Skip to main content
x

ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መማር ማስተማር ሥራቸው የመመለስ ፈተና

ማዕረግ ሞላ (ሙሉ ስሟ ተቀይሯል) ተወልዳ ያደገችው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ካሉ ወረዳዎች አንዱ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ እናቷ ጠላ እየጠመቁና እየሸጡ በሚያገኙት ገቢ እንዳሳደጓት፣ አባቷ በሕይወት ቢኖሩም ከእናቷ ጋር ከመለያየታቸው ባሻገር ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደማያደርጉላት ታስረዳለች፡፡ የእናቷን ውለታ ለመክፈል በማሰብም ለትምህርቷ ትኩረት በመስጠቷና በማጥናቷ ጥሩ ውጤት በማምጣት ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ አግኝታለች፡፡ ዘንድሮ በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የአካውንቲንግ ተማሪ መሆኗንም ትገልጻለች፡፡

የመሠረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን በሚያጓድሉት ላይ ተጠያቂነትን የሚያመጣው ሥልት

በሳምንቱ ከታዩ ክንውኖች ውስጥ መንግሥት በመሠረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥ መስክ ከለጋሾች ጋር ያካሄደው ግምገማ አንዱ ቢሆንም፣ ከዚሁ ጋር የሚገናኘውና የዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው የአጋርነት ማዕቀፍ የተሰኘ ፕሮግራም ኩታ ገጠም ሆኗል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በፀጥታ ችግሮች ሳቢያ መቀነሱ አሳስቦኛል አለ

በዩኒቨርሲቲዎች የተቋረጠው የታሪክ ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተወሰነ ከመስከረም ወር ጀምሮ በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት የሚጠበቅባቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር መቀነሱ እንዳሳሰበው፣ ትምህርት ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።

በመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት መስክ ለውጦችን ያመላከተው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት በርካታ ጉድለቶች እንዳሉ ጠቆመ

በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት በሚመደብ በጀት ሲተገበሩ በቆዩት የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በየጊዜው ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በርካታ ጉድለቶች እንደሚታዩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት አመላከተ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ረገድ አፋርና ሶማሌ ክልሎችና የድሬዳዋ አስተዳደር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ዕጩ ምሩቃን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊወስዱ ነው

ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በአገሪቱ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊወስዱ መሆኑ ታወቀ፡፡ ሰሞኑን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ የሚሆነውን አጠቃላይ ምዘና ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ለሶማሌና ለኦሮሚያ ክልሎች አንደኛ ዓመት ተማሪዎች አዲስ ምደባ አወጣ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 ዓ.ም. የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አምጥተው ከኦሮሚያ ክልል ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲና ከሶማሌ ክልል ወደ ኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ለነበሩ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች አዲስ ምደባ ማውጣቱ ታወቀ፡፡