Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጤና ኮሌጁ የተበረከተለት 10 የአልትራ ሳውንድ ማሽኖች

የጤና ኮሌጁ የተበረከተለት 10 የአልትራ ሳውንድ ማሽኖች

ቀን:

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የጤና ኮሌጅ፣ 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ አሥር የአልትራ ሳውንድ ማሽኖችን ከጀርመኑ የሲመንስ ሄልዝ ኬር ድርጅት ተበረከተለት፡፡ በጤና ሚኒስቴር አማካይነት የተገኙትን ማሽኖች የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ከጀርመን አምባሳደር ሚስተር ስቲፈን ኦር ከተረከቡ በኋላ ባሰሙት ቃል፣ ድጋፉ የጤና አገልግሎቶችን በብቃት ከመስጠት አኳያ በተለይም የእናቶችን ጤና ከማሻሻልና ሞት ከመቀነስ አንጻር የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የአልትራሳውንድ ማሽኖቹ በኮሌጁ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመመርመር ከማገዙም በላይ ኮሌጁ የሚሰጠውን የሕክምና  አገልግሎት ጥራት ከፍ እንደሚያደርገው የኮሌጁ ፕሮቮስት ወንድማገኝ ገዛኸኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ፎቶው የርክክቡን  ገጽታ ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...