የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዚዳንትነት ወሳኝ ቅስቀሳ ከጀመሩበት እ.ኤ.አ 2016 አጋማሽ ጀምሮ ስለሩሲያ ያላቸው ለዘብተኛ አመለካከት፣ በአሜሪካውያኑ ባለሥልጣናት በተለይም በዴሞክራቶቹ የሚተች ነው፡፡

  • ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው ሚሳይል የትኛውም ሥፍራ ይደርሳል ተብሏል

ሰሜን ኮሪያ ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ከ37 እስከ 40 ደቂቃ የተምዘገዘገውንና 930 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዞ በጃፓን ባህር ውስጥ የወደቀውን የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራ ማድረጓ፣ የአካባቢውን አገሮች ብቻ ሳይሆን ኃያላኑንም አስደንብሯል፡፡

ታላቋ ብሪታኒያ እ.ኤ.አ. ከ2000 በፊት ሽብርን አስተናግዳ ብታውቅም፣ ዘንድሮ እየገጠማት ያለውና በተለይ ከእስልምና አክራሪነትና እስልምናን ከመፍራት የሚመነጨው ግን ለዜጎች፣ በተለይም በመዲናዋ ለሚገኙት ሎንዶነርስ ሥጋት፣ ለአገሪቷ ደኅንነት ክፍልም ፈተና ሆኗል፡፡

ዛሬ በነዳጅ ሀብቷ የበለፀገች ብትሆንም እ.ኤ.አ. ከ1939 በፊት የነበራት የሀብት ደረጃ ደሃ ከሚባሉት አገሮች ያሠልፋት ነበር፡፡ በ1700ዎቹ ለንግድ በሚዘዋወሩ ሰዎች በባህረ ሰላጤው ደሴት ላይ ተመሠረተችው ኳታር፣ አሁን ከባህረ ሳላጤው ሀብታም አገሮች በሀብቷ ከቀዳሚዎቹ ትሠለፋለች፡፡ 

Pages