Skip to main content
x

‹‹በታሪካችን በየትኛውም ጊዜ ዓይተነው የማናውቀው ተማሪ ሌላ ተማሪን የሚገድልበት ሁኔታ ተፈጥሯል››

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ፓርቲው አገሪቱን በመምራት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ባስቆጠረበት ጊዜ ውስጥ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየተከሰቱ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከመታወኩም በላይ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ቀውስ ለማስቆም፣ በርካታ የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስትርና የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ምክር ቤቶች የተካሄደው የጋራ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት፡፡ ከአንድ ወር በፊት በአገሪቱ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በፌዴራልና በክልሎች የጋራ ምክር ቤት ዕቅድ ወጥቶና መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ በመግባት በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ ሕገወጦችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል አኳያ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች መሆናቸውን የመንግሥት ሪፖርት አመለከተ

ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማርና ችግር ፈቺ የጥናትና የምርምር ሥራዎችን ከማከናወን ይልቅ፣ የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች እየሆኑ መምጣታቸውን በመንግሥት የተዘጋጀ ሪፖርት አመለከተ፡፡

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት 22 ዕጩዎች ቀረቡ

ለአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት 22 ዕጩዎች ቀረቡ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ 22 ምሁራን ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዚዳንትነት ለማገልግል በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ማመልከቻቸውን አስገብተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋስትናው አንድነቱ ብቻ ነው!

‹‹አንድ ከሆንን ፀንተን እንቆማለን፣ ከተከፋፈልን ግን እንገረሰሳለን›› የሚባለው ታዋቂ አባባል በዓለም ዙሪያ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኘ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ አንድነት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የአንድነትን ትርጉም ለመግለጽ ‹‹ድር ቢያብር አንበሳ ያስር››፣ ‹‹ለአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ››፣ ‹‹ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ››፣ ወዘተ. ዕድሜ ጠገብ አገር በቀል አባባሎች በስፋት ይታወቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ የሚታወቀውም የሚወዳት አገሩን ከባዕዳን ወራሪዎችና ተስፋፊዎች ለመከላከል በከፈለው ወደር የሌለው መስዋዕትነት ነው፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ተቋረጠ

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ዓርብ ታኅሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡

የአክሲዮን ገበያ አለመጀመሩ ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ ተገለጸ

የአክሲዮን ገበያ ቢቋቋም 200 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማመንጨት እንደሚቻል ተጠቆመ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም በመለየት ብሔራዊ የአክሲዮን ገበያ (Stock Market) አለማቋቋሟ፣ በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ የፋይናንስ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በተከፈተው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ባለመቋቋሙ ምክንያት ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት አለመቻሉን፣ በዚህም አገሪቱን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች እያሳጣት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአክሲዮን ገበያ አለመጀመሩ ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ ተገለጸ

የአክሲዮን ገበያ ቢቋቋም 200 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማመንጨት እንደሚቻል ተጠቆመ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም በመለየት ብሔራዊ የአክሲዮን ገበያ (Stock Market) አለማቋቋሟ፣ በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ የፋይናንስ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በተከፈተው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ባለመቋቋሙ ምክንያት ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት አለመቻሉን፣ በዚህም አገሪቱን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች እያሳጣት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አሥራ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ማስተማር ጀመሩ

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብሔር ተኮር ግጭት ከተከሰተ በኋላ የማስተማር ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አቋርጠው ከነበሩ 19 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፣ 16 ያህሉ ማስተማር መጀመራቸው ታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት ከአምቦ፣ ከመቱና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማስተማር ሥራ ተጀምሯል፡፡