Skip to main content
x

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብና የእስራት ቅጣት የሚጥል ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በተደራጀና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሕጉን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ በሕገወጥ ደላሎች የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነትና በሌሎች ሥራዎች ተሠማርተው በነበሩ ኢትጵያውያን ላይ በደረሰው ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ምክንያት መንግሥት ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቃዊ አገሮች እንዳይጓዙ ዕግድ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሼክ አላሙዲን እንዲፈቱ መስማማታቸውን ገለጹ

ለጉብኝት ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሐመድ አሊ አላሙዲን እንዲፈቱ ጠይቀው ስምምነት ላይ እንደደረሱ ተናገሩ፡፡

ከስደት ተመላሾችን ለመታደግ

ኤልሳ ተክላይ ተወልዳ ያደገችው ጎንደር ከተማ ሲሆን፣ የምትኖረውም ከቤተሰቦቿ ጋር ነው፡፡ የአሥረኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ብትወስድም ውጤት ስላልመጣላት፣ የትውልድ ቀዬዋን ለቃ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር የሄደችው፡፡ ይሁን እንጂ ኤልሳ ብዙ አልማ የሄደችለት ሕይወት እንደጠበቀችው አልሆነላትም፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ20 ኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ለመሠማራት ፈቃድ የሰጣቸው የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች 20 ብቻ ናቸው አለ፡፡ ይህ የተባለው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋናው አድማሱ፣ የሰው ኃይል ጥናትና ሥምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ኃይሌና የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

ምንም እንኳን ለኤጀንሲነት ምዝገባ 923 ድርጅቶች ማመልከቻ ያስገቡ ቢሆንም፣ መሥፈርቱን አሟልተው ፈቃድ ማግኘት የቻሉት ግን 20 ብቻ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

መንግሥት በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ የጣለውን ዕገዳ አነሳ

መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ለዓመታት ጥሎት የነበረውን ዕገዳ ከማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲነሳ ወሰነ። የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዕገዳው እንዲነሳ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥር 22 ቀን ጀምሮ ዕገዳው እንዲነሳ መወሰኑን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በሱዳንና ሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው በሱዳንና በሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር፣ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሪፖርተር ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለጉዳዩ በጣም ቅርብ የሆኑ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት ፍርደኛ ኢትዮጵያውያኑን ከሱዳንና ከሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች ለማዘዋወር በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው፣ ሕጋዊ ሥልጣን ያለው የአገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ነው፡፡

የሳዑዲ ዓረቢያ ኩባንያዎች ወኪል ከኢትዮጵያ አቻው ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ውድቅ ተደረገ

መንግሥት የዜጎቹን መብት ለማስከበር የውጭ ሥራ ሥምሪትን አስመልክቶ የሁለትዮሽ ስምምነት ካደረገባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች አንዷ ከሆነችው ከሳዑዲ ዓረቢያ ኩባንያዎችንና ቢሮዎችን በመወከል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው የሳዑዲ ልዑካን ቡድን፣ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ያደረገው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ውድቅ መደረጉ ታወቀ፡፡

ሼክ አል አሙዲ ታስረው እየተመረመሩ ነው

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ ታስረው እየተመረመሩ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያን ፀረ ሙስና ዘመቻ የሚመሩት የአገሪቱ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በታዋቂው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው 11 ልዑላንና 38 ታዋቂ ባለሀብቶች መካከል አንዱ የሆኑት ሼክ አል አሙዲ፣ በሙስና ተጠርጥረው እየተመረመሩ ይገኛሉ፡፡

ሼክ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በቁም እስር ላይ ናቸው

​​​​​​​የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀ መንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል አንዱ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ ሼኩ በአሁኑ ጊዜ በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው ታዋቂው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡