Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተፈናቃዮች የሚጠቀሙበት የ145 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ተፈናቃዮች የሚጠቀሙበት የ145 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ቀን:

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት የ145 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን ኤስኦኤስ የሕፃናት መንደር አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፕሮጀክቱም መቀመጫው በጀርመን የሆነው የኤስኦኤስ ችልድረን ቪሌጅ ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ ዕውን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱን ዕውን ለማድረግ 225 ሚሊዮን ብር መበጀቱን፣ ከዚህ ውስጥ 145 ሚሊዮን ብሩ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚውል የኤስኦኤስ ችልድረን ቪሌጅ የሰብዓዊ ድጋፎች ሥራ አስተባባሪ አቶ ቢኒያም አስፋው አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እንደ አቶ ቢኒያም ገለጻ፣ ድጋፉ ተግባራዊ የሚደረገው በሰሜን ወሎና ደቡብ ወሎ አካባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት ነው፡፡

አርሶ አደሮች የቅድሚያ ቅድሚያ የተሰጣቸው ዋነኛ ምክንያት ወቅቱ የእርሻ ወቅት በመሆኑ ነው ያሉት አቶ ቢኒያም፣ ለእነዚህም አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ለእርሻ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶችን በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከተደረገው ድጋፍ ቀሪው ገንዘብ በአፋርና በትግራይ ክልል የሚውል ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ በጀቶችን በመጠየቅ በሁለቱ ክልሎች ተደራሽ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱም በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው የጤናና የትምህርት ተቋማትን መልሶ ከማቋቋም ባለፈ ለተጎዱ ወገኖች ምግብ ነክ የሆኑ ግብዓቶች ተደራሽ ማድረግ እንደሆነ አክለዋል፡፡

በአማራ ክልል ለ231 ሺሕ ሰዎች ድጋፉን ለመስጠት መታቀዱን ጠቅሰው፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ከወላጆቻቸው የተለያዩ ሕፃናትን የማገናኘት ሥራም የሚሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ወላጆቻቸውንም ያጡ ሕፃናትን በቋሚነት ለመርዳት ተቋሙ የሚሠራ መሆኑን፣ ለዚህም መነሻ የሆነ በጀት ከተለያዩ ድርጅቶች በመጠየቅ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት፣ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜ ቀድሞ በመድረስ ተቋሙ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

‹‹በጦርነቱ ምክንያት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ደርሷል፤›› የሚሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለተጎዱ ወገኖች የሕግም ሆነ የሞራል ምክር እንደተሰጣቸው አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ3,800 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዳሉና እነዚህ ድርጅቶች በድርቅ፣ በጦርነትና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጋለጡ ወገኖች ፈጥነው በመድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደቻሉ አስታውሰዋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት ተቋሙ ባደረገው ጥሪ መሠረት የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና የምግብም ሆነ የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ መደረጉን በቀጣይም ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የጤና፣ የትምህርት ተቋማቶችን መልሶ ለመገንባት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፣ በተለይ በአፋርና በአማራ በተከሰተው ጉዳት 440 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከዚሁ ጎን ለጎን ከሠራተኞች ደመወዝ በየወሩ በማስቆረጥ 17 ሚሊዮን ብር በካሽ መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የግጭት አፈታት ሁኔታን በማጥናት ዘላቂ የሆነ የአፈታት የአፈታት ሥርዓት ለመዘርጋት እየሠሩ እንደሆነ ይሄንንም አጠናክሮ ለመቀጠል ከኤስኦኤስ ችልድረን ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኤስኦኤስ ችልድረን ቪሌጅ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ137 አገሮች ላይ መቀመጫውን ያደረገ ሲሆን፣ በአፍሪካ ደግሞ 48 አገሮች ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...