Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበጀርመን የደመቁት ፃልቄዎች

በጀርመን የደመቁት ፃልቄዎች

ቀን:

በባህላዊ ሙዚቃ መስክ ኢትዮጵያን ከ1950ዎቹ አጋማሸ ወዲህ በባህር ማዶ በማስተዋወቅ የተሳካላቸው የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ከያንያን እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

‹‹እኛም አለን ሙዚቃ መንፈስ የሚያነቃ…›› እያሉ በነ ቻርልስ ሰተን፣ ተስፋዬ ለማ አማካይነት ያቀነቅኑ የነበሩ፣ የየነገዱን ባህላዊ ጨዋታ ሲያንፀባርቁ የነበሩት ጥበባውያን በታሪክ ሲወሱ ይታያል፡፡

በ1970ዎቹ አጋማሽ ‹‹ሕዝብ ለሕዝብ ኢትዮጵያ›› በሚባለው ስብስብም የኢትዮጵያን ባህል በተለያዩ አገሮች በመዘዋወር ሲያስተዋውቅ መክረሙም የኪነቱ ታሪክ አንዱ ገጽ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ አገሮች በሚዘጋጁ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች የተሳተፉ አገራዊ ከያንያን በየወቅቱ መታየታቸው አልቀረም፡፡

ባለፈው ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጠናቀቀውና ለሦስት ቀናት በተከናወነው የጀርመኑ የሞርስ ሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ የጋሞ ፃልቄዎች ማኅበር ባህላዊ ሙዚቃ ተጫዋቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዕድሜያቸው ከ50ዎቹ እስከ 70ዎቹ የሚደርሱ ሴቶችና ወንዶች ትርዒቱን ለማቅረብ ወደ ጀርመን የዘለቁት የፈንድቃ ባህል ማዕከል መሥራች የሆነው ከያኒ መላኩ በላይ ባመቻቸላቸው ዕድል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዱዞልዶርፍ ክፍለ ግዛት በራይን ወንዝ ዳርቻ በምትገኘው ሞርስ ከተማ አደባባይ ላይ ሙዚቃ ትርዒት ኢትዮጵያውያኑ ሥራቸውን ያቀረቡት ግንቦት 27 ቀን መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በታዋቂው ከያኒ መላኩ እየተመሩ የተለያዩ ዜማዎችን ከባህላዊ ጭፈራ ጋር አዋድደው ባቀረቡት ሥራቸው የብዙኃን ታዳሚዎች ቀልብ መሳባቸው ጭምር፡፡

የፈንድቃ ባህል ማዕከል በየዓመቱ በጥምቀት በዓል አጋጣሚ በሚያዘጋጀው ‹‹ፍለጋ›› በተሰኘው የአደባባይ ፌስቲቫል የጋሞ ፃልቄ ሙዚቀኞች በመሳተፍ ይታወቃሉ፡፡

ድምፃውያኑ በሙያቸው ተሰጥዖ ያላቸው ሸማኔዎች፣ እንጨት በመሰብሰብና በመሸከም በትጋት የሚሠሩ ሲሆኑ፣ በተጓዳኝም የባህላቸው እምብርት የሆነውን ሙዚቃቸውንም ሲጫወቱ ያስደንቃሉ፣ ያስደምማሉ ይሏቸዋል፡፡ በሁለገብና በማይታክቱት ሥራቸውም የሰው ልጅ የጥንካሬና የደስታ ምልክት ናቸውም እያሉ ጸሐፍት ያደንቋቸዋል፡፡

ይህ ዓለም አቀፍ ዝግጅት በሞርስ ፌስቲቫልና በፈንድቃ የባህል ማዕከል አስተባባሪነት የተደራጀ መሆኑን፣ ይህም ትብብር እንዲሳካ ያደረጉት የኢትዮጵያ ባህል አፍቃሪ ቲም ኢስፎርትና ሴባስቲያን እንዲሁም ኦሊቨር መሆናቸው ፈንድቃ አውስቷል፡፡

ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሉ በሞርስ ከተማ በቡርክሃርድ ሄነን አማካይነት የተመሠረተው በ1963 ዓ.ም. ሲሆን ከተለያዩ አኅጉሮች የመጡ የሙዚቃ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡

በመጀመርያዎቹ ዓመታት ፌስቲቫሉ የተካሄደው በቅጥር ግቢው አስፋልት ውስጥ ሲሆን፣ አምስተኛው ዓመት ላይ ታዳሚዎች በመጨመራቸው በአቅራቢያው ወደሚገኝ መናፈሻ ተዛውሯል። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ወደ አደባባይ በመዝለቅ ታዋቂ ፌስቲቫል ሊሆን እንደቻለ ተመልክቷል፡፡

በተለይ በ1977 ዓ.ም. በተዘጋጀው የአፍሪካ የዳንስ ምሽት ላይ እንደ ሳሊፍ ኬይታ፣ ሞሪ ካንቴ፣ ቼብ ማሚና ዩሱ ንዶር ያሉ ታዋቂ አርቲስቶች የመድረኩ ፈርጥ እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...