Skip to main content
x
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ጉብኝት በርካታ ስምምነቶች እንደሚደረጉበት ይጠበቃል
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ጉብኝት በርካታ ስምምነቶች እንደሚደረጉበት ይጠበቃል
ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው ከ40 በላይ የሚሆኑ አገሮች መሪዎች በሚታደሙበት የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ቻይና ገቡ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎች የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎችን ያቀፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የልዑካን ቡድን፣ በቻይና ቆይታው የብድር መክፈያ ጊዜ ማራዘምን ጨምሮ የተለያዩ ስምምነቶችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የሚድሮክ ሄሊኮፕተር አደጋ ደረሰበት
ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መከስከሱ ታወቀ፡፡
 በጊቤ ፓርክ የጉማሬዎች ሞት መንስዔ እየተጣራ ነው
 በጊቤ ፓርክ የጉማሬዎች ሞት መንስዔ እየተጣራ ነው
ሰሞኑን በደቡባዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ፣ የሞት አደጋ የደረሰባቸው ባብዛኛው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ጉማሬዎች አሟሟትን የሚመረምር የባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው ማቅናቱን፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የወልዲያ - ሃራ ገበያ - መቀሌ የባቡር ፕሮጀክትን ለማስቀጠል ፈታኝ የገንዘብ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ
የወልዲያ - ሃራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ለመፈጸም መቸገሩን፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና ሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ያለፉት ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን፣ ማክሰኞ ሚያዚያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት።
እስከ 200 ሺሕ ብርና ለሰባት ዓመታት የሚያስቀጡ ክልከላዎችን ያካተተ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተጠራ
እስካሁን ሲሠራበት የቆየውን የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ በመሻር በተሻሻሉ ድንጋጌዎች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩት የወንጀልና አስተዳደራዊ መቀጫዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማድረግ ድንጋጌዎቹን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ፣ እስከ ሰባት ዓመታት በሚደርስ እስርና እስከ 200 ሺሕ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ቅጣት የሚጥሉ ክልከላዎችን ያካተተው ረቂቅ አዋጅ ለውይይት ቀረበ፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ትወልደ ኢትዮጵያዊው ለአሜሪካ መንግሥት ተላልፎ እንዲሰጥ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአሜሪካ ሁለት ሰዎችን በመግደልና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተጠርጥሮ፣ በኢትዮጵያ በቁጥጥር ሥር የሚገኘውን በትውልድ ኢትዮጵያዊና በዜግነት አሜሪካዊ የሆነውን ወጣት አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ፡፡
በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ መስክ ለመሰማራት የሚያስችለውን የአዋጭነት ጥናት ለማጠናቀቅ መቃረቡን ዲፒ ወርልድ አስታወቀ
በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ መስክ ለመሰማራት የሚያስችለውን የአዋጭነት ጥናት ለማጠናቀቅ መቃረቡን ዲፒ ወርልድ አስታወቀ
የዱባይ የወደብና ተርሚናል ኦፕሬተር ዲፒ ወርልድ፣ በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ መስክ ለመሰማራት የሚያስችለውን የአዋጭነት ጥናት በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

ዜና መጽሔት
ማስታወቂያ

ዓለም

በሲሪላንካ የ290 ሰዎችን ሕይወት የነጠቀው ጥቃት
በሲሪላንካ የ290 ሰዎችን ሕይወት የነጠቀው ጥቃት
ምዕራባውያኑ የፋሲካን በዓል ያከበሩበት ሚያዝያ 13 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ለሲሪላንካውያን የትንሳዔ ሳይሆን የሐዘን ቀን ነበር፡፡
ተቃውሞ የቀጠለባት ሱዳን
ተቃውሞ የቀጠለባት ሱዳን
በሱዳን ከሦስት ወራት በፊት በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ ከሥልጣናቸው የተወገዱት ኦማር አል በሽርን የተካው ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ (ካውንስል) ለሁለት ዓመት የሽግግር ዘመኑ አገሪቱን እንደሚያስተዳድር ማሳወቁን ተከትሎ የሕዝቡ ተቃውሞ ቀጥሏል፡፡
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሥልጣን እንዲለቁ የተጠራው ሠልፍ
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሥልጣን እንዲለቁ የተጠራው ሠልፍ
ለሦስት አሠርታት ያህል ሱዳንን የመሩት ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጠራ ሠልፍ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ
የቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ
በቱርክ ከተሞችን የሚያስተዳድሩ ከንቲባዎችንና የምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ እሑድ በተካሄደ አካባቢያዊ ምርጫ፣ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኤኬ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች ተሸነፈ፡፡
በቬንዙዌላ ጉዳይ የሚወዛገቡት ሩሲያና አሜሪካ
በቬንዙዌላ ጉዳይ የሚወዛገቡት ሩሲያና አሜሪካ
ከወር በፊት በቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮና ‹‹የሽግግር መንግሥት መሥርቻለሁ›› ባሉት ተቀናቃኛቸው ሁዋን ጋይዶ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ሩሲያና አሜሪካ ጎራ ለይተው እንዲወዛገቡ ሌላ በር ከፍቷል፡፡
ሞዛምቢክ ዚምባቡዌንና ማላዊን የመታው ‹‹ሳይክሎን ኢዳይ››
ሞዛምቢክ ዚምባቡዌንና ማላዊን የመታው ‹‹ሳይክሎን ኢዳይ››
ያለፈው ሳምንት በሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌና ማላዊ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን የፈተነው ከባድ በአውሎ ንፋስና ዝናብ በተያዘው ሳምንት ለዘብ ቢልም፣ በአውሎ ንፋሱ የተጎዱ ሥፍራዎችን ለመድረስ የሚደረገው ጥረት ግን ፈተና ውስጥ ነው፡፡
ማስታወቂያ
የተመረጡ

ምን እየሰሩ ነው?

ግማሽ ምዕት ዓመትን የተሻገረው የካቶሊክ ማኅበራዊ ተራድዖ
ግማሽ ምዕት ዓመትን የተሻገረው የካቶሊክ ማኅበራዊ ተራድዖ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ የሰዎችን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የማኅበራዊና ልማት አገልግሎቶችን ለዘመናት ስታበረክት የነበረ ሲሆን ይበልጥ በተቀናጀ መልኩ ይህንን አገልግሎት ለማበርከት ይረዳ ዘንድ የማኅበራዊ ልማት ኮሚሽን በ1957 ዓ.ም
‹‹አብዛኛው ተረጂ በድርቅ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው ነው››  መሸሻ ሸዋረጋ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊ
‹‹አብዛኛው ተረጂ በድርቅ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው ነው››  መሸሻ ሸዋረጋ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በኢትዮጵያ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡
የበለጠ ጌራ ጫካ ቡናን የማልማት ፋይዳ
የበለጠ ጌራ ጫካ ቡናን የማልማት ፋይዳ
የጫካ ቡና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅዕኖ መሸከም የሚችልና በውጭውም ዓለም ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው ነው፡፡ ሆኖም በኢትዮጵያ ቡና በብዛት የሚገኝባቸው ጫካዎች በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ተጋርጦባቸዋል፡፡
‹‹የመም ውድድሮች በመጥፋታቸው ታዳጊዎች ወደ ማራቶን ለመግባት እየተገደዱ ነው›› አቶ ሀጂ አዴሎ፣ የረዥም ርቀት አሠልጣኝ
‹‹የመም ውድድሮች በመጥፋታቸው ታዳጊዎች ወደ ማራቶን ለመግባት እየተገደዱ ነው›› አቶ ሀጂ አዴሎ፣ የረዥም ርቀት አሠልጣኝ
የቀድሞው የረዥም ርቀት አትሌት በአርሲ ክፍለ አገር ጭላሎ አውራጃ ጢዮ ወረዳ ደንካ ካበረቻ ቀበሌ ውስጥ ነው የተወለደው፡፡ ስመ ጥር የሆኑ አትሌቶች መፍለቂያ የሆነችው አርሲ ሩጫን ባህል ማድረጓ የቀድሞውን አትሌት የአሁኑ አሠልጣኝ አድርጋዋለች፡፡
ወባን ከመከላከል እስከ ተቀናጀ ጤና
ወባን ከመከላከል እስከ ተቀናጀ ጤና
በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢ በ1990 ዓ.ም. ወባ የሰውን ሕይወት እየቀጠፈ ነበር፡፡ ችግሩ በ1990 ዓ.ም. ላይ ጎልቶ ይውጣ እንጂ፣ ከ1980 አጋማሽ ጀምሮ መባባሱ አልቀረም፡፡ የበረሃ በሽታ ማለትም ቆላ አካባቢ የሚከሰተው ወባ በደጋማ አካባቢዎችም መታየት ጀመረ፡፡ በሰሜኑ በተለይም ጎጃም የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ የሚታወቀው ወባ ተስፋፋ፡፡
በክር እና በመርፌ የተሠሩ ሥዕሎችን በዐውደ ርዕይ የማሳየት እክል
በክር እና በመርፌ የተሠሩ ሥዕሎችን በዐውደ ርዕይ የማሳየት እክል
ወይዘሮ ሳባ ፀሐዬ የሠዓሊ ንጉሤ ታፈሰ ባለቤት ናቸው፡፡ ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ወደ 18 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ወ/ሮ ሳባ፣ ባለቤታቸው በሕይወት በነበሩበት ዘመን የሠሯቸውን ልዩ ልዩ ሥዕሎች በኤግዚቢሽን መልክ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡