተን እንቆማለን፣ ከተከፋፈልን ግን እንገረሰሳለን›› የሚባለው ታዋቂ አባባል በዓለም ዙሪያ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኘ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ አንድነት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የአንድነትን ትርጉም ለመግለጽ ‹‹ድር ቢያብር አንበሳ ያስር››፣ ‹‹ለአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ››፣ ‹‹ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ››፣ ወዘተ. ዕድሜ ጠገብ አገር በቀል አባባሎች በስፋት ይታወቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ የሚታወቀውም የሚወዳት አገሩን ከባዕዳን ወራሪዎችና ተስፋፊዎች ለመከላከል በከፈለው ወደር የሌለው መስዋዕትነት ነው፡፡

የመላውን ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት የሚቻለው በትክክለኛ ቁመና ላይ በመገኘት ብቻ ነው!

በሩን ዘግቶ ለበርካታ ቀናት ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰንበቻውን በመሀል ባወጣው መግለጫ፣ ራሱን በመገምገም ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የሚመጥን ድርጅታዊ ቁመና ለመያዝ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ በአገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ ባደረገው ግምገማም የችግሮቹ ዓይነተኛ ባህሪያትና ዋነኛ መንስዔዎች ላይ ዝርዝር ውይይት መደረጉን፣ ለችግሮቹም የማያዳግምና መሠረታዊ የሆነ መፍትሔ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

አገር እስካሁን ያለችው በጨዋው ሕዝብ እንጂ በብቁ አመራር አይደለም!

ኢትዮጵያ እስካሁን ያለችው በዚህ ጨዋና ኩሩና አስተዋይ ሕዝብ ምክንያት እንጂ፣ በብቁ አመራር አለመሆኑ አሁን በትክክል ግልጽ እየሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጨዋና ኩሩ ሕዝብ በአስተዋይነቱና በአርቆ አሳቢነቱ ሳቢያ እርስ በርሱ ከመደጋገፍ በላይ፣ የሚወዳት አገሩ ክፉ እንዳይነካት ሲል በርካታ ችግሮችን ችሎ ኖሯል፣ እየኖረም ነው፡፡ ከአስመራሪው ድህነትና እንደ እሳት ከሚጋረፈው የኑሮ ውድነት ጋር እየታገለ፣ በየደረጃው ያሉ የአገር አስተዳዳሪዎችን በትዕግሥት ብዙ ጠብቋቸዋል፡፡ በስሙ ከሚነግዱበት ጀምሮ በአጉል ተስፋ እስከሚቀልዱበት ድረስ ከሚፈለገው በላይ ታግሷቸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የግጭት ዓውደ ግንባር አይሁኑ!

የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከበፊት ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ሁነኛ መገናኛ ሥፍራ በመሆናቸው ‹‹ትንሿ ኢትዮጵያ›› በመባል ይታወቃሉ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ለጋ ወጣቶች ከአራቱም ማዕዘናት የሚገናኙባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ብሔር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ እምነት፣ ወዘተ. ተቻችለውባቸው የመማር ማስተማር መርሐ ግብራቸውን ሲያከናውኑ ነው የሚታወቁት፡፡

የኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንከኖች መላ ይፈለግላቸው!

ሰባት ስድስት ያህል ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ከ80 በላይ ቋንቋዎች፣ በጣም በርካታ ባህሎች፣ ልማዶች፣ ወጎች፣ የአኗኗር ዘይቤዎች፣ የተለያዩ እምነቶችና አስተሳሰቦች ባሉባት በዚህች ታሪካዊት አገር ከፌዴራል ሥርዓት ውጪ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ በአገሪቱ የተለያዩ መልክዓ ምድሮች ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር፣ የመዳኘትና የጋራ ጥቅሞቻቸውን የሚያስከብሩበት ሕገ መንግሥትም ይኖራቸው ዘንድ የግድ ነው፡፡

ፓርላማው በ13 ድምፀ ተአቅቦ የደን ልማት ጥበቃ አዋጅን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢሕገ መንግሥታዊ ነው የሚል ክርክር የቀረበበትን የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ በ13 ድምፀ ተአቅቦ አፀደቀ፡፡ ኢሕአዴግ በሚመራበት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ መሠረት የፓርላማ አባላት ከፓርቲው የበላይ አካል የተሰጡ ውሳኔዎችን መቃወም እንደ ዲስፕሊን ጥሰት የሚቆጠር በመሆኑ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቃውሞ ክርክር ያቀረቡ አባላትና ሌሎችም በተቃውሞ ድምፅ ከመስጠት ይልቅ ድምፅ ተአቅቦ ማድረግን መርጠዋል፡፡ አንድ ረቂቅ አዋጅ በ13 የኢሕአዴግ አባላት ድምፅ ተአቅቦ ሲፀድቅም የመጀመርያው ሊሆን እንደሚችል ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡