Skip to main content
x

እንተላለፍ እንጂ?

እነሆ ጉዞ ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ። ምድር ትውልድን በትውልድ እየተካች የደከመውን በሞት ሸኝታ ለጋውን እያሳደገች ፋታ አሳጥታ ታራውጠናለች። ተስፋ አይሞትምና እውነት ለመሰለን ሁሉ እየደከምን በባዶ እንደመጣን በባዶ እስክንሸኝ እንደክማለን። እርቃናችንን እንደመጣን እርቃናችንን እንቀበራለን።

ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ባንሰጣጥስ?

እነሆ መንገድ! ታክሲያችን በወሬና በጫጫታ ደምቃለች። ወያላችን ደጋግሞ ፀጥታ እያለ ተንሸራታቹን በር ይደልቀዋል። ‹‹ምንድነው ነገሩ? ቤተ መጻሕፍት የገባን መሰለው እንዴ ሰውዬው?›› ይነጫነጫሉ ሦስተኛው ረድፍ ላይ የተሰየሙ ወጣቶች። ‹‹ምናለበት አንዴ ወሬ ብንሰማ? ድምፅ ስጠው አቦ፤›› ወያላው ቀንድ ሊያበቅል ምንም አልቀረውም። ሾፌራችን የሬዲዮኑን ድምፅ ይጨምራል። ‹‹አሁን እኮ ጥያቄው ምርጫው ይራዘም? ወይስ አይራዘም ነው? አድማጫችን በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ?›› ጋዜጠኛው ይጮሃል።

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ ኪስ ይሻላል!

እነሆ መንገድ! ከፒያሳ ወደ ሜክስኮ ልንጓዝ ነው። ሰው ብርቱው በመጓዝ ምኞቱ መንገድ አበጅቶ መራመድ አይታክተውም። ወዲያ ይመጣል ወዲያ ይሄዳል። የመገንባት ጥረቱ ሳይነጥፍ የማፍረስ ጥበቡም አይቅርብኝ እንዳለ በመንታ ማንነት ይወዛወዛል። “ታክሲ! ታክሲ!” ይጮሃል አንድ ሰው። ወደ መጨረሻው አካባቢ አንድ ጎልማሳ ያላማቋረጥ ስልክ እያወራ ነው።

ምነው ተናካሹ በዛ?

እነሆ መንገድ! እነሆ ጉዞ! ከወሎ ሠፈር ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። መንገድ አልቆ መንገድ ልንጀምር፣ ዕድሜ ጨርሰን ዕድሜ ልንቀጥል እንራመዳለን። ወያላው፣ ‹‹የሞላ ሁለት ሰው›› እያለ ይጮሃል። ‹‹ምንድነው የሚያወራው?›› አንዱ ተሳፋሪ ይጠይቃል። ታክሲው ባዶ ነበር። ‹‹የመዋሸትን መብት ለመንግሥት ብቻ የሰጠው ማን ነው? ትገቡ እንደሆነ!›› ግቡ ይላል ወያላው የሰውየውን መደናገር ግልጽ አደርጋለሁ እያለ ነገር ያወሳስባል።

ለመውጣት ግፊያ ለመውረድ ግፊያ!

እነሆ ጉዞ እነሆ መንገድ! ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። መስኮቶች ተከፋፍተዋል። በተከፈቱት መስኮቶች ተሻግሮ እየነፈሰ የሚገባው አየር ግን የተዘጋ ነው። እንዲያ ነው! “የቆጡን እናወርዳለን ብለው የብብታችንን አስጣሉን እኮ እናንተ?” ይላል አንዱ። ደንዳና ሰውነቱ መተማመኛ ዛኒጋባ እንዳጣ ያስታውቅ ነበር። ‘እንዴት? እነማን  ናቸው እነሱ?’ መሰል ተመሳሳይ ጥያቄዎች የሚጠይቀው ሰው አጠገቡ የለም። ውለውም ሆነ አድረው ተጠያቂዎቹና ተተችዎቹ ተመሳሳይ ናቸው። በምንመላለስበት ጎዳና ሁሉም የሰው ጉድፍ ጠቋሚ ነው።

እንዲያው በጨረፍታ ልባችን አይምታ!

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ አያት። ‹‹የቆጡን እናወርዳለን ብለው የብብታችንን አስጣሉን እኮ እናንተ!›› ይላል አንዱ። ደንዳና ሰውነቱ መተማመኛ ዛኒጋባ እንዳጣ ያስታውቅ ነበር። ‘እንዴት? እነማን ናቸው እነሱ?’ መሰል ተመሳሳይ ጥያቄዎች የሚጠይቀው ሰው አጠገቡ የለም። መንገዱ ተወጥሮ ከአሁን አሁን ተነፈሰ እያስባለ ያራምደናል።

አዋቂ ሲጠፋ ታዋቂ ይበዛል!

እነሆ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ ልንጓዝ ነው። ዕቅድ በማይገዛው አንዳንዴም ድካም መሪውን ጨብጦ የማስተዋል ቀልብ በሚከዳን ጎዳና ላይ ዛሬም በእንፉቅቅ እንጓዛለን፡፡ ሳይጀመር የሚያልቀው፣ ሳይወጠን የሚከሽፈው፣ ሳይታለም የሚፈታው ነገር ብዛት የእኔ ቢጤውን አዝሎታል። ዝለቱ ይመስላል ጎዳናውን የሽሙጥና የትችት አውድማ ያደረገው።

ችግር ፈጣሪ መፍትሔ የለውም!

እነሆ መንገድ። ከወሎ ሠፈር ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ‹‹አቦ ደመና ነው መነጽሩን አውልቀህ ምናለበት ሰውን ብታየው?›› ይላል በትምባሆ ጭስ ከሰል የመሰለ ከንፈሩን ደጋግሞ የሚያረጥበው ሾፌራችን።

ጥላቻና ውርስን ምን አገናኛቸው?

እነሆ ዛሬ የምንጓዘው ከቦሌ ወደ ካዛንቺስ ነው። ተሳፋሪዎች ቦታችንን ከያዝን ከየት ማለት ጀመርን። ከብዙ ዓይነት የሕይወት መንገድ፣ አስተሳሰብና እምነት ያለቀጠሮ ታክሲያችን ውስጥ መሰባሰባችን እየቆየ የሚደንቀን ጥቂት ነን። “ማን ወደ ማን ይሆን የሚገሰግሰው፣ መቼም ያገናኛል መንገድ ሰውና ሰው፤” እንዲሉ፣ ጉዞ ሰበብ ሆኖ ሰው ከሰው እንዲህ ያለ ቀጠሮ ይገናኛል።

የልብን ስብራት በምን ያክሙታል?

እነሆ ጉዞ። ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበልን ባቀናነው፣ ባፈረስነው፣ ባሳመርነው፣ በቆፈርነው ጎዳና ዛሬም በ‘ኧረ መላ፣ መላ’ ዜማ ጉዟችንን ጀምረናል። ‹‹አለመጠጋጋት የጠባብነትና የትምክህተኝነት አስተሳሰብ ማሳያ ነው። ሄይ . . . ጠጋ ጠጋ. . .” እያለ ወያላው ትርፍ ያግበሰብሳል። “ምን አስገለበጠኝ ወተቱን በጋን፣ ችዬ እገፋዋለሁ የማልለውን?” ስትል መላ የጠፋት፣ መላ የጠፋበት በበኩሉ፣ “ከቶ አንቺ አይደለሽም ጥፋቱ የእኔ ነው፣ እንደማይሆን ሳውቀው የምመላለሰው፤” ይላታል።