Skip to main content
x

የምንዛሪ ለውጡ ምስቅልቅሎሽ

መንግሥት የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አኳያ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰን ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም በርካታ የገበያ ውዥንብር ተፈጥሯል፡፡ እንደ መንግሥት ማብራሪያ፣ የተደረገው ለውጥ እንዲያመጣ ከሚጠበቁበት መሻሻሎች አንደኛው የአገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪ ማድረግ ነው፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በሰባት ወራት ውስጥ ከ188 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ገቢ አስመዘገበ

ወደ ሥራ ከገባ ዘጠነኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ እ.ኤ.አ. በ2017 (የበጀት ዓመቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር መሠረት) ሰባት ወራት ውስጥ በወጪ ንግድ የባንክ አገልግሎት አማካይነት ከ188 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ፡፡ በ2010 ሰባት ወራት ውስጥ ያገኘው ትርፍም እ.ኤ.አ. በ2016 ሙሉ ዓመት ካገኘው በከፍተኛ ደረጃ ብልጫ እንዳለው ባንኩ  አስታውቋል፡፡ ባንኩ በየዓመቱ የሚያከብረው የወጪ ንግድ ቀን ሰኞ ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲካሄድ እንደተገለጸው፣ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ ማግኘት የቻለው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከቀዳሚው ዓመት ብልጫውን ይዟል፡፡

የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምርታማነትን እየጎዳ ነው

የውጭ ምንዛሪ እጥረት የአምራች ኢንዱስትሪውን እግር ከወርች ይዞ አላላውስ እንዳለ የተለያዩ ፋብሪካዎች ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተፈጠሩ ችግሮች ለከፍተኛ ችግር እንደዳረጓቸው አምራቾች ለፌዴራል መንግሥት አስታውቀዋል፡፡ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ፣ የተለያዩ ፋብሪካዎች ባለቤቶችና ተወካዮች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ምርታማነታቸው እንዳሽቆለቆለና ህልውናቸው አደጋ ውስጥ እንደገባ ገልጸዋል፡፡

ለነዳጅ ታሪፍ ጭማሪ የዘገየው የመንግሥት ምላሽ አንድምታ

የነዳጅ ትርፍ ህዳግ (ታሪፍ) ለዓመታት ባለመስተካከሉና የዘርፉ ቢሮክራሲ ከመቃናት ይልቅ እየተወሳሰበ በመቀጠሉ፣ በርካታ የነዳጅ ማመላለሻ ትራንስፖርት ባለቤቶች እንዲሁም የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ሥራ ማቆምን አማራጭ አድርገው ማሰብ ጀምረዋል፡፡ ነዳጅ ለኢትዮጵያ ዋነኛው ስትራቴጂክ ሸቀጥ ቢሆንም፣ መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመንፈጉ የነዳጅ ዘርፍ ነጋዴዎች ለኪሳራ በመዳረጋቸው ኪሳራውን መሸከም የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አበክረው እያሳወቁ ነው፡፡ በመንግሥት ቸልተኝነት እያዘኑ ከሚገኙ ዋነኛ የነዳጅ ዘርፍ ተዋናዮች መካከል አቶ ፀጋ አሳመረ ይገኙበታል፡፡ የ77 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው አቶ ፀጋ፣ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማመላለሻ ትራንስፖርት፣ በነዳጅ ማደያ ዘርፍ እንዲሁም በነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ ውስጥ ለ56 ዓመታት ጉልህ ሥፍራ ይዘው ቆይተዋል፡፡

የቢራ ፋብሪካዎች በምርቶቻቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ አደረጉ

የቢራ ፋብሪካዎች በጠርሙስና በድራፍት ቢራ ምርቶቻቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ አደረጉ፡፡ ሰኞ ጥር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢጂአይ ኢትዮጵያ የተጀመረው የዋጋ ጭማሪ፣ በተመሳሳይ ሌሎቹም የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ምርቶቻቸውን ማከፋፈል ጀምረዋል፡፡ ሁሉም የቢራ ፋብሪካዎች ያደረጉት የዋጋ ጭማሪ በተከታታይ ቀናት ተግባራዊ የሆነ ሲሆን፣ የዋጋ ጭማሪያቸውም ተመሳሳይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሰሞናዊው የዋጋ ጭማሪ መታዘብ እንደተቻለው የአንድ ሳጥን ቢራ በአዲስ አበባ የማከፋፈያ ዋጋ ከ214 ብር ወደ 251 ብር ከፍ ብሏል፡፡ የአንድ በርሜል የድራፍት የማከፋፈያ ዋጋ ከ600 ብር ወደ 700 ብር ከፍ ብሏል፡፡

ከንፋስ አመጣሽ ታክስና ከልማት ድርጅቶች ሽያጭ የሚገኝ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ሆኖ ቀረበ

የብር ምንዛሪ ተመን እንዲቀንስ በመደረጉ የአገሪቱ ባንኮች ከነበራቸው ተቀማጭ የዶላር ክምችት ካገኙት ድንገተኛ ትርፍ ላይ መንግሥት በንፋስ አመጣሽ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ፣ እንዲሁም ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሽያጭ እንደሚገኝ የታሰበ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት በጀት እንዲሆን ተጠየቀ፡፡ ባለፈው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤተ ያፀደቀው ይህ የተጨማሪ በጀት፣ ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ፓርላማው እንዲያፀድቀው ቀርቧል፡፡

የኢኮኖሚው ጣጣ ሌላ ቀውስ እንዳያመጣ!

ላለፉት ሁለት ዓመታት አገሪቱ ያጋጠማት የፖለቲካ ቀውስ በዜጎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ በበርካቶች ላይም የሥነ ልቦና ችግር  አስከትሏል፡፡ የፖለቲካ ቀውሱ የፈጠራቸው ተጓዳኝ ችግሮች በኢኮኖሚው ላይ በስፋት እየታዩ ነው፡፡ ሁከት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በተደጋጋሚ የጥቃት ሰለባ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንቶች መጠነ ሰፊ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በማኅተም የተደገፈ የውጭ ምንዛሪ ምዝገባ ቁጥር ለአመልካቾች እንዲሰጥ የሚያሳስብ ማስታወቂያ አወጣ

የውጭ ምንዛሪ ጥያቄን በግልጽነት ለማዳረስና ለማስተዳደር በማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ዓመት በፊት ያወጣውና በየጊዜው ሲያሻሽለው የቆየውን መመርያ በቅርቡ ከማማሻሉም በላይ፣ ይህንኑ መመርያ መሠረት ያደረገና የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ የሚያቀርቡ ደንበኞች ላቀረቡት ጥያቄ በማኅተም የተደገፈ ተራ ቁጥርን ጨምሮ ሌሎች መብቶችና ግዴታዎቻቸውን የሚገልጽ ማስታወቂያ በየባንኮች መለጠፍ ጀመረ፡፡

ሃያ ሦስት ሺሕ ቶን ብረት ለመግዛት የወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተሰረዘ

የመከላከያ ፋውንዴሽን 23 ሺሕ ሜትሪክ ቶን አርማታ ብረት ለመግዛት አውጥቶት የነበረውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ለመሰረዝ ተገደደ፡፡ በምትኩ ተቋሙ የአገር ውስጥ ጨረታ እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ስድስት ያህል ዓለም አቀፍ የዓርማታ ብረት አቅራቢዎችን ሲያሳትፍ የነበረው ጨረታ የቴክኒክ ግምገማው ሲደረግ ቢቆይም፣ ተቋሙ በመጨረሻ ብረቱን ለመግዛት የሚያስችለውን የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻሉ ጨረታውን መሰረዙ ተገልጿል፡፡