Skip to main content
x

የሳምንቱ ገጠመኝ

በመስከረም 1998 ዓ.ም. የመስቀል በዓል ሲከበር በመስቀል አደባባይ ተገኝተን ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የአዲስ አበባ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ኢሕአዴግን በምርጫ ካርድ ያሰናበተበት ጊዜ በመሆኑ፣ በኢሕአዴግና በተቃዋሚዎች ንትርክ የተነሳ አዲስ አበቤዎች አኩርፈን ስለነበር የመስቀል በዓል ሲከበር ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ተቃውሞ አጋጠመ፡፡

የቃል ኪዳን ካርታ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ከሆኑ ነገሮች ዋነኛው የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአደራ ቃል ነው፡፡ መጀመርያ ቃል ነበር እንዲል ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስመልክቶ ያስተላለፉት ቃልኪዳን ነበር፡፡ የቃል ኪዳኑ መልዕክት የንጉሡን ብልኃት፣ ጥበብና የመሪነት ሚናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከሳምንት በፊት በአንዱ ቀን በማለዳ ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚያመራው ሐይገር ባስ ውስጥ ተሳፈርኩ፡፡ የመጨረሻው መቀመጫ ላይ በስተቀኝ በኩል ያለው መስኮት አጠገብ ከመቀመጤ፣ አንዲት ሴት አራስ ሕፃን ታቅፋ አጠገቤ ቁጭ አለች፡፡ ዞር ብዬ ሳያት በጣም ለጋ ወጣት ናት፡፡ ከ20 ዓመት አይበልጣትም፡፡ ተመቻችታ ከተቀመጠች በኋላ፣ ‹‹ተመስገን!›› የሚል የምሥጋና ቃል አሰማች፡፡ አሁንም ዞር ብዬ ሳያት ያቺ ለጋ ወጣት ፊቷ ከመገርጣቱም በላይ ድካም ይታይባታል፡፡ ሕፃኗ እናቷ እቅፍ ውስጥ ሆና ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ናት፡፡ እናቲቱ በእጇ ይዛ የነበረውን የተቋጠረ ኩርቱ ፌስታል እግሮቿ መሀል ካሳረፈች በኋላ አሁንም ‹‹ተመስገን!›› አለች፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ባለፈው ሳምንት በሆቴል አዳራሽ የተዘጋጀ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚታደም አንድ ዘመዴን አድርሼው እየወረደ ሳለ፣ አንድ ረዥም ቀይ ሰው በእጁ ወደ እኔ አቅጣጫ እያመላከተ ይጣራል፡፡ እኔ ደግሞ ዘመዴን ከመኪናው አስወርጄው እየተሰናበትኩት ነው፡፡ ይኼ የማላውቀው ሰው ማን ነው? ወይስ ሌላ ሰው ነው የሚጣራው? ገልመጥ ገልመጥ ብል ከእኔ በቀር ማንም የለም፡፡ ሰውዬው በረዥም ቅልጥሙ እየተሳበ መጥቶ መኪናዬ አጠገብ ቆሞ መሳቅ ይጀምራል፡፡ ይኼ ደግሞ ማን ነው? ግራ እንደተጋባሁ ገብቶት ኖሮ በጎርናና ድምፁ፣ ‹‹ዓምደ ወርቅ ረሳኸኝ እንዴ?›› ሲል በዕውኔ ሳይሆን በህልም ውስጥ ያለሁ መሰለኝ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በጎልማሳነቴ ዘመን የማያቸው በርካታ ነገሮች ከድሮው የወጣትነቴ ዘመን ያን ያህል ፈቅ ባለማለታቸው በጣም ይገርመኛል፡፡ ለምሳሌ ድሮ ተማሪዎች በነበርንበት ጊዜ ‘የተማሪ ተንኮል’ ውጤት የሆኑ በርካታ ድርጊቶች ይፈጸሙ ነበር፡፡ አንደኛው የሆነ ነገር ፈጥሮ ማስወራት ነው፡፡ አንድ ጊዜ የ11ኛ ክፍል የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪያችን ክፍል ውስጥ ፈተና እየሰጡን ሳለ፣ ማን እንደ ጻፈው የማይታወቅ በአራት ማዕዘን ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ ተሠራጨ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ጊዜው እንዲህ ሳይራቀቅ፣ ይቅርታ መላ ቅጡ ሳይጠፋ፣ ወላጆቻችን ኪሳቸው ውስጥ ሃያ ብር ካለ ዓለም አበቃላት ይባል ነበር፡፡ ያኔ ድሮ ያኔ፡፡ በተለይ በበዓል ሰሞን እኔ ነኝ ያለ ሙክት በአሥር ብር ተገዝቶ ተጎትቶ ሲመጣ የሠፈሩ ሰው የመጀመርያ ጥያቄ፣ ‹‹በስንት ብር ተገዛ?›› የሚል ነበር፡፡ በእርግጥ አሁንም ይህ ጥያቄ እንዳለ ነው፡፡ መልሱ ቢለያይም፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ፖለቲካውንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ መዝናኛውንም፣ ምክሩንም፣ ‹‹ቫካንሲውንም›› አጣምሮ የሚያቃምሰኝን ሳምንታዊውን ሪፖርተር ጋዜጣ ሰኞ ከሰዓት በኃላ፣ አራት ኪሎ ፕሬስ ድርጅት ጎን ያለው የሕዝብ መናፈሻ ውስጥ የጀበና ቡናዬን ይዤ ካነበብኩና ከኮመኮምኩ በኋላ፣ በእግሬ በሺሕ ሰማንያ በኩል ወደ ቤቴ ማዝገም ልምዴ ነው፡፡ ታዲያ በአንዱ ቀን ታኅሳስ 09 ቀን 2010 ዓ.ም.

የሳምንቱ ገጠመኝ

ሰውየው ነው አሉ በመጥረቢያው የአገር እንጨት ከምሮ ሲፈልጥ ሳለ አንዱ ጀርጃራ ‘ቆም ብሎ፣ ‹‹ጃል ምን እየሠራህ ነው?›› ይለዋል፡፡ በጥያቄው የተናደደው ሰው ከግንባሩ ላይ ላቡን እየጠረገ፣ ‹‹ትሞታታለህ እንጂ አልነግርህም፤›› አለው፡፡ እኔ እንዲህ ዓይነት ገጥሞኝ ያውቃል፡፡ አንዱ ቤቴ ይመጣና ምን እየሠራሁ እንደሆነ ይጠይቀኛል፡፡ ልብ በሉ እሱ ሲደርስ እኔ ልብሶቼን እየተኮስኩ ነበር፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በቀደም ዕለት በሞባይል ስልኬ የጽሑፍ መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ስልኬ ድምፅ አሰምቶኝ ስከፍተው በባለ አራት አኀዝ ቁጥር አድራሻ የያዘ መልዕክት ነው የመጣው፡፡ ምን ይሆን ብዬ ስከፍተው በአማርኛ ቋንቋ ሲነበብ የሚረዱት በላቲን ፊደሎች የተጻፈ ነው፡፡ መልዕክቱ በአጭሩ የሚለው ‹‹ሲኖትራክ ያሸንፉ! ሞባይል፣ ቲቪ፣….›› በማለት ሦስት ብር በመክፈል መሳተፍ እንደምንችል ያግባባል፡፡ እኔ በበኩሌ ኢትዮ ቴሌኮም የማልፈልገውን ነገር ለምን እንደሚልክብኝ በጣም ነው የምናደደው፡፡ ይህ የግለሰቦችን መብት የሚዳፈር ድርጊት እንደሆነ አድርጌ ነው የምቆጥረው፡፡ መልዕክት መቀበል እንደምፈልግ ጠይቆኝ ካልተስማማሁ በስተቀር ምንም ዓይነት ነገር እንዲልክብኝ አልፈልግም፡፡ ይህንን የምለው ራሴን ወክዬ ነው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ከንጋቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን የሞባይል ስልኬ ተንጫረረ፡፡ አንስቼ ሳየው ቁጥሩን አላውቀውም፡፡ ነገር ግን መልስ መስጠት ነበረብኝ፡፡  ‹‹ሃሎ ማን ልበል?›› አልኩ፡፡ ደስ የሚል የዜማ ቅኝት ያለው የአንዲት ሴት ድምፅ ተሰማኝ፡፡ ‹‹ሰላም ወንድም ያሬድ እኔ ራሔል እባላለሁ፡፡ ከአሜሪካ ለእረፍት ነው የመጣሁት፡፡ ወንድምህ ዮናስ ገንዘብ ስለላከልህ የት ተገናኝተን ልስጥህ?›› አለችኝ፡፡