Tuesday, February 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከደረጃ በታች የሆኑ ጋራዦችን ደረጃ እንዲያሟሉ የሚያስችላቸው ድጋፍ ሊደረግ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ከደረጃ በታች የሆኑ የጋራዥ ማዕከላት ወደ ደረጃ እንዲመጡ የሥልጠናና የድጋፍ ሥራዎች ሊያደርግ መሆኑን፣ በኢትዮጵያ የአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ሕጋዊ አስመጪና ገጣጣሚ የሆነው ካኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አስታወቀ፡፡

ማኅበር ይህን የገለጸው አዲስ ሞዴል የሆነውን አይሱዙ ኤፌሳር 700ፒ (ISUZU FSR 700P) ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ትራንስፖርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባስመረቀበት መድረክ ላይ ነው፡፡ 

የካኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ገብረ ሚካኤል ግርማይ እንዳስታወቁት፣ ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ2017 ሕጋዊ የአስመጪነት ውክልና ካገኘበት ጊዜ አንስቶ በአይሱዙ የሚመረቱ አዳዲስ ምርቶች ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ለተገልጋዮች ይፋ መደረግ አለበት የሚለውን የአምራች ኩባንያ ፖሊስ በመከተል ሁነቱ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው እኤአ ከ2019 ጀምሮ አይሱዙ ኤንፒአር(NPR) የሚባለውንና 35 ኩንታል የሚጭነውን ተሽከርካሪ በአገር ውስጥ መገጣጠም እንደጀመረ የተገለጸ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ በአዲስ ሞዴል ይፋ የተደረገውን የኤፌሳር ተሽከርካሪ መገጣጠም ይጀምራል ተብሏል፡፡

ደርጅቱ አብሯቸው የሚሠራ ከደረጃ በታች የሆኑ በርካታ ጋራዦች እንዳሉ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ፣ እነዚህ ጋራዦች አስፈላጊውን ደረጃ አምጥተው ብቁ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የስልጠናና ድጋፍ ሥራዎችን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለማድረቅ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቶቹ ደረጃውን ማሟላታቸው የሚሰጡትን ጥገና በአይሱዙ ኩባንያ ስታንዳርድ እንዲሰጡ የሚያስችላቸው ሲሆን፣ ተፈላጊው የመለዋወጫ ግብዓት ተሞልቶላቸው ጥገና ማከናወናቸው ለጥገና በሚል የሚወጡ ከፍተኛ ወጪዎችን በቀላሉ መዳኝ የሚቻል መሆን አቶ ገብረ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ቁጥሩ ከ50 ሺሕ በላይ የሆነ የአይሱዙ ተሽከርካሪ እንዳለ ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ፣ መኪኖቹ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ ልክ እንዲያገለግሉ ጥገናዎች በአቅራቢያ አካባቢዎች መሟላት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች