Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊውትወታው ያልተቋረጠው የአካል ጉዳተኞችን ያማከለ ሕንፃ ግንባታ

ውትወታው ያልተቋረጠው የአካል ጉዳተኞችን ያማከለ ሕንፃ ግንባታ

ቀን:

መንግሥት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ አሠራር እየሠራ ነው ቢባልም መሬት ወርዶ የተሠሩ ሥራዎች እምብዛም ናቸው የሚሉት ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ በተለይም አካል ጉዳተኞችን ያማከለ ሕንፃ ከመገንባት አኳያ ችግሮቹ እንደሚጎሉ  በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡ ይኼም ቁጥራቸው በርካታ ለሆኑ አካል ጉዳተኞች ፈታኝ ከመሆንም አልፎ በሚሠሩበት ተቋም የጤና መድን አለማግኘታቸውን ጥያቄ ሆኖባቸዋል፡፡ ጥያቄ ከሆነባቸው መካከልም አቶ አያሌው ብርሃኑ ይገኙበታል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሰሞኑን የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን አቅም ለማጎልበት ባዘጋጀው የሥልጠና መርሐ ግብር ላይ ከተሳተፉት አንዱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሠራተኛ የሆኑት አቶ አያሌው ብርሃኑ ናቸው፡፡

እሳቸው በተቋሙ መሥራት ከጀመሩ ከአሥር ዓመት በላይ ማስቆጠራቸውን በአንድ አጋጣሚ ግን አካል ጉዳተኛ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በተለይም ተቋሙ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥራ መጨናነቅ በመኖሩ አብዛኛዎቹን ሠራተኞች ወከባ ውስጥ ይገባሉ የሚሉት አቶ አያሌው በክረምት ወቅት ሥራ በመብዛቱ የተነሳ እዚያ እዚህ በሚሯሯጡበት ጊዜ ሕንፃው አዳልጧቸው ሲወድቁ በወገባቸው ላይ ስብራት እንደገጠማቸውና አካል ጉዳተኛ ሊሆኑ እንደቻሉ አስታውሰዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሕንፃ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ባለመሆኑ የተነሳ በፈለጉት መንገድ እየተጓጓዙ ሥራዎቻቸውን እንዳይሠሩ እንዳረጋቸው የገለጹት አቶ አያሌው፣ ለወደፊቱ መንግሥት ይኼንን ታሳቢ ያደረጉ ሕንፃዎች መገንባት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በተቋሙ የጤና መድን ዋስትና  ባለመኖሩ ጉዳት በደረሰባቸው ወቅት ላልተፈለገው ወጪ መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የገቢዎች ሥራ ከፍተኛ የሆነ ጫና ያለበትና ግር ግር የበዛበት ሥራ በመሆኑ አሁን ላይ እንደፈለጉት ተሯሩጠው ለመሥራት መቸገራቸውን አስታውሰዋል፡፡

በተለይም የቤተሰብ ኃላፊነት ያለበት ሰው እንደዚህ ዓይነት ችግር በሚገጥመው ወቅት የተለያዩ አማራጮችን መንግሥት ማቅረብ ይኖርበታል የሚሉት አቶ አያሌው፣ አሁን ላይ የከፋ ችግር ውስጥ መግባታቸውንና የሰው እጅ በማየት ሕክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ይልቁንም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ሠራተኞች ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው፣ ይኼም ለከተማ አስተዳደሩ ብቻ የሚተው ሥራ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ የጤና ኢንሹራንስ በሁሉም የመንግሥት ተቋማት ማድረግ ከተቻለ የአብዛኛዎቹን የአካል ጉዳተኞች ቁስል ማከም ይቻላል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

ሌላኛዋ በሴቶችና ሕፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የግንዛቤና ማኅበረሰብ ንቅናቄ ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ አየሉ ደመቀ እንደገለጹት፣ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ አዋጅ ሆነ መመርያ ቢወጣም ተግባራዊ ግን አልተደረገም፡፡

በከተማዋ የሚሠሩ አብዛኛዎቹ ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ያማከሉ አይደሉም የሚሉት ወ/ሮ አየሉ፣ በተለይ ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ ለሌላቸው ወገኖች የጤና መድን ሽፋን እንዲያገኙ ቢሮው እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት በ2015 ዓ.ም. ለሁሉም ሽፋን ለመስጠት መረጃ የመሰብሰብ ሥራ መሠራቱን ገልጸው፣ የጤና መድን ሽፋን የማይሰጡ ተቋሞችን ግን የወጣውን ሕግ በመተላለፍ ይቀጣሉ ብለዋል፡፡

የአካል ጉዳተኞች አብዛኛውን ጊዜ መብቶቻቸውን በመጠየቅ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀው ሥልጠና ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ሉሌ እንደገለጹት፣ በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለሚገኙ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ሥልጠና በመስጠት አቅም የማጎልበት ሥራ ይሠራል፡፡

በዚህ መሠረት ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳተኞች በተለያየ ደረጃ በመንግሥት ተቋማት ሥር እያገለገሉ መሆኑን፣ ነገር ግን የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ሕንፃ አለመሠራቱ ትልቅ ችግር ሊሆን እንደቻለ አክለው ገልጸዋል፡፡

አካል ጉዳተኞች በአገር ግንባታ ላይ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፣ እነዚህ ሰዎች ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ፋይዳዎች ላይ አሻራቸውን በሚጥሉበት ወቅት የሥራ አካባቢያቸው ምቹ እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡

በተለይም ወረዳም ሆነ ክፍለ ከተሞች ላይ የሚገነቡ ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞች ያማከሉ አለመሆናቸውንና ይህንንም ችግር ለመፍታት ቢሮው በተያዘው በጀት ዓመት 120 ወረዳዎች ላይ በመሄድ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ሕንፃ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይም በ145 ወረዳዎች ላይ ተደራሽ ለመሆን የሚሠራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኃይሉ፣ ይህንን በሚሆንበት ወቅት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሠራ ይሆናል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርገው የሚሠሩ ተቋሞች እንዳሉ የነዚህም ተቋሞች ተሞክሮ በመውሰድ በሌሎችም አካባቢዎች ለመተግበር ቢሮው የሚተጋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...