በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሸጥ የተወሰነውን ባለሰባት ወለል ሕንፃ የጨረታ ሒደቱን በ680 ሚሊዮን ብር በማሸነፍ የገዛው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ የሚጠበቅበትን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ በማድረግ ሕንፃውን እንደተረከበ አስታወቀ፡፡

ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከፍተኛው እንደሆነ የተነገረለትን የ881 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ያስገኘው ቡና፣ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ መሪነቱን ቀጥሏል፡፡

  • ከዓለም አቀፍ አሥር ጎብኚዎች አራቱ አፍሪካውያን ናቸው
  • አዲስ አበባ ከሆቴል ፎረም የ5.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች

ከጥቂት ቀናት በፊት ይፋ የተደረገውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ (UNCTAD) የተሰናዳው ሪፖርት፣ የአፍሪካ ቱሪስቶች ለአኅጉሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ እያበረከቱ የሚገኙትን አስተዋጽኦ ተንኗል፡፡

  • በ2009 በጀት ዓመት ከ5.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት ነበር

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በ2010 በጀት ዓመት 101 ፕሮጀክቶችን ለመተግበር መነሳቱንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የ6.38 ቢሊዮን ብር በጀት እንዳፀደቀለት አስታወቀ፡፡

አቢሲኒያ ባንክ የ2009 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሰጠው የብድር መጠን በ73.3 በመቶ በማሳደግ 14.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ደግሞ ከ 20.7 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወቃል፡፡ የማቋቋሚያ አዋጁ እንደገና እንዲሻሻል የተፈገለው የአገሪቱን የቡና ዘርፍ ብቻም ሳይሆን ወጪ ንግዱን ችግሮች ለማሻሻል ከተጀመረው እንቅስቃሴ ጋር  በማያያዝ ለውጥ እንዲመጣ በማሰብ ነው፡              

Pages