Skip to main content
x

በገቢዎች ጽሕፈት ቤት ቃጠሎ ምክንያት የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ከምክትላቸው ጋር ከሥልጣን ተነሱ

ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በእሳት ቃጠሎ ከወደመ በኋላ፣ ተገቢውን ዕርምጃ አልወሰዱም በሚል ምክንያት የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ አኬኔ ኦፓዳ እና ምክትላቸው አቶ ጀምስ ኬች ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) ለሳምንት ያህል ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ምክትላቸው ጥፋተኞች ናቸው በማለት ከሥልጣናቸው ማንሳቱ ታውቋል፡፡

የፌዴራል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች  ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ

የፌዴራል መደበኛ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በጥምቀት በዓልና በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ወቅት፣ የፀጥታ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል በመግለጽ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫ፣ የጥምቀት በዓልም ሆነ የኅብረቱ የመሪዎች  ጉባዔ በየዓመቱ ያለምንም ችግር ሲከበር እንደቆየ በማስታወስ፣ ዘንድሮ ግን ሁነቶቹ በሰላም እንዳይከናወኑ ለማድረግ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል፡፡

የሕግ የበላይነትን የሚፈታተኑ ድርጊቶች ይወገዱ!

መንግሥት ሰሞኑን በመጀመርያ ዙር 528 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንደሚለቀቁ አስታውቋል፡፡ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ደግሞ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያደረገውን ግምገማ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው ባለ ስምንት ነጥብ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረጉ ሰዎች ከእስር መፈታታቸው መልካም ጅምር ነው፡፡ በዚህ መሠረት ሒደቱ ቀጥሎ በርካቶች ከእስር እንደሚለቀቁ ይጠበቃል፡፡

ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራን በወፍ በረር ዕይታ

ከዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ወደ ሰሜን ማዘጋጃ በሚወስደው በላይ ዘለቀ ጎዳና ጥቂት እንደተጓዙ በስተቀኝ በኩል አንድ ደሴት ላይ ሁለት ዓይነት ፖሊሶች ይገኛሉ፡፡ መጀመርያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) ቀጥሎ ደግሞ የብዙ ኢትዮጵያውያን እንባና ደም የፈሰሰበት የፌዴራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ ማዕከል (ማዕከላዊ) ይገኛል፡፡

ዮድ አቢሲኒያ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል የሚል አቤቱታ ለመንግሥት አቀረበ

ጥርጣሬውን ወደ አቶ ሰይፉ ፋንታሁን ማድረጉን ሰነዶች ይጠቁማሉ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ታዋቂ በመሆን ‹‹የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር›› ተብሎ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተሰየመው ዮድ አቢሲኒያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል›› በማለት አቤቱታ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ማቅረቡ ታወቀ፡፡

የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ዶ/ር መረራ ለብይን ተቀጠሩ

ዓቃቤ ሕግ እንዲከላከሉ ብይን ይሰጥልኝ ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 01/2009 አንቀጽ 12(1) ሥር የተደነገገውንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርምጃ አፈጻጸም አንቀጽ 2(1)ን በመተላለፍ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ ወንጀል የተከሰሱት ዶ/ር መረራ ጉዲና ለብይን ተቀጠሩ፡፡

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ

የጋምቤላ ከተማ መምህራን ሥራ አቁመው ነበር የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት፣ ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለእሑድ አጥቢያ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በተነሳ ቃጠሎ ወደመ፡፡ የክልሉ ፖሊስ የጠረጠራቸውን አሥር ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገልጿል፡፡ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አከነ ኦፓዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት በቃጠሎው ኮምፒዩተሮች፣ ሰነዶችና የቢሮ ዕቃዎች ወድመዋል፡፡ ከቃጠሎው ጋር በተገናኘ አሥር ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ቃላቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡  

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎችን ግጭት ሲከታተል የነበረው ግብረ ኃይል አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ

ከወራት በፊት በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ሲከታተል የነበረው ግብረ ኃይል፣ አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የፌዴራል ግብረ ኃይል ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የሶማሌ ክልል በግጭቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ባለመቻሉ፣ ተባባሪ ያልነበሩ አመራሮች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡