አውቆ የተኛውን፤
ቀና ጠርጣሪውን፤
ታጋሹን ናቂውን፤
ውለታ ናፋቂውን፤
ሲያርሙ መንፏቀቅ…
ተመልሶ ጭቃ
የሳሙና ኑሮ እያጸዱ ማለቅ!
ሰሞኑን የኅትመት ብርሃን ያየው የግጥም መድበል ‹‹የሳሙና ኑሮ›› ሲሆን ገጣሚው ሙሉጌታ ስመወርቅ ይባላል፡፡ በዚህ ጽሑፍ መንደርደርያ ላይ የሠፈረው ግጥሙ የመድበሉ መጠርያ የተገኘበት ነው፡፡ የግጥም መድበሉ የመጀመርያ ዕትም ከዐሥር ዓመት በፊት ኒው ዮርክ መታተሙ ታውቋል፡፡
ገጣሚው ከመድበሉ የመጨረሻ ገጽ በፊት ‹መርዝ አይገድልም›› በሚል ርዕስ በዝርው እንዲህ ከትቦታል፡፡
‹‹በትንሽ በትንሹ ከለመዱት መርዝ አይገድልም›› ይባላል፡፡ በምሳሌ የሚማረው አሳቢው መንግሥታችንም እሱም በዝቶ እንዳይጨርሰን ፈርቶ፤ ደስታን በጠብታ፤ በምሳሌ፣ በደጋፊዎቹ ሕይወት በኩል ያሳየናል፤ በጥጋብ ስድባቸው ያቀምሰናል፡፡
የመጽሐፉ የሽፋን ዋጋ 120 ብር ነው፡፡