Skip to main content
x

የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት ተስማሙ

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት 700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ዝርጋታ ያካሄዳል በፌዴራል መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመሠረተ ልማት ተቋማት፣ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ የሚያከናውኗቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በመናበብ ለመገንባት ረቡዕ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በውጭ ምንዛሪ እጥረት መሥራትም ሆነ ብድር መክፈል አልቻልኩም አለ

በአገሪቱ ካለፉት ዓመታት ጀምሮ የተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት እየተባባሰ በመምጣቱ፣ ለበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ሥራዎች ማከናወን አለመቻሉን፣ መክፈል የሚገባውን የውጭ ብድሮችን ለመክፈል መቸገሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት እንዲሠሩ የሚያደርግ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

የአገሪቱ የመሠረተ ልማት ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂዱትን የዘፈቀደ ግንባታ እንዲያስቆም ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሠረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የመሠረተ ልማት ተቋማቱን አቀናጅቶ የሚመራበትን ደንብ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡

የአይቴል ሞባይል ስልኮች አምራች የ300 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ለማከናወን መነሳቱን አስታወቀ

በዚህ ዓመት 40 ሚሊዮን ዶላር ለማስገባት አቅዷል በኢትዮጵያ የሞባይል ስልኮችን በመገጣጠም ሥራ መስክ አሥረኛ ዓመቱን ባስቆጠረውና ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በተባለው የቻይና ኩባንያ ሥር ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አንዱ የሆነው አይቴል ኩባንያ፣ በዚህ ዓመት የሞባይል ስልኮች የወጪ ንግድ ገቢውን 40 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ፡፡

ከውጭ አገር በሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ማጭበርበር እየተፈጸመ ነው

ወንጀሉን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቁሟል ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች በኢትዮ ቴሌኮም ሳተላይት ኔትወርክ በኩል ማለፍ ሲገባቸው፣ ሕገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎች ያስገቡ ግለሰቦች ዓለም አቀፍ ጥሪዎቹን በመጥለፍ በራሳቸው መስመሮች ለደንበኞች እያቀረቡ እንደሆነ ታወቀ፡፡