Skip to main content
x

የቁጠባ ሒሳብን በማንኛውም ሰዓት ማንቀሳቀስ ካልተቻለ ለምን እንቆጥባለን?

በአሁኑ ወቅት ባንኮች ቁጠባ የሚያድፍበት ዘመን መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በርካታ ቅርንጫፎችን መክፈት ልዩ ሒሳቡን ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ማዘጋጀት፣ የባንኮች የዕለት ተዕለት ሥራ ሆኗል፡፡

ስለ እግር ኳሳችን የሚሰማኝን ልናገር

እግር ኳሱን ከ60ዎቹ አጋማሽ እስከ 80ዎቹ መጨረሻ ድረስ ለመከታተል ከቻሉ አንዱ ዕድለኛ ነኝ፡፡ አሁንም መሄጃ ካጣሁና እግር ከጣለኝ ብቅ ማለቴ አለቀረም፡፡ በዚያን ወቅት የነበሩ አመራሮች ከስፖርቱ ጋር የነበራቸው ቁርኝት የላቀ በመሆኑ፣ በተጨዋቾቹ ዘንድ ከበሬታ እንዲያገኙ አስችሏቸው ነበር፡፡

የአገራችን የወቅቱ ችግሮችና መፍትሔዎች

የአገራችን ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰቡና እየሰፉ ቢመጡም፣ በመንግሥት በኩል ግን ለችግሮቹ ትኩረት ባለመስጠት ነገሮች ወደ አሳሳቢ ደረጃ እየደረሱ፣ ሕዝብም  ሥጋት ላይ በመውደቅ ለህልውናው ዋስትና እያጣ ነው፡፡

በምንዛሪ ለውጡ የተመታውን ሕዝብ መታደግ የመንግሥት ግዴታ ነው

መንግሥት የአገሪቱን የወጪ ንግድ ለማበረታታትና ለማደፋፈር በማለት የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ ካደረገ ወዲህ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ የወትሮው ክራሞት ተረብሿል፡፡ የተፈጠረውን አጋጣሚ የተመረኮዙ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከተለመደው የገበያ ዋጋ ያፈነገጠ ሒሳብ ሲጭኑ ከርመዋል፡፡ በየሚዲያው ‹‹ምክንያት አልባ›› የዋጋ ጭማሪ ወዘተ. እየተባለ ሲደሰኮር ሰንብቷል፡፡ ምክንያት ግን ነበረው፡፡ ያውም መንግሥት ያመጣው ምክንያት፡፡

እነሆ ሦስት መድኃኒት ለኢሕአዴግ

አገራችን በአሁኑ ጊዜ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ብዙ ሰዎች ብዙ ብለውበታል፡፡ አንዳንዶች ‹‹አጣብቂኝ ውስጥ ያለች አገር›› ሲሏት፣ ሌሎች ደግሞ ‹‹መስቀለኛ መንገድ ላይ የቆመች አገር›› ይሏታል፡፡ ‹‹ነፋስ የሚያንገላታት መርከብ››፣ ‹‹ገደል አፋፍ ላይ የቆመች›› የሚሉትና ሌሎች አስተያየቶችም ለዚችው ጥንታዊቷ አገር የገባችውን ሥጋት የሚገልጹበት ቋንቋ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ግርማ ምነው በጃገማ ኬሎ ብቻ ተወሰኑ?

ከወራቶች በፊት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባስተላለፈው ዝግጅት፣ ለታዋቂው  የ‹‹በጋው መብረቅ›› ለጄኔራል ጃገማ ኬሎ ሐውልት እንዲቆምላቸው የሚያስተባበር ኮሚቴ መቋቋሙን ሰምቻለሁ፡፡ የኮሚቴው አስተባባሪ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሲሆኑ፣ ጄኔራል ዋስይሁን ገበየሁም አባል መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ አልሞተም!

ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ነኝ የሚለው አዲስ ቴሌቪዥን መስከረም 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በዕለታዊ የዜና ማስታወሻ ፕሮግራሙ በምሥልና በጽሑፍ አስደግፎ ካቀረባቸው ዜናዎች መካከል “የጂማ፣ የባህር ዳርና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህራን የትምህርት ልቀት ማዕከላት እንዲሆኑ ተመረጡ” የሚለው አንዱ ነበር፡፡

የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚያስከብረው አዋጅ በእርግጥ የሕዝቡን ጥቅም ያስከብራልን?

አብዛኛውን ጊዜ ችግሮች የሚገጥሙን እኛ እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር ለማድረግ የሌሎችን ሐሳብም ሆነ ፍላጎት ሳንረዳ፤ ብንረዳም ከቁም ነገር ባለመቁጠር እንደዋዛ ወደ ጎን በመግፋት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ደግሞ ሁልጊዜ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡ የደረሰውን ችግር ለማረም ብንፈልግ ግን የሚከፈለው ዋጋ እጅግ የሚጎዳ ነው፡፡ ለእነዚህ ማሳያ የሚሆኑ ጥቂት አብነቶችን ብቻ እንይ፡፡