Skip to main content
x

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት መልካም ዕድልና ሥጋት

አፍሪካውያን በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ ሊባል በሚችል ደረጃ በርከት ብለው ፊርማቸውን ያኖሩበት ትልቅ ሰነድ እንደሆነ የተገለጸለት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ባለፈው ሳምንት በሩዋንዳ ርዕሰ ከተማ ኪጋሊ ላይ ተፈርሟል፡፡

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት ቁርጥ ያሉ ውሳኔዎች ያልተላለፉበት 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ የፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የአፍሪካ ኅብረት ማሻሻያ፣ ነፃ የንግድ ቀጣና መመሥረት፣ የአፍሪካን የአየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድረግና በአኅጉሪቱ በሚታዩ የፀጥታ ሥጋቶችና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ባለፈው እሑድና ሰኞ በተካሄደው 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ የአርባ ዘጠኝ አገሮች መሪዎች ተገኝተው ነበር፡፡

ግብፃዊያን በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ ነው

ግብፃዊያን ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው፣ ይህንን አመለካከት ወደ አንድ ሐሳብ ለማምጣትና የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ 30ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመካፈል የመጡና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አብዛኛው የግብፅ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ሁሉም ግብፃውያን የጋራ አቋም እንደሚኖራቸው ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የአገሪቱ ሕዝብ ከመንግሥት አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ተቃውሞ ገጠመው

የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አውታር ወደፊት እንደሚያራምድ የታመነበት የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ የአፍሪካ የአየር መንገዶች ዕድገት ፈታኝ እንዳደረገው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የገበያ ክልከላን በማስቀረት የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ በነፃነት ከአገር አገር እንዲበሩ የሚያስችል የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ፣ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ በይፋ አውጇል፡፡ ሰኞ ጥር 21 ቀን በተካሄደው የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መመሥረቱን ያወጁት አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ናቸው፡፡ ፖል ካጋሜ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ለአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዕድገት ትልቅ ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሙስናን በጥበብ መዋጋት

ፒላቶ በሚል የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ዛምቢያዊው አቀንቃኝ ፉምባ ቻማ የዛምቢያውን ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉና የፖለቲካ ፓርቲያቸውን የሚተች ‹‹ኮስዌ ሙምፓቶ›› የተሰኘ ዘፈን የለቀቀው በቅርቡ ነበር፡፡ ‹‹በማሰሮ ውስጥ ያለ አይጥ›› የሚል ትርጓሜ ያለው ዘፈኑ እንደተለቀቀ በመላው አገሪቱ ይደመጥ ጀመር፡፡ በዘፈኑ፣ የአገሪቱ ፖለቲከኞች እንደ አይጥ ምግብ ብቻ ሳይሆን የማይጠቅሙ ነገሮችንም ከሕዝቡ እየሰረቁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ዘፈኑ በሬዲዮና ቴሌቭዥን ከመቅረቡ ባሻገር ፒላቶ በተለያዩ መድረኮች እንዲያቀነቅነው ተጠይቋል፡፡ ነገሩ ያልተዋጠላቸው የአገሪቱ አመራሮች ዘፈኑ በመገናኛ ብዙኃን እንዳይሰራጭና ፒላቶም ኮንሰርቶቹን እንዲሰርዝ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ሊመሠርት ነው

የአፍሪካ አገሮች የገበያ ክልከላን በማስወገድ የጋራ የሆነ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ሊመሠርቱ ነው፡፡ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በይፋ የሚመሠረተው፣ ጥር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ነው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ፣ የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ እንደልባቸው መሥራት ተስኗቸው እንደቆየ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የአፍሪካ አገሮች ለአፍሪካ አየር መንገዶች የበረራ ፈቃድ ለመስጠት ሲያንገራግሩ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አገሮች በአየር ትራንስፖርት ያላቸው ትስስር ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡፡

የአፍሪካ መሪዎች በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ ይመክራሉ

ከጥር 14 እስከ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ፣ ኢትዮጵያም ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስከብርባቸው ውይይቶች እንደሚደረጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት ወደ ሥልጣን ከመጡ ለመጀመርያ ጊዜ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡ በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የአኅጉሪቱን የተለያዩ ችግሮች ከመፍታት አንፃር ጠቃሚ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ገልጸው፣ መሪዎቹም በዋነኝነት በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

የፌዴራል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች  ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ

የፌዴራል መደበኛ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በጥምቀት በዓልና በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ወቅት፣ የፀጥታ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል በመግለጽ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫ፣ የጥምቀት በዓልም ሆነ የኅብረቱ የመሪዎች  ጉባዔ በየዓመቱ ያለምንም ችግር ሲከበር እንደቆየ በማስታወስ፣ ዘንድሮ ግን ሁነቶቹ በሰላም እንዳይከናወኑ ለማድረግ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል፡፡

አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ኅብረት አቀረቡ

በቅርቡ በአፍሪካ ኅብረትና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር አቀረቡ። በባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ዘርፍ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አምባሳደር ወይንሸት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኅብረቱ ኮሚሽን ሙሳ ፋኪ ማሃመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ማቅረባቸውን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።