Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪካዊት ቀንና ማምሻዋ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪካዊት ቀንና ማምሻዋ

ቀን:

ለአይቮሪኮስቱ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በምድብ አራት የተደለደሉትን ግብፅ፣ ጊኒ፣ ማላዊና ኢትዮጵያን የማጣሪያ ጨዋታ ተከትሎ፣ ቅድመ ትንታኔ ሲሰጡ የነበሩ የተለያዩ ሚዲያዎች የዋሊያዎቹ ስብስብ ከማላዊ አቻው ጋር ያደረገውን ጨዋታ ተመልክተው ብሔራዊ ቡድኑ በማጣሪያው እስከ የት ሊጓዝ እንደሚችል በመተንተን ተጠምደው ከርመው ነበር። ዋሊያዎቹ በካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ ምድብ በማለዳው መሰናበታቸውና በውድድሩ ዋጋ ያስከፈላቸውን ጉዳይ የተመለከቱ ተንታኞቹ፣ ብሔራዊ ቡድኑ ከማላዊ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ከስህተቱ መማር ተስኖት ከዕረፍት በፊት በተቆጠሩበት ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶች በመረታቱ ለተንታኙ ትችት እንዲሰነዝር መንገድ አስጠርጎት ነበር። በተለይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባዕድ አገር የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከግብፅ ጋር ማድረጉ፣ መቶ በመቶ አሸናፊነቱ ለፈርዖኖቹ እንዲሰጥ አስችሎታል።

የአፍሪካ ዋንጫን ለሰባት ጊዜ በማንሳት ክብረ ወሰን በእጁ የጨበጠውና በእግር ኳስ በአፍሪካ በቀዳሚነት ማማ ላይ የተቀመጠው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን፣ በመጀመሪያው ማጣሪያ ጨዋታ ጊኒን 1 ለ0 መርታቱን ተከትሎ፣ ከዋሊያዎቹ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ቀለል አድርጎ እንዲመለከተው ማድረጉ ሲገለጽ ነበር።

በዓባይ ጉዳይ በፖለቲካው ጥረት ውስጥ የከረሙት ኢትዮጵያና ግብፅ፣ በተለይ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የውኃ ሙሌት ለማከናወን በተዘጋጀችበት ዋዜማ፣ በአንድ ምድብ መደልደላቸው አግራሞትን የፈጠረ አጋጣሚ ነበር። ለዓመታት የዓባይን ግድብ ፖለቲካ ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ ዛቻ አዘል ዘገባዎችን ሳይታክቱ ሲያቀርቡ የከረሙት የአገሪቷ ሚዲያዎች ‹‹ግብፅ በኢትዮጵያ አስደንጋጭ ሽንፈትን ቀመሰች›› ሲሉ ዘገቡ።

ዋሊያዎቹ ፍፁም የበላይነት ባሳዩበት የምድቡ ሁለተኛ ማጣሪያ ጨዋታ በዳዋ ሆቴሳ የ21ኛ ደቂቃና በሽመልስ በቀለ 39ኛ ደቂቃ ግቦች ኢትዮጵያ ፈርâኖችን ድል ነሳች። ኢትዮጵያዊውያን በደስታ ጮቤ ያስረገጠ ድል ሆኖም ተሰማ።

አማካዩ ጋቶች ፓኖም፣ አጥቂዎች አቡበከር ናስር፣ ዳዋ ሆቴሳ እንዲሁም አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በግብፅ ስፖርት ጋዜጠኞች አፍ ተደጋግመው ሲጠሩ ዋሉ።ከእግር ኳስም በላይ የሆነው የዋሊያዎቹ አይበገሬነት በማላዊ ቢንጎ ስታዲየም ሰማይ ሥር ማላውያንን ሳይቀር ጮቤ ያስረገጠ ክስተት ሆነ። ማኅበራዊ ሚዲያው በደስታ መልዕክት ተጥለቀለቀ። የእግር ኳስ ግንዛቤ የሌላቸው ፖለቲከኞች ሳይቀሩ ‹‹እንኳን ደስ አለን›› የሚል መልዕክት በማስፈር ሥራ ተጠምደው ዋሉ።

በማላዊ ኢትዮጵያውያን ያረፉበት ሆቴል ሳይቀር የአገሪቷ እግር ኳስ ወዳጆች እንዲሁም የስፖርት አመራሮች ብሔራዊ ቡድኑን ሲያሞግሱ አመሹ።

የአፍሪካ ዋንጫ ጠንሳሽ ከሆኑት መካከል የሚጠቀሱት ሁለቱ አገሮች በእግር ኳሱ ዕድገት የተመጣጠኑ ባይሆኑም፣ ኢትዮጵያ ከእግር ኳስ በላይ የሆነውን ጨዋታ በባዕድ አገር ላይ መርታት ችላለች። በውጤቱ ሲወቀስ የሰነበተው የዋሊያዎቹ ስብስብ ጨዋታውን በአገሩ አፈር ላይ ባለማድረጉ በርካቶችን ያስቆጨ አጋጣሚ ነበር።

ኢትዮጵያ አንድም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ደረጃን የሚያሟላ ስታዲየም በማጣቷ ምክንያት ለማላዊ ስታዲየም 30 ሺሕ ዶላር ከፍላ ለመጫወት ተገዳለች።

ብሔራዊ ቡድኑ ያመጣው ውጤት ጮቤ ቢያስረግጥም፣ ሜዳ አልባ መሆኑ በርካቶችን አንገት ያስደፋ ነው። መንግሥትም ውጤት ሲመጣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥቶ እንኳን ደስ አላችሁ ከማለት፣ ስፖርተኛው ወደ አገር ሲመለስ በአየር ማረፊያ በአበባ ጉንጉን ከመቀበል በዘለለ ብሔራዊ ቡድኑን በባዕድ አገር እንዳይጫወት የሚያደርገውን መፍትሔ ሲሰጥ አለማስተዋል መመልከት የተለመደ ሆኗል።

ምንም እንኳ በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች ረብጣ ገንዘብ ፈሶባቸው የተገነቡ ስታዲየሞች ቢኖሩም፣ ለፖለቲካ ዲስኩርና ለበዓላት ማድመቂያ ከመሆናቸው በዘለለ ፋይዳ ሊኖራቸው አልቻለም።

ግብፅና ኢትዮጵያ 17 ጊዜ ተገናኝተው ግብፅ 13 ጊዜ ስታሸንፍ፣ ኢትዮጵያ ግን ያሸነፈችው ሁለት ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡ ግብፅ 56 ጎሎችን ስታስቆጥር፣ ኢትዮጵያ 14 ጎሎችን ማስቆጠር ችላለች (የዘንድሮን ማጣሪያ ጨዋታ ሳያካትት)። ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ድል የተቀዳጀችው የመጀመርያው በ1954 ዓ.ም. የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ 4-2 እና በ1982 ዓ.ም. የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 1-0 በሆነ ውጤት ነው።

ዋሊያዎቹ በማላዊ ያደረጉት ጨዋታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መስከረም ላይ በካይሮ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጉት ሦስተኛው የምድብ ጨዋታ ይጠበቃል።የሁለተኛውን የምድብ ጨዋታ ውጤት ተከትሎ ዋሊያዎቹ ምድቡን በሦስት ነጥብ እየመሩት ቢገኝም፣ ከግብፅ አቻቸው ጋር ያሳዩትን ድንቅ ብቃት በቀሪዎቹ የምድብ ጨዋታዎች ለመድገም ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው እሙን ነው።

ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በምድብ አራት የተመደቡት ጊኒና ማላዊ ወቅታዊ አቋምና በካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ከመሳተፋቸው በዘለለ፣ በውድድሩ ፈታኝ የነበሩ ብሔራዊ ቡድኖች መሆናቸው ነው። ለዚህም የታየውን የተስፋ ጭላንጭል ለማስቀጠል ቡድኑ ላይ የሚስተዋሉትን ስህተቶች በማረምና ወደ አይቮሪኮስት የአፍሪካ ዋንጫ ሊያሻግራቸው የሚችለውን ወጥ አቋም መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ባለሙያዎች ያስቀምጣሉ።

ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን የስታዲየም ግንባታዎች አፋጥና ለቀሪዎቹ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በአገር ውስጥ እንዲደረጉ መጣር እንደሚያስፈልግ የብዙኃኑ ምኞት ነው።

ብሔራዊ ቡድኑ በማላዊ ያመጣውን ድል ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁለት ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ገንዘብ እንደሚሰጥ ተገልጿል። ሆኖም በአንድ ጨዋታ የውጤት ጭላንጭል በታየ ቁጥር የማበረታቻ ገንዘብ ከመስጠት ይልቅ ዘለቄታዊ ፋይዳ የሚሰጠውን የስታዲየም ግንባታ ማፋጠን እንደሚገባ የሚመክሩ በርካቶች ናቸው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...