Skip to main content
x

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

ይህ አጭር የግል አስተያየት የኢትዮጵያ ምኅዳሮች የኢትዮጵያውያን ሴቶችንና ሴት ልጆችን ድምፅና አመለካከት ያካተቱ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ሰፊ ውይይቶችን ለማስጀመር ታስቦ የተጻፈ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በትረ ሥልጣኑን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር መሠረት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጻፍነው ግልጽ ደብዳቤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ፍትሕን ለማግኘት የሚያደርጉት ተጋድሎ መጠነ ሰፊ ውጤት እንዲኖረው ለማስቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕውቅና እንዲሰጡት የሚያበረታታም ነው።

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

አገራችን በከፍተኛ ችግር ውስጥ በነበረችበት አጋጣሚ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጥዎ፣ ከሕዝቡ ጋርም በጋራ በመሥራት አገራችንን ከገባችበት ችግር ለማውጣት በማመንዎና ቆርጠው በመነሳትዎ በቅድሚያ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ እመኛለሁ፡፡

ሳታጣ ያጣችን አገር እንታደግ

ይህች አነስተኛ ማስታወሻ ልጽፍ ያነሳሳኝ አገራችን በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ ሀብት የታደለችና ምንም ቀረሽ የማትባል አገር ብትሆንም፣ ሕዝቧ ከዓመት ወደ ዓመት ችግረኛና ሁሌም ተመፅዋች፣ የአገሮች ሁሉ የበታች ሆናለች፡፡

ሰሜናዊው የጉዞ ማስታወሻ

ከእያንዳንዱ ዕድሜ ጠገብ ታሪክ አጠገብ፣ ትንፋሽን ነጥቆ ከሚያስቀር ውብ፣ አስደናቂ፣ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ሥፍራዎችን ከቦ የሚገኝ ማኅበረሰብ፣ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው የማንነቱን ቅኝት ለዛ የሚመሰክር፡፡ ይህ ሰው ለማተቡ ሟች ነው፣ ይህ ሰው ጨዋታ አዋቂ ነው፣ ይህ ሰው ቀልዱ ጊዜና ቦታ አለው፣ ይህ ሰው እንግዳ አክባሪ ነው፣ ይህ ሰው ከሰሜን ብቻም አይደለም፣ ከደቡብ ብቻም አይደለም፣ ከምሥራቅ ከምዕራብ ከመሀል ብቻም አይደል ከመላው ኢትዮጵያ እንጂ፡፡

ያላሳከከን ቦታ ማከክ ትርፉ ቁስለት ነው

ይኼንን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ ዋናው ጉዳይ፣ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለሥልጣን የሥራ አፈጻጸም ሲሰጡ የነበሩ መግለጫዎችን አስመልክቶ መሥሪያ ቤቱ ከምሥረታው ጀምሮ እየተንከባለሉ የመጡት ችግሮች ለዚህ አፈጻጸም ድክመት እንደዋና መንስኤ መወሰድ እንደሚገባቸው እነዚህን መግለጫዎች ለሚዲያ ለሰጡ፣ ለጻፉና ላነበቡ አካላት እውነታውን ለማሳወቅ፣ እንዲሁም ቀደም ሲል ስለመሥሪያ ቤቱ ግልጽ ግንዛቤ ላልነበራቸው የመንግሥት አካላት ደግሞ የነበሩትንና አሁንም ያልተፈቱትን ችግሮች በግልጽ ማሳወቁ በቀጣይ መወሰድ ለሚገባቸው የመፍትሔ እርምጃዎች አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናል ብዬ በማመን ነው፡፡

ደበበ ሰይፉ ተወዳጅ ገጣሚ ብርቱ ሐያሲ

ደበበ መምህሬ አልነበረም፡፡ በአካል የማየት ዕድሉም አልነበረኝም፡፡  ከደበበ ጋር ምንም ዓይነት የጋብቻም ሆነ የሥጋ ዝምድና የለኝም፡፡ ቤቱ የት እንደሆነ አላውቅም፡፡ ደበበን የሚያውቁ የቅርብ ሰዎች ስለ ደበበ ቀን ከለሊት አላጫወቱኝም፡፡

ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ይገባ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን አዲሱ ካቢኔያቸውን በማዋቀር ሥራቸውን በሙሉ ኃይል መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ባሳለፍናቸው ጊዜያት በሁከት፣ በሰላም መደፍረስና የውስጥ ሽኩቻ አገር ስትታመስ ከርማለች፡፡ ከዚያም አልፎ በተለይ በመንግሥት ወገን በስብስብና በተሃድሶ፣ አልፎም በሹም ሽርና ሽግሽግ፣ አሁን ደግሞ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በርካታ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት ባክኗል፡፡

መርማሪ ኮሚስዮን

የመርማሪ ኮሚሽን አዋጅ እንዲረቀቅ ንጉሣዊ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ከመጋቢት 16 ቀን 1966 ዓ.ም. አዋጁ እስከፀደቀበት ሰኔ 8 ቀን 1966 ዓ.ም. ድረስ መለዮ ለባሹን ወክሎ በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የነበረው በኮሎኔል የዓለም ዘውድ ተሰማ ሊቀመንበርነት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ይመራ የነበረው የጦር ኃይሎች ኮሚቴ በመባል የሚታወቀው ነበር። ኮሚቴው የተቋቋመውም መጋቢት 1966 ዓ.ም. ነው።

የአዋሽ ጦማር ለዓባይ

ይድረስ ለተከበርከው ለኃያሉ ዓባይ፣ ባያሌው እንዴት አለህ? እኔ አንተ መብራት ሆነህ ትመጣለህ ከሚል ናፍቆት  በስተቀር ክፉንም ደጉንም እያሳለፍኩ አለሁ፡፡ ለመሆኑ አንተ ማነህ እንዳትለኝ፡፡ እኔ ይህንን ደብዳቤ የጻፍኩልህ የአገርህ ልጅ አዋሽ ነኝ፡፡ አዎ አዋሽ ወንዝ፣ ለሀገር ልጅ የመድረስ፣ አንዲት ጠብታ ውሃ ወደውጪ የማላፈስ፣ አዋሽ አንጀት አድርስ ነኝ፡፡ እንደዚህ ስልህ መቼም ጎረርክብኝ እንዳማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡