Skip to main content
x

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ መጥሪያ ሊደርሳቸው ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሩዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና ምክትላቸው አቶ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ምስክሮቹ ያልቀረቡበት ምክንያት ሬጅስትራር ማዘዣ ወጪ ሳያደርግ በመቅረቱ እንደሆነ አስረድቶ አሁን ግን ማዘዣ ወጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መከላከያ ምስክሮቹም ታህሳስ 17፣ 18 እና 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርበው እንዲሰሙ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

‹‹የምስክር ትንሽ ትልቅ የለውም›› አቶ በቀለ ገርባ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የሽብር ተግባር ወንጀልና ከባድ የማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ፣ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡

የአቶ በቀለ ገርባ ዋስትና መታገድ እያነጋገረ ነው

ከአንድ ዓመት በፊት በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ የተከሰሱበት የሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ ተቀይሮ ዋስትና ቢፈቀድላቸውም ሳይለቀቁ በይግባኝ መታገዱ እያነጋገረ ነው፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በሥር ፍርድ ቤት ዋስትና የተከለከሉት ያለበቂ ምክንያት እንደሆነ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ በሥር ፍርድ ቤት የዋስትና መብት የተነፈጋቸው ያለበቂ ምክንያትና የተለወጠላቸው የሕግ ድንጋጌ ግምት ውስጥ ሳይገባ መሆኑን በመጥቀስ፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወሰነ፡፡