Skip to main content
x

ከቅስም ሰባሪ ይሰውረን!

ሰላም! ሰላም! ‹‹ሥልጣን ከላይ ካልተሰጠ በቀር ከሌላ ከማንም አይገኝም፤›› እያሉ ባሻዬ ሰሞኑን ይሰብኩኛል። ሙጋቤን ለመደገፍ ሳይሆን አይቀርም። ወይም ሌላ ሰው አላውቅም ብቻ። የማውቀው አንድ ነገር ነው። ሲያበቃ ሁሉም ያበቃል። ኃያላን በኃይላቸው፣ ጎበዛዝት በጉብዝናቸው አይበረቱም።

የታገሰ ፅልመትን ብርሃን ያለብሳል!

‹‹ውኃ ወርዶ ወርዶ አቀበት ይዋኛል፣ አትበሳጭ ልቤ የባሰ ይገኛል፤›› አለ የወንዙን ልጅ ትቶ የሰው አገር ሲያድን የመነመነው። ምን በምግብ ዋስትና ራስን ቢችሉ፣ መመንመን አይተወንማ። እና ውዷ ማንጠግቦሽ ራሷን አልችል ብላው፣ ደረቴ ላይ ጣል አድርጋው ሳለ ቅዠት ነው መሰል ብንን አልኩ። ቀን እየባነንን ሌሊት ይቀናናል። እንዲያው እኮ! ስባንን ቀሰቀስኳት። እየተገላበጠች፣ ‹‹ስንት ሰዓት ነው?›› ብላ ጠየቀችኝ። አይገርምም? እስኪ አሁን ጨለማ ቆጠረ አልቆጠረ ምን ይፈይዳል? ‘ከሌሊቱ ስንት ሰዓት ነው?’ ይሉናል ደርሰው።

በሽተኛው ብዙ መድኃኒቱ ትንሽ!

ሰላም! ሰላም! አንዱ ነው አሉ፡፡ አንዱ ስላችሁ ደግሞ ይኼ ኮምፒውተር ላይ ያለው ማለቴ አይደለም፡፡ እሱንማ መሆን ብንችል በምን ዕድላችን? የኑሮ ሩጫችንን አቋርጠን ኑሮን ራሱ አንዱ እያደረግን አንዘፍንም ነበር? እሱም አውቆ ሰማይን አርቆ ሆነና ነገሩ ሰው ሕይወቱን አንዱ ማለት ቢያቅተው በአምሳሉ ሮቦት ፈጠረ፡፡ ይኼም እንደ አንዱ ከተቆጠረ ቁጠሩት፡፡

ሞኝ ሲሰምጥ ብልጥ ይንሳፈፋል!

ሰላም! ሰላም! እንዴት ነው መረብና ኑሮ? የመረብ ዘመን አይመስላችሁም መደፋፈሩን ያናረው? እ? እውነቴን እኮ ነው። እንጃ በስንት ፐርሰንት መሆኑን ግን። ጥያቄዬ እኮ እንዲያው ለጨዋታ ለ‘ኦፒኒዬን’ ነው እንጂ፣ ወጋችንን የታዳጊ አገር  የኢኮኖሚስቶች ማኅበር ባናስመስለው ደስ ይለኛል። ደላላው አንበርብር ምንተስኖት ዶላር በመረብ እያጠመደ ያስተነትናል ብላችሁ እሙኝ።

እሳት ጎርሰን ቤንዚን ጠጥተን ይቻላል ወይ?

ሰላም! ሰላም! ደላላው አንበርብር ምንተስኖት የተቀደደ ሰማንያ መስፋት ጀምሯል እያለ አገር ያማኛል አሉ። ‹ቀዶ ቀዶ ከጨረሰ በኋላ አገር ሁሉ የሚያማህ ምን አምጣ ብሎ ነው?› አትሉኝም። እኔ ምን አውቃለሁ? ‹‹እውቀት ቢኖረኝ ኖሮ ደላላ እሆን ነበር?››

እንረጋጋ እንጂ!

ሰላም! ሰላም! ‹እንቁላል ቀስ በቀስ ሽጉጥ ይሆናል› ማለት ጀመርን አሉ። ዕድገታችን የማያመጣብን ጉድ የማይለዋውጥብን አባባል የለም። አሁን እስኪ አንድ እንቁላል በስንት ተገዝቶ፣ ስንቴ ተቀቅሎ፣ ስንቴ ተጠብሶ ተበልቶ ነው ወደ ሽጉጥነት ያደገው? የሚለው ጥያቄ የእኔም ነው። በጥያቄ ላይ ጥያቄ ስንከምር በትውልድ ላይ ትውልድ ይደረብና ይኼው ነገር ሁሉ ርችት ይሆናል። እውነቴን እኮ ነው። በቀደም ከእንቅልፌ ስነቃ ስልኬ ጢን ብላ ጮኸች።

ጣፊያና ሻኛን እንለይ እንጂ!

ሰላም! ሰላም! ‹‹የሰው ልጅ ባህሪው የሚወሰነው አካባቢውን ለመቋቋም በሚያደርገው ተጋድሎ መሆኑን ያወቅኩት ገና በልጅነት ዘመኔ ነበር . . .›› አለ ብሎ ምሁሩ የባሻዬ ልጅ ስለሌኒን ወዳጅ ማክሲም ጎርኪ ሲያጫውተኝ ሰነበተ። እኔስ ማነኝ ብዬ ተራዬን የሚከተለውን አልኩ።

የፊቱ ከኋላው ተምታታብንሳ?

ሰላም! ሰላም! ስንሞት በፎቶ እንጂ በባንክ አካውታችን የሚለቀስልን ይመስል ገንዘብ ላይ እኝ ብለን ልንሞት ነው አሉ። ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር የምንሸጋገረው እንግዲህ በዚህ አያያዛችን መሆኑ ነው።

ኧረ ጀማው እስኪ እንደማመጥ?

ሰላም! ሰላም! ሰው ዘንድሮ ምን እንደበላ ወይ ምን እንዳበሉት አላውቅም፣ ከራስ በላይ አዋቂ ሆኗል። ለራስ የሚያውቅ ጠፍቶ ምክር በዱላ በሆነበት አገር ሰው ለመምከር የሚያዘው ሠልፍ የታክሲ ሠልፍ ያስንቃል።

አሁንስ አልበዛም?

ሰላም! ሰላም! “የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ የኢትዮጵያን የሰሜን ተራሮች ተነስታችሁ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ስጠሙ ብላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ፤” ብለው ማስተማር ቢጀምሩስ ቴክሳሶች? ሲያሻን ተራራ እያንቀጠቀጥን ሲያሻን ደግሞ ተራራው እየተንቀጠቀጠብን የእኛ መጨረሻ እንዲያው ምን እንደሚሆን ዝም ብሎ ማየት ነው።