Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልብቅ ብቅ እያለ የመጣው የሙዚቃ ድግስ

ብቅ ብቅ እያለ የመጣው የሙዚቃ ድግስ

ቀን:

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት መንግሥት በትምህርት ቤቶች፣ ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎችና በሌሎች ነገሮች ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል፡፡ ይኼም በኢኮኖሚውና ማኅበራዊ ግንኙነት ላይ ጫና ማሳደሩ ይታወሳል፡፡ በተለይ የመዝናኛ ዘርፉን በስፋት ሊጎዳው ችሏል፡፡ በዚህም የተነሳ አብዛኛውን የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለይም ደግሞ ወጣቶች እንደፈለጉ ወጥተው እንዳይዝናኑና በሥራ የተወጠረ አዕምሮአቸውን እንደልባቸው እንዳይፈቱት እንዳደረጋቸው ይታመናል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ አርቲስቶች የሙዚቃ ድግሶችን (ኮንሰርት) አለማቅረባቸው ከያንያኑንም ሆነ የሙዚቃ ኢንዱስትሪውን መጉዳቱ አልቀረም፡፡

በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተስፋፋበት ወቅትና አገሪቱ ባጋጠማት ጦርነት ሰሞን አልበማቸውን የሠሩ ድምፃውያን እነ ዳዊት ጽጌ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ቢያጠናቅቁም በነበሩት ገደቦችና ሁኔታዎች ምክንያት ሳያቀርቡ ቀርተዋል፡፡

ይኼም አንድም የኢንዱስትሪ ዘርፉን ሊጎዳ በሌላ መንገድ ደግሞ የሁነት አዘጋጆች ፕሮሞተሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ገበያቸው ሊቀዘቅዝ ከመቻሉም ባለፈ ላልተፈለገ ኪሳራ ሊወድቁ እንደቻሉ መረጃው ያሳያል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በጆርካ ኢቨንትና በሌሎች አዘጋጅነት በመቻሬ፣ በመስቀል አደባባይና በግዮን ሆቴል የተለያዩ ድምፃውያን የሙዚቃ ድግሳቸውን (ኮንሰርት) ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

የዚያ ተቀፅላ የሆነው ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ፀሐይ ዮሐንስ፣ አብዱ ኪያር፣ ሳሚ ዳንና ቬሮኒካ አዳነ ያቀረቡት የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) የሙዚቃውን ማኅበረሰብ አስደስቷል፡፡

የሙዚቃው ድግስ በቀረበበት ወቅት አብዛኛዎቹን ታዳሚ ወጣቶች የሙዚቃ ጥማታቸውን አብሮ በማዜምና በመደነስ ከሁሉም በላይ ደግሞ አገራዊ መልዕክት ያላቸው ዜማዎች በተዋናዮች አንደበት ሲቀርብ ማየት ምን ያህል እንደሚያስደስት ኮንሰርት የሚያዘወትረው ዘወትር ለሪፖርተር አስረድቷል፡፡

‹‹የሙዚቃ ድግስ ወይም ኮንሰርት አዕምሮን ከማዝናናት ባለፈ የራስህን የሕይወት መንገድ የምታይበት ነው፤›› የሚለው ወጣቱ፣ በተለይ ደግሞ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታና ጦርነቱ ከባድ በመሆኑ አገራዊ ኮንሰርቶች ያስፈልጋሉ ሲል ያምናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...