Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፍሪካ ዋንጫ መሥራቾችን ያገናኘው ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ

የአፍሪካ ዋንጫ መሥራቾችን ያገናኘው ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ

ቀን:

በሚቀጥለው ዓመት በአይቮሪኮስት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያውን ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር ያከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ)፣ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን (ፈርâኖቹ) ጋር ያከናውናል፡፡ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ 2 ለ 1 የተረታው የዋሊያዎቹ ስብስብ፣ ሁለተኛውን የምድብ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም ያደርጋል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫን ለሰባት ጊዜ ማንሳት የቻለው የፈርâኖቹ ስብስብ ከዋሊያዎቹ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከፍተኛ ግምት ተስጥቶታል፡፡ በካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ለፍጻሜ መድረስ ችለው የነበሩት ፈርâኖቹ፣ ከወዲህ የማሸነፍ ግምት እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያውን የምድብ ጨዋታ ጊኒን የገጠመ ሲሆን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል፡፡

በምድብ አራት ላይ ከግብፅ፣ ማላዊና ጊኒ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2 ለ 1 በተረታበት የምድብ አንድ ጨዋታ፣ ማሻሻል ባልቻላቸው ስህተቶች ምክንያት በሽንፈት ጀምሯል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከወራት በፊት በተጠናቀቀው የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በመክፈቻው ቀን ኬፕ ቨርዴን የገጠመው የዋሊያዎቹ ስብስብ፣ በተከላካዩ ያሬድ ባዬ በተሠራ ስህተት ገና በአሥረኛው ደቂቃ ለመመራት ችሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር ባደረገችው የምድብ አንድ የመጀመሪያ ጨዋታም ተመሳሳይ ስህተት ገና በአሥረኛው ደቂቃ በተከላካዩ ያሬድ ባዬ በተሠራ ስህተት የቅጣት ምት ሊሰጥበት ችሏል፡፡ ገና በጠዋቱ በተሠራ ስህተት ጨዋታውን የቀጠለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ሁለተኛ ስህተት ለመሥራት 24 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

የዋሊያዎቹ ተከላካይ ምኞት ደበበ በ34ኛው ደቂቃ በተቃራኒ ተጨዋች ላይ በሠራው ጥፋት ማሊ ከዕረፍት በፊት 2 ለ 0 ልትመራበት የምትችልበትን ዕድል ፈጥሮላታል፡፡

ከጨዋታ ጨዋታ ስህተቶችን ማረም የተሳነው ብሔራዊ ቡድኑ በ68ኛው ደቂቃ ላይ በተገኘች ብቸኛ የአቡበከር ናስር የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 2 ለ 1 ተረትቶ በምድቡ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

በካሜሮኑ አፍሪካ ዋንጫ ላይ ከስምንት ዓመት በኋላ መሳተፍ ችለው የነበሩት ዋሊያዎቹ፣ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ተጠግተው የግብ ዕድል መፍጠር ሲቸገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይኼን ችግር በአንፃሩም በሆን ከማሊ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ወደ ግብ ክልል እየተቃረቡ የግብ ዕድሎችን ሲሞክሩ ቢስተዋልም፣ አሁንም የመሀል ክፍሉ የሳሳ እንደነበር ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ሐሙስ በሚያደርጉት ጨዋታ መጀመሪያ የተስተዋለውን ችግር የሚሞላ አሠላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

እ.ኤ.አ 1957 ከሱዳን፣ ግብፅና ደቡብ አፍሪካ ጋር በመሆን የአፍሪካ ዋንጫ የመሠረተችው ኢትዮጵያ በአይቮሪኮስት 2023 አፍሪካ ዋንጫ ከመሥራችዋ ግብፅ ጋር በምድብ አራት መመደቧ በበርካቶች ዘንድ ጉጉትን ፈጥሯል፡፡ ለዚህም ሁለቱ አገሮችን በዓባይ ግድብ ያላቸው የፖለቲካ ሒደት የአንበሳውን ድርሻ ቢወስድም፣ ሁለቱ አገሮችም በተገናኙበት ጨዋታ ግብፅ ሰፊውን የበላይነት መውሰዷ ነው፡፡

በተለይ ኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ሁለተኛ ሙሌት ይፋ አድርጋ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚችሉ የመጀመሪያዎቹ ተርባይኖች ግንባታ ማጠናቀቋን ተከትሎ፣ ሁለቱ አገሮች ያላቸው የፖለቲካ አቋም በሚያንፀባርቁበት ማግሥት መሆኑ ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል፡፡

ኢትዮጵያና ግብፅ 16 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን፣ ግብፅ 11 ጊዜ ስትረታ ኢትዮጵያ በ1954 እና 1981 ብቻ ማሸነፍ ችላለች፡፡ ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ፣ በሦስት ጨዋታዎች ላይ ግብፅ የጎል ናዳ አውርዳለች፡፡

ሁለቱ አገሮች የአፍሪካ ዋንጫ የመሠረቱ ቀዳሚ አገሮች ቀዳሚ መሆን ቢችሉም በእግር ኳስ ደረጃቸው አራምባ እና ቆቦ መሆናቸው ዕሙን ነው፡፡

በአፍሪካ የእግር ኳስ ደረጃቸው እየተሻሻለ ከመጡ አገሮች አንዱ የሆነችው ግብፅ የሊቨርፑሉን መሐመድ ሳላህን የመሳሰሉ ድንቅ ተጨዋቾች መፍራት መቻሏ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውም ከፍተኛ ግምት እንዲሰጣት አድርጓታል፡፡

በምድቡ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ የሊቨርፑሉ አጥቂ መሐመድ ሳላህ እንደማይሰለፍ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁንም ቢሆን የማሸነፍ ግምቱ ለፈርâኖቹ ተስጥቷል፡፡

ከመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ በኋላ በማላዊ ልምምዱን የቀጠለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ጨዋታውን በገለልተኛ ስታዲየም ማድረጉ ከተመልካች ማግኘት የሚችለውን ድጋፍ ማሳጣቱ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚጎዳ ይታመናል፡፡

ኢትዮጵያ የማላዊን ስታዲየም ፈቃድ ከማግኘቷ አስቀድሞ፣ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ሙሉ ወጪውን ችሎ ጨዋታውን በካይሮ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቆ ነበር፡፡ ሆኖም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለክብር ሲል ጥያቄውን አለመቀበሉን አስረድቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...