Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበኢትዮጵያ ለኤድስና ካልአዛር ሕሙማን የሚሰጠው ጥምር ሕክምና ውጤት እያመጣ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ለኤድስና ካልአዛር ሕሙማን የሚሰጠው ጥምር ሕክምና ውጤት እያመጣ ነው ተባለ

ቀን:

በኤችአይቪ ኤድስና በካልአዛር ተጓዳኝ ሕመሞች ለሚሰቃዩ ሰዎች በዓለም ጤና ድርጅት መመርያ (ጋይድላይን) መሠረት መሰጠት የጀመረው ጥምር ሕክምና ውጤት ማምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

በተለይ በብራዚል፣ ምሥራቅ አፍሪካና ህንድ ከፍተኛ የጤና፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ የሚገኘው ካልአዛር ወይም ቁንጭር የሚባለውና አፍንጫና ፊትን የሚያቆስለው በሽታ፣ ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ከሌሎች በበለጠ የሚያጠቃ መሆኑ ሕክምናውን አዳጋች አድርጎት ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ ጥምር የሕክምና ዘዴ አስተዋውቆ የነበረ ሲሆን፣ ይህም ውጤታማ መሆኑን ለመፈተሽ በኢትዮጵያና በህንድ ጥናት ተሠርቷል፡፡

- Advertisement -

ድርጅቱ እ.ኤ.አ. በ2010 ተግባራዊ እንዲሆን ያስቀመጠው የሕክምና አሰጣጥ መመርያ በህንድ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ ሕክምናውም ከኤድስ ጋር እየኖሩ በካልአዛር የተጠቁ ሕሙማን በካልአዛር ዳግም የመጠቃት ዕድላቸው በ96 እንዲቀንስ አስችሏል፡፡ ይህም በመደበኛው ሕክምና ከተመዘገበው 88 በመቶ ውጤት ስሳምንት በመቶ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ1980 ወዲህ በኤችአይቪ ኤድስና በካልአዛር ጥምር በሽታዎች የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 በመቶ እስከ 30 በመቶ አድጓል፡፡ ይህ በዓለም በሁለቱ ጥምር በሽታዎች ከተመዘገበው ቁጥር ከፍተኛው ነው ያለው ድርጅቱ፣ አሁን ላይ ቁጥሩ እየቀነሰ ቢሆንም፣ የሁለቱ በሽታዎች ጥምር ኢንፌክሽን መከሰት አሁንም የጤናው ዘርፍ ፈተና እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያም የተጀመረው አዲሱ ጥምር ሕክምና 88 በመቶ ውጤታማ እንደሆነና ይህም አሁን ላይ በመደበኛ እየተሰጠ ከሚገኘው ሕክምና ከተመዘገበው የ55 በመቶ ውጤታማነት የተሻለ እንደሆነ አስፍሯል፡፡

ትኩረት በተነፈጉ ሐሩራማ በሽታዎች ላይ በሚሠራው ‹‹ድራግ ፎር ኒግሌክትድ ዲዚስ ኢንሽየቲቭ›› (ዲኤንዲአይ)፣ በዓለም አቀፍ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ)ና ተባባሪ አካላት በጋራ ጥምር የሕክምና ጋይድላይንኑ በኢትዮጵያና በህንድ ያስገኘውን ውጤት አስመልክቶ የሠሩትን ጥናት ተመርኩዞም የዓለም ጤና ድርጅት የ2010ሩን ጋይድላይን አሻሽሎ ይፋ አድርጓል፡፡

የተሻሻለው የኤድስና ካልአዛር ጥምር ሕሙማን አዲስ የሕክምና ጋይድላይንም በምሥራቅ አፍሪካና በደቡብ ምሥራቅ እስያ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡

        በዲኤንዲአይ ትኩረት የተነፈጉ የሐሩር በሽታዎች፣ የቁንጭርና ማይሶቶሚያ ክላስተር ዳይሬክተር ፋቢያና አልቬዝ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በኤችአይቪ እና በቁንጭር በሽታዎች በአንድ ላይ የተጠቁ ህሙማን ከተለመደው ሕክምና መኋላ የሚያሳዩት መሻሻል እምብዛም የነበረ ሲሆን፣  የድርጅቱ ጥምር የሕክምና መመሪያ ግን አመርቂ ውጤቶችን አስገኝቷል፡፡

        አዲሱ የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ በሁለቱም በሽታዎች፣ በአድሎና መገለል፣ በካልአዛል በሽታ ማገርሸትና በገቢ እጦት የሚሰቃዩትን ህሙማን ሕይወት የሚያሻሽል ነው፡፡

        ካልአዛር በአሸዋ ዝንብ ንክሻ የሚተላለፍ ሲሆን ትኩሳት፣ የክብደት መቀነስ እና ከፍተኛ ድካም ያስከትላል። በቁንጭር በሽታ የተጠቃ ሰው በተገቢው ጊዜ ህክምና ካልተደረገለትም የመሞት እድሉ ሰፊ ነው፡፡

        ብዙውን ጊዜ ከእነዚህ ሁለት በሽታዎች ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ማከም አስቸጋሪ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ በሽታ የመቋቋም አቅማቸው መዳከሙ ለመደበኛ ህክምና አወንታዊ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑ ነው፡፡

        በቁንጭር በሽታ የተያዙ ታካሚዎች አሁንም የተሻሻለ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ፈዋሽ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በቁንጭር በሽታ ምክንያት የሚከሰት የሞት መጠንን ከሶሥት በመቶ በታች ለማድረስ እየሰራች መሆኑ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...