Wednesday, February 28, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኦሮሚያ ባንክ በ20 ቢሊዮን ብር ወጪ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣበትን ሕንፃ ነገ ያስመርቃል

ኦሮሚያ ባንክ በገላን ከተማ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ለማስገንባት ያቀደውን ሁለገብ ኮንፕሌክስ የልህቀት ማዕከል ግንባታ ለመጀመር የመጨረሻ የዲዛይን መረጣ ላይ መሆኑንና በአዳማ ከተማ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያወጣበትን ሕንፃ ነገ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡

ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በገላን ከተማ የሚያስገነባው (ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ) ግንባታ ከገላን ከተማ ባገኘው 15 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ነው፡፡

ለልህቀት ማዕከል የሚሆነውን ዲዛይኖች ቀደም ብሎ የመረጠ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የመጨረሻዎቹን በማወዳደር አሸናፊውን ይለያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የባንኩ የማርኬቲንግና ፓርትነርሺፕ ምክትል ፒፍ ኦፊሰር አቶ በላይ ባይሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ይህ በገላን የሚገነባው ማዕከል የባንክ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የማደሪያ ሕንፃዎችን ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሌሎች ሕንፃዎችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡

የመሰብሰብያ አዳራሾች፣ የገበያ ማዕከሎች የነዳጅ ማደያ፣ የመዋኛ ገንዳዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎችና ለተለያዩ ቢዝነሶችና አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡

ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. አዳማ የሚያስመርቀው በ49 ሚሊዮን ብር የገዛውን ሕንፃ 51 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ በማውጣት አሻሽሎ የገነባው ሲሆን፣ ባንኩ ለራሱ አገልግሎት የሚጠቀምበት ይሆናል ተብሏል፡፡

ባንኩ ከእነዚህ ግንባታዎች ሌላ 33 ወለል ያለውን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ አዲስ አበባ ጐማ ቁጠባ በመባል በሚታወቀው ቦታ ላይ እየገነባ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ባንኩ ይህን ሕንፃ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚፈጅበት አቶ በላይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዋና መሥሪያ ቤትነት የሚጠቀምበትን ሕንፃ ደግሞ ከዓመታት በፊት በ210 ሚሊዮን ብር መግዛቱ ይታወሳል፡፡ በባንኩ ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በተመረጡ የአገሪቷ ከተሞች የራሱን ሕንፃዎች እንደሚገነባ የተገለጸ ሲሆን በተለይ በቅርቡ በጅማ፣ ሻሸመኔና መሰል ከተሞች ላይ የራሱን ሕንፃ ለመገንባት በማቀድ በመንቀሳቀስ ላይ ነው ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች