Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነትና ቅድመ ታሪክ ከቋንቋ አንፃር እንዴት ይታያል?

መጋቢት ወር በሀገረ አሜሪካ ለንባብ ካበቁት አካዴሚያዊ መጻሕፍት ተጠቃሹ ‹‹ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነትና ቅድመ ታሪክ›› የሚል ርዕስ ያለው የዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ መጽሐፍ ነው፡፡ ዶ/ር ግርማ የሥነ ልሳንና የኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ባለሙያ ሲሆኑ፣ የምርምር ትኩረታቸው በአብዛኛው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ታሪክና ሥነ መዋቅር ላይ ነው፡፡

በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጡት ቅርሶች የትኞቹ ናቸው?

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ውስጥ ከሚገኙ ሐውልቶች መካከል በአንድ ጥግ አፄ ኃይለ ሥላሴ ተማሪዎችን ሲያነጋግሩ የሚያሳየው፣ በሌላው ኢትዮጵያዊ የዘር ግንድ እንዳለው የሚነገርለት የአሌክሳንደር ፑሽኪን፣ የአዘቲክስን (ሜክሲኮ) የጥንት ሥልጣኔ የሚያሳየው የኦልማክ ሐውልት ይገኛል፡፡ ወረድ ብሎ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አልባኒያውያንን እንደጨፈጨፈ የሚነገርለት የኮሚኒስቱ ኢንቨር ሆዛ ሐውልት ከአንዱ ግርጌ አለ፡፡

ስለ ዴር ሡልጣን ገዳም አዲሱ የእስራኤል ፕሬዚዳንት የገቡት ቃል ይፈጸም ይሆን?

ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም ጋር ያላት ግንኙነት ከሦስት ሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ እንደሆነ ይወሳል፡፡ ንግሥተ ሳባ/ንግሥተ አዜብ የምትባለው ማክዳ ንጉሥ ሰሎሞንን ከጎበኘችበት ዘመን እንደሚያያዝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚያን ወቅት ነው “ዴር ሡልጣን ” ተብሎ የሚታወቀው ሥፍራ በርስትነት ለኢትዮጵያ የተሰጠው የሚባለው፡፡

‹‹መክተፏ - የሕይወት ታሪክ››

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሥር የሚገኘው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል፣ በሠዓሊ ታምራት ሥልጣን የተዘጋጀ ‹‹መክተፏ - የሕይወት ታሪክ››  የተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ቅዳሜ ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በ9፡00 ሰዓት ይከፍታል፡፡

የወላይትኛ ድምፃዊ ኮይሻ ሴታ (1963-2010)

ድምፃዊው ኮይሻ ሴታ በ1980ዎቹ አጋማሽ የወላይትኛ ባህላዊ ሙዚቃ በማስተዋወቅ ረገድ ተጠቃሽ ነበር፡፡ በ1984 ዓ.ም. ባሳተመው የወላይትኛ አልበሙ ከሚገኙት ዘፈኖቹ “ኤ አዬ ኤሲስ አቦ…ቡሌ ጋሼ ወላ ሎሜ አያ›› ተደናቂነትን እንዳተረፈበት ይወሳል፡፡

ሴት ከዘር ምንጭነት እስከ እውነት አረጋጋጭነት በድራሼ

በዕለተ ሰንበቱ በዓለም ዙሪያ የእናቶች ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ እናቶችን፣ እናትነትን፣ ወላጅነትና እናቶች ለማኅበረሰቡ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚዘከርበት ነው፡፡ በየዓመቱ የሜይ ወር ሁለተኛ እሑድ የሚከበረው የእናቶች ቀን፣ ዘንድሮ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ላይ ውሏል፡፡

ለአፄ ዮሐንስ ሐውልትና ሙዚየም ሊገነባ ነው

አፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሠ ጽዮን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ (1863-1881) በተወለዱበት ዓቢይ ዓዲ ከተማ የመታሰቢያ ሐውልታቸውን ለማቆምና ታሪካቸው የሚዘከርበት ሙዚየም ለመገንባት ታቅዶ ለተግባራዊነቱ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ በመከናወን ላይ ነው፡፡ እስካሁንም በተካሄደው እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ ውሎ አድሯል፡፡

የፕሮፌሰር ዓቢይ ፎርድ ሥርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ይፈጸማል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የጋዜጠኝነትና የኮሙዩኒኬሽን ድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት ዲን፣” የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አማካሪ የነበሩት ፕሮፌሰር ዓቢይ ፎርድ ሥርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ እንደሚፈጸም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የሕዝብ መዝሙር ደራሲና የባህል ባለሙያ አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ (1928-2010)

ከኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ እስከ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በነበሩት አሥራ ሰባት ዓመታት (1967-1983) የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር የነበረውና ብዙኃኑ የዘመረውን፣ ከአብዮት አደባባዮች እስከ ትምህርት ቤቶች፣ ከስፖርት ስታዲየሞች እስከ ኦሊምፒክ አደባባይ (የሞስኮ ኦሊምፒክ የምሩፅ ይፍጠር ወርቃማ ድሎች) የተዜመውን ‹‹ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረሰባዊነት አብቢ ለምልሚ…›› ብሔራዊ መዝሙር ደራሲነታቸው ይታወቃሉ፡፡

የድል ደወል

ፋሺስት ጣሊያን አዲስ አበባን በያዘበት ማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1928 ዓ.ም.) በሕዝቡና በአርበኞች ተጋድሎ የኢትዮጵያ የድልን ቀን ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1933 ዓ.ም.) ተበሰረ፡፡ 77ኛ ዓመቱንም ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተዘከረ፡፡ ዘውዴ ረታ ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት›› በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ታሪካዊቷ ሚያዝያ 27 እንዲህ ጽፈዋል፡፡