Skip to main content
x

ጃፓንና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ስምምነት ለመፈረም ድርድር ጀምረዋል

ለዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያቀርበው የቆየውን ውትወታ፣ በመንተራስ በጃፓንና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ስምምት ለመፈረም የሚያስችሉ ድርድሮች ተጀመሩ፡፡ የመጀመሪያው ኦፊሴላዊ የድርድር መድርክ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ ከጃፓን በመጡ ባለሥልጣናትና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኃላፊዎች መካከል፣ ከጥር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት ድርድር መካሄዱን ከጃፓን ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የድርድሩን ዝርዝር ጉዳይና ይዘት ለማወቅ የተደረገው ጥረት ባይሳካም፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ግን ድርድሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደሆነ በመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

የእንግሊዝ ኩባንያ በኢትዮጵያ የ200 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ሊጀምር ነው

ኢንትሬድ የተሰኘውና ዋና መሥሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ኩባንያ በሱዳን ሰፊ የጥጥ እርሻ እንዳለው ከመግለጹም ባሻገር፣ በኢትዮጵያ ሰፊ የጥጥ እርሻ የማልማት ዕቅድ እንዳለውና በ200 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ሦስት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መነሳቱን አስታወቀ፡፡

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ድርሻ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ባለሙያዎች ገለጹ

ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው የጃፓንና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ወቅት በቀረቡ የጥናት ውጤቶች መሠረት፣ የአገሪቱ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጠበቀውን ውጤት ከማስገኘት ይልቅ እያሽቆለቆለ እንደመጣ ታይቷል፡፡

የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ በግሉ የገነባው ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተጠናቀቀ ነው

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ትልልቅ የሚባሉ የግንባታ ሥራዎችን በማከናወን የሚታወቀው በቻይና መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው ቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ሲሲሲሲ)፣ በግሉ እየገነባ ያለውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡