Skip to main content
x

ከእናቶች ጤናማነት ወር ባለፈ

ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ሰላም ተመስገን ሦስተኛ ልጃቸውን ሊገላገሉ ቀናት ቀርተዋቸዋል፡፡ ሁለቱንም ልጆቻቸውን የወለዱት በጤና ተቋምና በሠለጠነ ባለሙያ አዋላጅ ታግዘው ነው፡፡ የእርግዝናቸውን ጤንነት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመከታተል ላይ ናቸው፡፡

ባለመፍትሔ ፈጠራዎች እንዲፈጠሩ

አንድ ነገር እንደየተመልካቹ አተያይ፣ አስተሳሰብ፣ ዕድሜና የብስለት ደረጃ የተለያየ ውጤት አልያም ምላሽ ይኖረዋል፡፡ ልክ በብርጭቆ ውስጥ እንዳለው ግማሽ ውኃ ግማሽ ጎዶሎ፣ ግማሽ ሙሉ አገላለጽ ዓይነት ተቃርኖ ያላቸው ነገር ግን ከእውነታው ያልራቁ አገላለጾች ማለት ነው፡፡ እንደየተመልካቹ አተያይ አጋጣሚው መልካም አልያም መጥፎ ይሆናል፡፡

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን በአዲስ አበባ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በባንግላዴሽ ኤምባሲ ተከበረ፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሒሩት ወልደማርያም (ፎቶ) ባሰሙት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ በማድረጓ ለዓለም ተምሳሌት መሆን አስችሏታል ብለዋል፡፡

 ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ለምን እንደሚሰደዱ ጥናት ተጀመረ

ለቤት ሠራተኝነት ወይም ለተለያዩ የሥራ መደቦች ከኢትዮጵያ ክልሎች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች፣ እንዲሁም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮችና ሌሎችም አገሮች የሚሰደዱ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ መሄድ ትተው ለምን ሕገወጥ መንገድ እንደሚመርጡ ለማወቅ ጥናት ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኛ በባልደረባቸው ተገደሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ክልል የቴክኒክ ኃላፊ በሽጉጥ ተገደሉ፡፡ ግድያው የተፈጸመው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነው፡፡

ኃላፊው አቶ ይታያል  ካሳሁን የሚባሉ ሲሆን፣ ግድያውን ፈጽመዋል የተባሉት ተጠርጣሪ ደግሞ የአገልግሎቱ ቴክኒሻን (ሱፐርቫይዘር) የሆኑት አቶ ጌትነት ኃይሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አቶ ጌትነት ከሟች ቢሮ ገብተው ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከአቶ ይታያል ጋር ሲነጋገሩ እንደቆዩና ከቢሮው ፈጥነው በመውጣት እጃቸውን ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

የሊዝ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢገባም እስካሁን ውይይት አልተደረገበትም

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 በድጋሚ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ ከወራት በፊት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢቀርብም፣ ምክር ቤቱ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በመጠመዱ እስካሁን እንዳልመከረበት ምንጮች ገለጹ፡፡

የእሳት ቃጠሎ በሰሜን ማዘጋጃ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና በቀለመወርቅ ትምህርት ቤት በስተጀርባ (ሰሜን ማዘጋጃ) የሚገኘው፣ በተለምዶ ዶሮ ተራ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ሰኞ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የንግድ መደብሮች ወደሙ፡፡

የሕክምናው ተምሳሌት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዳራሽ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለግማሽ ቀን ያህል ለየት ያለ ድባብ ታይቶበታል፡፡ ለየት የሚያደርገውም በመማር ማስተማሩና በሕክምና ዘርፎች የተሠማሩት ምሁራንና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ማስተናገዱ ነው፡፡ በዚህ መልኩ በታየው አዳራሽ ፊት ለፊት መድረክ ላይ የልሂቁ ሐኪም ፕሮፌሰር እደማርያም ፀጋ ፎቶግራፍ ተቀምጧል፡፡

የመሬት ሊዝ ጨረታ ሳይወጣ ስድስት ወራት ተቆጠሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ መሬት በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚያወጣ የደነገገ ቢሆንም፣ ላለፉት ስድስት ወራት አንድም የመሬት ሊዝ ጨረታ አልወጣም፡፡ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ለመጨረሻ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣው፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡