Skip to main content
x

የ1950ዎቹ ኢትዮጵያውያን ጄኔራሎች

በመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (1923 - 1967) የጦር ኃይሎች ከፍተኛ ጄኔራል መኰንኖች መካከል ግንባር ቀደምቱ በፎቶው የሚታዩ ናቸው፡፡ ፎቶው ከ1953 ዓ.ም. የታኅሣሥ ግርግር በፊት የተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአፋር ባህላዊ ቤቶች

በኅዳር ወር መጨረሻ በአፋር ክልል የሚከበረው 12ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለእንግዶች ማረፊያ እንዲሆኑ የአፋርን ሕዝብ አኗኗርና ባህል እንዲያሳዩ ተደርገው የተሠሩት ባህላዊ ቤቶች 480 ናቸው፡፡

‹‹ከማን አንሼ››

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ኤድና ሞል ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ ከመኪኖች ጋር እየተጋፉ ያለፉት አህዮች ናቸው፡፡ በአፀደ ሥጋ የሌለው ዕውቁ ደራሲ መንግሥቱ ገዳሙ ‹‹ከማን አንሼ›› የምትባል ቤሳ ልብወለድ ነበረችው፡፡ የፊት ሽፋኗ አህያ ሙሉ ሱፍ ከነሰደርያውና ካፖርት ደርባ፣ ባርኔጣ ደፍታ፣ መነጽር አጥልቃ ትታይበታለች፡፡

ዝንቅ

በድርቅና በግጦሽ እጦት ምክንያት ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ተሰደው የነበሩ ሳላዎች ወደ መኖሪያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡

ቀዳሚው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት

በፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም. ሰማዕት ለሆኑት አቡነ ጴጥሮስ፣ ከ1933 ዓ.ም. ድል በኋላ በአዲስ አበባ የቆመው የመጀመርያው የመታሰቢያ ሐውልት በፎቶው (በ1941 ዓ.ም. የተነሳ) የሚታየው ነበር፡፡

መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር

መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር ከአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ 2 ሺሕ አገልጋዮች ፅናፅን፣ መቋሚያና ከበሮ ይዘው በዓሉን በወረብ አድምቀውታል፡፡ ምዕመኑም ጧፍ በመለኮስ የደመራውን ምሽት አስውበውታል፡፡ በዕለቱ የውጭ አገር ዜጎችም ነጠላቸውን ጣል አድርገው ጧፍ አብርተው ታይተዋል

ዓይን ያጣው!

ሲኤምሲ ጊብሰን ትምህርት ቤት አካባቢ የእግረኛ መንገድ ላይ የሚገኝ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ክዳን ለፅዳት ተከፍቶ ሳይከደን ተትቷል፡፡ የ2010 ዓ.ም. ትምህርትን የጀመሩ ተማሪዎች በስፍራው ሲያልፉ ይስተዋላሉ፡፡