Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ የአገሮች ደረጃ በነበረበት ቆሟል

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በየወሩ የሚያወጣው የኮካኮላ የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎች) ከነበረበት አንድ ደረጃ ቀንሶ 146ኛ ሆኗል፡፡ የውጤትም ሆነ የአሰልጣኝ ቆሌ የራቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ከመደበኛው አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቻ ሳይሆን፣ ነጥብ ሊያስገኝ ከሚችል የወዳጅነት ጨዋታ ከራቀ ወራትን አስቆጥሯል፡፡ ቡድኑ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከሌላቸው ጥቂት የዓለም አገሮችም አንዱ ሆኗል፡፡

ስለ ዴር ሡልጣን ገዳም አዲሱ የእስራኤል ፕሬዚዳንት የገቡት ቃል ይፈጸም ይሆን?

ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም ጋር ያላት ግንኙነት ከሦስት ሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ እንደሆነ ይወሳል፡፡ ንግሥተ ሳባ/ንግሥተ አዜብ የምትባለው ማክዳ ንጉሥ ሰሎሞንን ከጎበኘችበት ዘመን እንደሚያያዝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚያን ወቅት ነው “ዴር ሡልጣን ” ተብሎ የሚታወቀው ሥፍራ በርስትነት ለኢትዮጵያ የተሰጠው የሚባለው፡፡

የድል ደወል

ፋሺስት ጣሊያን አዲስ አበባን በያዘበት ማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1928 ዓ.ም.) በሕዝቡና በአርበኞች ተጋድሎ የኢትዮጵያ የድልን ቀን ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1933 ዓ.ም.) ተበሰረ፡፡ 77ኛ ዓመቱንም ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተዘከረ፡፡ ዘውዴ ረታ ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት›› በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ታሪካዊቷ ሚያዝያ 27 እንዲህ ጽፈዋል፡፡

በአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች

በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች ከእግር ኳስና አትሌቲክስ ቀጥሎ በተለይም በወጣቱ በመዘውተር ይታወቃል፡፡ ስፖርቱ በባህሪው ልዩ ክህሎና ብቃት ይጠይቃል፡፡ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) በፕሮግራሙ ከሚያካትታቸው የኦሊምፒክ ስፖርቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡

ዝክረ ዓድዋ

የዛሬ 122 ዓመት ጀግኖች የኢትዮጵያን መሬትና ሉዓላዊነት ለወራሪው የጣሊያን ጦር አሳልፈው ላለመስጠት ግንባራቸውን ለጥይት ሳይሰስቱ በታሪካዊው የዓድዋ ተራሮች የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ የቀራቸው ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነበር፡፡ ከአምባላጌ ጀምሮ ጠላትን እየደመሰሱ የዓድዋ ተራራማ ሥፍራዎች በደረሱበት ወቅት አስቸጋሪውና ብዙ የሕይወት መስዋዕትነት ነበር ያስከፈላቸው፡፡

በአህጉራዊ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና ወላይታ ድቻ ይጠበቃሉ

በቶታል ካፍ አፍሪካ ሻምፒዮና ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዑጋንዳውን ክለብ ኬሲቪኤን ሲገጥም ወላይታ ድቻ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ የግብፅ ዛማሌክን ይገጥማል፡፡ በዘንድሮው የካፍ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚጫወቱት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በሐዋሳ ስታዲየሞች ያከናውናሉ፡፡

የዓድዋ ድል 122ኛ ዓመት

‹‹እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፉ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል፡፡

የኢትዮጵያና የኢራን ጥበባዊ ትስስር

የምሽቱ መርሐ ግብር የተጀመረው በመሶብ ባንድ ባህላዊ ሙዚቃዎች ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተገኙትን ታዳሚዎች በሙዚቃዎቻቸው ዘና አድርገዋል፡፡ ባንዱ በተለይም ግጥም በጃዝ በሚቀርብባቸው የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች በባህላዊ ሙዚቃ የግጥም ሥራዎችን በማጀብ ይታወቃል፡፡ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በዋሽንትና በከበሮ ውህድ ግጥሞቻቸውን ያስደመጡ ጸሐፍትም በርካታ ናቸው፡፡

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ኢትዮጵያን አደነቀ

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም በዚሁ እያስመዘገበች ያለውን ውጤት አደነቀ፡፡ አገሪቱ ለዋዳ ፀረ አበረታች ቅመሞች ዘመቻና ለሦስትዮሽ ፕሮግራሞች ትክክለኛ ማሳያ መሆኗን የዋዳ ምክትል ዳይሬክተር ሮበርት ኮህለር ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ፣ ኢትዮጵያ በተለይ በአትሌቲክሱ ዓለም ላይ ያላትን የበላይነት ግምት ውስጥ በማስገባት አበረታች ቅመኞች በይበልጥ ይመለከታቸዋል በሚል ለይቶ ካስቀመጣቸው አምስት አገሮች አንዷ አድርጎ ሲመለከታት ቆይቷል፡፡ በዚሁ መነሻነት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ችግሩን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ፣ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት በማቋቋም እንቅስቃሴ ስታደርግ መቆየቷ አይዘነጋም፡፡