Skip to main content
x

ኢትዮጵያ ቡና የፈረንሣዩን አሠልጣኝ ይሁንታ አግኝቷል

ክለቡ የሰርቢያዊ አሠልጣኝ ጉዳይን በፌዴሬሽኑ በኩል ክትትል እያደረግኩ ነው ብሏል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተለይም በክለቦች እንቅስቃሴ፣ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለየት ያለ የደጋፊዎች ኅብር ያለው ስለመሆኑ ይጠቀስለታል፡፡ በደጋፊዎች ብዛት ብቻም ሳይሆን፣ ደጋፊዎቹ በሚለብሷቸው የክለቡ መለያ ቀለማት ያሸበረቁ አልባሳት የሚጎላው ኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎቹን ብዛት፣ ውበትና ኃይል በውጤት ማጀብ ግን ብዙም ሲሆንለት አይታይም፡፡ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ እንኳን ከስድስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

የዋሊያዎቹ የሴካፋ ተሳትፎ ተጠናቀቀ

በኬንያ አስታናጋጅነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) የተሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ከምድብ ማጣሪያው ውጪ ሆኖ ተሳትፎውን አጠናቋል፡፡ ከምድቡ ኡጋንዳና ቡሩንዲ ከሁለተኛው ምድብ ደግሞ አዘጋጇ ኬንያና ዛንዚባር ወደ ግማሽ ፍጻሜው የገቡ አገሮች ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያን የሊግ ደረጃና ቴክኒካዊ ብቃት ያላገናዘበ ቁጭት

የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) ዋንጫ በኬንያ አስተናጋጅነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ደቡብ ሱዳንን አሸንፎ በቡሩንዲ አቻው በሰፊ ውጤት የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) እሑድ ታኅሣሥ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ከኡጋንዳ ጋር ያከናውናል፡፡

ብጥብጥና ሁከት ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› የሆነበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ

መንግሥት የመፍትሔው አካል ሊሆን እንደሚገባ ተጠይቋል በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ የሰው ልጆች በአንድ መድረክ ተገናኝተው በአንድ ቋንቋ ከሚግባቡባቸው መሣሪያዎች እግር ኳስ ተጠቃሽ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ግለሰቦች በፈጠሯቸው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለዓመታት ሰላም ርቋቸው የቆዩ አገሮችና ሕዝቦች በእግር ኳስና እግር ኳስ በፈጠራቸው ከዋክብት አማካይነት አንድ ሆነው የሰላምን ትርጉም እንዲሰብኩ ምክንያት እየሆነም ይገኛል፡፡

ፊፋ ለ22 ኢትዮጵያውያን ለኢንተርናሽናል ዳኝነት ዕውቅና ሰጠ

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ለ22 ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ዳኞችና ረዳቶች የኢንተርናሽናል ዳኝነት ዕውቅና ሰጠ፡፡ በሌላ በኩል በመጪው ክረምት በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደውን የ2018 የዓለም ዋንጫ እንዲዳኙ በዕጩነት ከተመረጡ ስድስት አፍሪካውያን አንዱ በመሆን የተመረጠው ባምላክ ተሰማ፣ በውድድር ዓመቱ በምርጥ ብቃታቸው ከታጩ የመጀመርያው በመሆን መመረጡ ታውቋል፡፡

ለብሔራዊ ቡድኑ ብሔራዊ ክብር ማጣት ተጠያቂው ማነው?

ኬንያ ለምታስተናግደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) ውድድር 27 ተጨዋቾችን ያቀፈው የአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቡድን የሚገባንው ያህል ብሔራዊ ክብር እያገኘ እንዳልሆነ አስተያየት የሚሰጡ የስፖርቱ ቤተሰቦች ቁጥር እየተበራከተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠራ

ለአፋሩ ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ ይሰይማል የዕጩ ተወዳዳሪዎች ገደብ ይነሳል  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ካስተናገዳቸው ሽኩቻዎች በኋላ የተነሱበትን ትኩሳቶች ቀስ በቀስ የማርገብ እንቅስቃሴ የጀመረ ይመስላል፡፡ ነባሩ አመራር ዓርብ ኅዳር 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ወስኗል፡፡

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የትግራይ ሴቶችንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይቅርታ ጠየቁ

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለ ወይኒ አሰፋ ባለፈው ሳምንት በተከናወነው የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የመቐለ ሴቶችን በተመለከተ ለተናገሩትና ተቃውሞ ላስከተለባቸው አነጋገራቸው ይቅርታ መጠየቃቸው ታወቀ፡፡

ያልተቋጨው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባዔ

ምርጫው ከ45 ቀን በኋላ በአፋር ይከናወናል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሥረኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ጥላውን ያጠላው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኀበር (ፊፋ) ማስጠንቀቂያ፣ ለወትሮውም ግራ የተጋባውን ጉባዔተኛ ይብሱኑ ሲያዘበራርቀው ታይቷል፡፡ ጉባዔውን ለመታዘብ የመጡት የፊፋው ተወካይ ራሳቸው ግራ ተጋብተው የአስመራጭ ኮሚቴውን ማንነት ለማወቅ ሲጠይቁ ታይተዋል፡፡