Skip to main content
x

ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እስከ ሰኔ መጨረሻ 32 ሺሕ የጋራ ቤቶች ይጠናቀቃሉ አለ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በተለያዩ ችግሮች እየተንጓተተ ቢሆንም፣ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 32 ሺሕ ቤቶች እንደሚጠናቀቁ ተመለከተ፡፡ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) የሚመራ ቡድን ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተለያዩ ሳይቶች ጉብኝት አድርጓል፡፡ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ከሚገነቧቸው 94,070 ቤቶች ውስጥ በመጋቢት 2010 ዓ.ም. 22 ሺሕ ቤቶችን፣ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ደግሞ 50 ሺሕ ቤቶችን የማጠናቀቅ ዕቅድ ነበረው፡፡

ቤቶች ኤጀንሲ ከሁለት ሺሕ በላይ የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶች ለመሸጥ ጨረታ ያወጣል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ በሰባት ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ 2,331 የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶችን ለመሸጥ፣ ሰኞ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጨረታ ሊያወጣ ነው፡፡ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡ ከ175 ሺሕ በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣ ወለል ላይ የሚገኙ 12,500 ቤቶች በ13 ዙር ጨረታዎች ለነጋዴዎች መተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ መጓተቱን የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማግኘት ተመዝግበው በየወሩ እየቆጠቡ የሚገኙ ቢሆንም፣ ግንባታው ግን አዝጋሚ መሆኑ በፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ተገለጸ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በ20/60 እና በ40/80 ቤቶች ፕሮግራም ሳይቶች ላይ ባካሄደው ቅኝት  ግንባታው በተያዘለት ዕቅድ ከመሄድ ይልቅ እየተጓተተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በአሥር ቢሊዮን ብር በጀት የሚካሄደው የጋራ ቤቶች ግንባታ በኮንትራክተሮች አቅም ማነስ እየተስተጓጎለ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት በአሥር ቢሊዮን ብር በጀት ከሚያስገነባቸው 94,070 የጋራ ቤቶች መካከል፣ በሰኔ 2010 ዓ.ም. 50 ሺሕ ቤቶችን ለማጠናቀቅ የያዘው ዕቅድ በኮንትራክተሮች አቅም ማነስ እየተስተጓጎለ ነው፡፡

በአዲስ አበባ የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኅብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት በ13 መሥሪያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ጥናት፣ 211 ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ዝርዝር የመፍትሔ ሐሳቦችን አቀረበ፡፡