Skip to main content
x

የአገራችንና የአኅጉራችን ትኩስ ፈተናዎች

የትራምፕ የአሜሪካ መንግሥት “አሜሪካን ከዓለም እየነጠለ ነው . . . ግሎባላይዜሽንንና ነፃ ገበያን እየተቃረነ ነው . . . በገበያ ጥበቃ የተጠመደ ነው . . . ” እየተባለ ይወረፋል፡፡ በሀብታም አገሮች አካባቢ ይህን መሰሉ ነቀፋ ቢደራ የተነካባቸውን ወይም የተስተጓጎለባቸውን ወይም ሥጋት ያገኘውን የንግድ ጥቅማቸውን ወደነበረበት የመመለስ ትግል መሆኑ ነው፡፡

የኮረሙን ነገር እስኪ እንነጋገር!

አገራችን ዛሬም አስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ናት፡፡ አስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ስንገባ በሁለት ዓመት ውስጥ ይህ ሁለተኛው ጊዜ ነው፡፡ መላውን የ2009 የካሌንደር ዓመት ከሁለት ወር ‹‹ፋታ›› በቀር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ነበርን፡

የግንባራችሁ ሊቀመንበር ‹‹ምርጫ›› የእናንተ ጉዳይ ብቻ አይደለም

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ ካስታወቁ እነሆ እሑድ ሲመጣ (ይህን ጽሑፍ የምታነቡት እሑድ ነው ብዬ ነው) 18ኛ ቀን ሆነ፣ በዚህ ምክንያትም ባይሆን፣ ከዚህ ጋር ግንኙነት ይኑረውም አይኑረውም፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የታወጀው በማግሥቱ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘለሉ ወይስ ተገፉ?

ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚባል ስያሜና የሥልጣን ቦታ አስተዳደሯ ውስጥ ያስተዋወቀችው በ1936 ዓ.ም. መጀመርያ ላይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ከጣሊያን ወረራና ከነፃነት ወዲህ ሥራ ላይ በነበረው ሕግ መሠረት፣ የኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሁሉ በንጉሠ ነገሥቱ የበላይ አዛዥነት ሥራቸውን የሚያካሂዱ ነበሩ፡፡

አገር የሚያስፈልጋት ከውድመትና ከጥቃት የፀዳ ትግል ነው

ላለፉት 26 ዓመታት ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር አብዛኛውን ጊዜ በሐሳብና በምናብ፣ አንዳንዴም እዚህ ጋዜጣ ላይ በሚወጣ ጽሑፍ ኢሕአዴግን ‹‹በላ ልበልሃ!›› እያልኩ የምሞግትበት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ግንቦት 20 ለኢሕአዴግ ከሞላ ጎደል አልፋና ኦሜጋው ነው፡፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የተመሠረተችበት፣ ታሪኳ መጻፍ የጀመረበት፣ ወዘተ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ያለውን ቢልም አንድ ነገር ግን እውነት ነው፡፡ ግንቦት 20 የወታደራዊ አምባገነንነት እንዳይሆን የፈረሰበት፣ ፈላጭ ቆራጮች እምቧጮ የሆኑበት፣ ወታደራዊ ኃይላቸው፣ የፀጥታ መረባቸውና ፓርቲያቸው የተበጣጠሰበት ዕለት ነው፡፡

ለኅብረ ብሔራዊ ትግል ወደፊት በሉለት!

እነሆ የ2010 ዓ.ም. የካቲት አባተ፡፡ የ1966 ዓ.ም. የየካቲት አብዮትም 44 ዓመት ሞላው፡፡ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ተጋምሶ 1966 ዓ.ም. በመጣበት ጊዜም ቢሆን፣ የመሳፍንቱንና የመኳንንቱን ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እያሳሳና እያደከመ የተባዛና የተጠናከረ ሥልጣን የቀረው የካፒታሊስት መደብ በኢትዮጵያ አልተፈጠረም ነበር፡፡ መሳፍንቱንና መኳንንቱም ወደ ካፒታሊስትነት የተሸጋገሩበት ለውጥ አልነበረም፡፡ ስለዚህም ያኔም ዋናው ጉዳይና ትግል እንደ ከዚያ በፊቱ ጭሰኝነትና ገባርነትን የማስወገድ ለውጥ ነበር፡፡

ለንቀትም ለእብሪትም የማይመች ዴሞክራሲያዊ ትግል ያስፈልገናል

ስለሕዝቦች ልዕልናና ስለዴሞክራሲ ድል መምታት እነሆ አሁንም 27 ዓመት ላይ ሆነን እያወራን ቢሆንም፣ ዛሬም የፀረ ዴሞክራሲ የአፈና ዘይቤዎች እንደደላቸው ናቸው፡፡ አሁንም የሕዝብ ቅሬታዎች መተንፈሻ አጥተው መጠራቀማቸውና አጋጣሚ እየጠበቁ መፈንዳታቸው አልተቋረጠም፡፡ ስለጥበትና ስለትምክህት አደገኛነት ለዓመታት ስናወራ ብንኖርም፣ ዛሬም አገሪቷን የሚንጧትን ችግሮች መስፋፋታቸውን ማዳከምና አደጋቸውን ማምከን አልተሳካልንም፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሆይ!

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የታኅሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ‹‹ጥልቅ›› የግምገማና የውሳኔ ዜና እና ሪፖርት ዛሬም ጥር ወር አጋማሽ ላይ እያለንም በእንጥብጣቢ ከሚነገረን በላይ፣ የፓርቲውንም ሆነ የመንግሥትን ሙሉ እምነትና ሁሉንም እውነት ዝርግፍ አድርጎ የሚያሳይ አይደለም፡፡ የዓለም የመገናኛ ብዙኃንና ስም ያላቸው መንግሥታትና የመንግሥታት ማኅበራትና ቡድኖች በተለይ ትኩረት ሰጥተው ዜና ያደረጉትና ያበረታቱት፣ ‹‹የታሰሩ ፖለቲከኞች›› ወይም ‹‹የፖለቲካ እስረኞች›› ጉዳይም ገና እንዳወዛገበ ነው፡፡

የአገራዊ ራዕይ አልባነት ጉዞ እስከ መቼ?

ዓለም ከሥልጣን ፖለቲካ ወደ ፖለቲካ ተሻግሮ፣ ስለታሪክ ከመነታረክ ወጥቶ ታሪክ ስለመሥራት በሚታገልበት፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ሐሳቦች ወጥቶ እጅግ ወደ ላቀና ውስብስብ ሐሳብ በገባበት፣ ከጓዳ ፖለቲካ ወደ አደባባይ ፖለቲካ፣ ከድንበር ተሻግሮ በዓለም አቀፋዊነት በሚተጋበት እኛ ከከባቢያዊነት ወደ መንደርተኝነት ስንገሰግስ፣ ዓለም ወደ ፊት ቀን ከለሊት ሲተጋ፣ እኛ ወደ ኃላ እያሰብን ሴራ ስንጎነጉን፣ ዓለም በነገ ማዕቀፍ ሲተጋ እኛ በትናንት ማዕቀፍ ለመኖር ስንተጋ፣ ፖለቲካችን እንደ ሕፃን ልጅ በትናንሽ ነገሮች እየረካ፣ ዓለም ከመሬት ፍትጊያ ወደ ስፔስ (ህዋ) ፍትጊያ ሲገባ፣ የእኛ ግን ነገር መብላት ብቻ ቢሆን ለምን ብሎ መጠየቅ ዜጋዊ ግዴታ ሆነና ጥያቄ አነሳሁ፡፡

የኢሕአዴግ የችግሮች ሁሉ ችግር እኔ ብቻ ባይነት

ኢሕአዴግ ከታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ያካሄደውን ‹‹የሁኔታዎች ግምገማ›› ካጠናቀቀ በኋላ፣ በተለይም የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት አምስት ሰዓት የፈጀ ‹‹መግለጫ›› ግንባሩ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ ችግር እንዳለበት ነግሮናል፡፡ ኢሕአዴግ ችግር አለብኝ ሲል ይህ የመጀመርያው ጊዜ አይደለም፡፡