Skip to main content
x

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ኢትዮጵያ የተከተለችውን የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜና የገቢ ስሌት ውድቅ አደረገ

በዚህ ዓመት የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቆ ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ገቢ የተሰላበትን መንገድ ውድቅ የሚያደርጉ ትንታኔዎች ከዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ብቅ ብለዋል፡፡

​​​​​​​አዲስ አበባ ዘግይታም ቢሆን የአየር ብክለትን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምራለች

የአሜሪካ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ባልደረቦች ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኘው የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በአየር በብክለት አማካይነት በኅብረተሰብ ጤና ላይ ስለሚከሰቱ ጠንቆች ብሎም የአየር ብክለት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን መከታተልና መቆጣጠር ስለሚቻልባቸው ሥልቶች ድጋፍ መስጠት የሚችልበትን ግንኙነት መሥርቷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ከጠቅላላ የአገልግሎት ሽያጭ 18.4 ቢሊዮን ብር ማስገባቱን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው እንደገለጸው፣ ከጠቅላላ ገቢው 13.2 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ገልጿል፡፡ የኩባንያው ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደጠቀሱት፣ በግማሽ ዓመቱ ከ15 በላይ አዳዲስ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመጀመሩ ገቢው 18.4 ቢሊዮን ብር ቢደርስም ቀደም ብሎ ካደቀው የገቢ መጠን አኳያ ማሳካት የቻለው 94.5 በመቶውን ነው፡፡

ባንኮችን ያስተሳሰረው የክፍያ ሥርዓት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ አንቀሳቅሷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉንም የግልና የመንግሥት ባንኮች የአክሲዮን ባለቤት በማድረግ የተቋቋመው ኢትስዊች ኩባንያ፣ የሁሉንም ባንኮች የኤቲኤም ማሽኖች በማጣመር የክፍያ ሥርዓትን ለማስፋፋት መንቀሳቀስ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ 

የመንግሥት ቁጥጥር በመዳከሙ በልኬት መሣሪያዎች የሚፈጸም ብዝብዛ ተባብሷል

በግብይት ሥርዓት ውስጥ ሚና ካላቸው አሠራሮች መካከል የልኬት መሣሪያ ወይም ሚዛን ይጠቀሳል፡፡ የልኬት መሣሪያዎች በሻጭና በገዥ መካከል የሚደረገውን  ግብይት የመዳኘት ድርሻ አላቸው፡፡ እነዚህ የልኬት መሣሪያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ  የሚያገለግሉ የጋራ ቋንቋ ለመናገር የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ዳኝነታቸው አወንታዊ የሚሆነው ግን መሣሪያዎቹ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውሉ ነው፡፡

ምርት ገበያ ከፍተኛ የሰሊጥና የቡና ግብይት ማከናወኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2010 ግማሽ በጀት ዓመት 317,607 ቶን የግብርና ምርቶች ያገበያየ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 133,818 ቶን ቡና በማገበያየት ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ በማስመዝገብ ቀዳሚውን ድርሻ መውሰዱ ተገለጸ፡፡ 

የምንዛሪ ለውጡ ምስቅልቅሎሽ

መንግሥት የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አኳያ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰን ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም በርካታ የገበያ ውዥንብር ተፈጥሯል፡፡ እንደ መንግሥት ማብራሪያ፣ የተደረገው ለውጥ እንዲያመጣ ከሚጠበቁበት መሻሻሎች አንደኛው የአገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪ ማድረግ ነው፡፡

ለደሃ አገሮች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ካልተተገበረ የኑሮ ልዩነት እንደሚባባስ ተመድ አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ትንታኔ መሠረት፣ አብዛኞቹ በድህነት ውስጥ የሚገኙ 47 በኢኮኖሚ ኋላ የቀሩ አገሮችን ከኢኮኖሚ ለመደገፍ የበለፀጉ አገሮች ቃል ቢገቡም፣ በዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት መዳከም ሳቢያ ለመስጠት የገቡትን ቃል ከማክበር ሲያፈገፍጉ ይታያሉ፡፡ በዚህ ሳቢያም ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባቸው ድሆቹ አገሮች እ.ኤ.አ. በ2030 መጨረሻ ዕውን እንዲሆኑ የተቀመጡትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ያወጣቸውን ዘላቂ የልማት ግቦች የማሳካት ዕድላቸው የመነመነ ስለመሆኑ አስጠንቅቋል፡፡