Wednesday, February 21, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ሚኒስትሩ ቢሮ መግባታቸውን የተመለከተው አማካሪያቸው የአንድ ባለሀብትን ጥያቄ ለማቅረብ ወደ ውስጥ ዘለቀ]

 • ክቡር ሚኒስትር አካም?
 • ምን አልክ?
 • አካም፡፡
 • ተው… ?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የማትቀጥለውን አትጀምር ማለቴ ነው፡፡
 • ያው እንዴት አደሩ ለማለት ነው።
 • እሱን ብቻ ሳይሆን ሌላም አውቃለሁ።
 • ምን ክቡር ሚኒስትር?
 • አካም የምትለው መቼና ለምን እንደሆነ?
 • ጠዋት ስንገናኝ ነው እንደዛ የምለው።
 • ለማንኛውም ምን ይዘህ ነው የመጣኸው?
 • ባለፈው የመጡት ባለሀብት የጠየቁት የቀረጥ ነፃ ዕድል ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለመጠየቅ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እኮ …ቀድሜ አውቄዋለሁ።
 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የሆነ ነገር ስትይዝ ምን ብለህ እንደምትጀምር፡፡
 • ምን ብዬ ነው የምጀምረው?
 • አካም፡፡
 • እ…
 • ባይ ዘ ዌ የሰላምታህን ቋንቋ በመለዋወጥ የሚቀየር ነገር የለም።
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ነገርኩህ አካም አልክም ጉድ ሞርኒንግ ለባለሀብቱ ጥያቄ የሰጠነው መልስ አይቀየርም።
 • ከመቼ ጀምሮ ነው ይህንን አቋም የያዙት ክቡር ሚኒስትር?
 • እሱ ትናንትናም ሊሆን ይችላል ዛሬም ሊሆን ይችላል። ከዚህ በኋላ ግን አቋማችን ነው።
 • ጥሩ ደህና ይዋሉ ክቡር ሚኒስትር !

[ክቡር ሚኒስትሩ ያለቃቸውን የፓርላማ ንግግር በአካል ተገኝተው ከተከታተሉ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ የእጅ ስልካቸውን በሌባ የተነጠቁት ባለቤታቸው እያማረሩ አገኟቸው] 

 • ዝም ብላችሁ ሕዝቡን አዘርፉት እንጂ መንግሥትማ የለም።
 • ምን ሆንሽ? ምን ገጠመሽ?
 • ዋናው የዚህ አገር ችግር ሌብነት ነው።
 • ያልሽው ትክክል ነው። እኛም ዋናው ችግር ይህ እንደሆነ ለይተናል።
 • ምንድነው የለያችሁት?
 • ችግሩ ሌብነት መሆኑን ብቻ ሳይሆን… ሌቦቹ እነ ማን እንደሆኑ ለይተናል፡፡
 • እነ ማን ናቸው?
 • ዋነኞቹ ብለን የለየናቸው ሌቦች የፍርድ ቤቶች ናቸው።
 • ዋነኞቹ?
 • አዎ። አልሰማሽም እንዴ?
 • ምኑን?
 • ዛሬ ፓርላማ ላይ ዝርዝራቸው በይፋ ተነግሯል።
 • እሺ ሁለኛው ዋና ሌባ ማነው?
 • ሁለተኛው ዋና ሌባ ዓቃቤ ሕግ ነው።
 • ምን?
 • ይሄ ብቻ መስሎሽ ነው? ሦስተኛም አራተኛም… ተዘርዝረዋል።
 • እሺ… ሦስተኛው ማነው?
 • ፖሊስ ነው፡፡
 • ወይ ጉድ አራተኛውስ?
 • አራተኞቹ ሌቦች ኦዲተሮች ናቸው።
 • ኦዲተሮች ደግሞ በየት በኩል ወደ ሌብነት ገቡ?
 • በሌብነት የተበላ ገንዘብ በኦዲት እንዲያጋልጡ ሲባሉ ነው መንገዱን ያገኙት።
 • እንዴት አድርገው ነው የሚሰርቁት?
 • የተበላ ገንዘብ መኖሩን በኦዲት ካረጋግጡ በኋላ ከማጋልጥህ ስንት ታመጣለህ ብለው ይቀበላሉ።
 • በሙሉ እዚህ ምድብ ናቸው በለኛ?
 • እነ ማን?
 • ከሌባ ይጠብቁናል ያልናቸው፡፡
 • ሌሎች አሉ…
 • እነ ማን ናቸው ደግሞ?
 • የእምነት ተቋማት ናቸው።
 • የጉድ አገር አሉ… እነሱም?
 • አዎ። መንግሥት በእምነት ውስጥ አይግባ ብንል ሰፊ ሌብነት ተንሰራፍቶ ተገኝቶባቸዋል። ቢሆንም መፍትሔ እናበጅላቸዋለን።
 • ምን ልታደርጉ አሰባችሁ?
 • አማኙ የሰጠው ገንዘብም ሆነ ስጦታ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ሕግ አውጥተን ኦዲት እናደርጋለን።
 • ኦዲት ልታደርጉ?
 • አዎ። የግድ መጀመር አለበት።
 • ሆሆ…?
 • ምነው?
 • ሙዳየ ምጽዋት ኦዲት ስታደርጉ ታይቶኝ ነዋ?
 • እሱ በሚወጣው ሕግ በዝርዝር ይወሰናል።
 • እስካሁን ከዘረዘርካቸው ውስጥ ግን በተለምዶ የምናውቃቸው ሌቦች የሉም።
 • በተለምዶ የሚታወቁት ሌቦች እነ ማን ናቸው?
 • የመንግሥት ሌቦች ናቸዋ?
 • እነሱም አሉበት?
 • አገሩ ሁሉ ሌባ ሆኗል በለኛ?
 • ምን እናድርግ ብለሽ ነው?
 • እንዴት?
 • ለህልውና ዘመቻ ወጥተን ስንመለስ ይኸ ጠበቀን።
 • እና መፍትሔው ምንድነው። ምን ልታደርጉ አሰባችሁ?
 • አቅጣጫ ተቀምጧል።
 • የምን አቅጣጫ?
 • ፓርላማ ላይ ሲነገር አልሰማሽም?
 • ምን ተነገረ?
 • የዘረዘርኩልሽን እነዚህን ሌቦች ከመንግሥት ሌቦች ጋር ቀላቅለን በመሄድ የምንፈልገውን ግብ ለማሳካት አቅጣጫ ተቀምጧል።
 • ኪኪኪኪ ….ሆሆሆ፡፡
 • ለምን እንደሳቃሽ አልገባኝም?
 • እሳቸው ቃል ሲገድፉ እናንተም እንደምትገድፉ አላውቅም ነበር?
 • ምን ማለትሽ ነው አልገባኝም?
 • እሳቸው ቃል ገድፈው እንጂ ለማለት የፈለጉት ቀላቅለን እንጠርጋቸዋለን ነው።
 • ቃሉ ገደፈው ነው ብለሽ ነው?
 • የቃል አጠቃቀም ስህተት መሆኑ ግልጽ እኮ ነው?
 • ቢሆንም…
 • እንዴት? እናንተ አርማችሁ ማስረዳት አትችሉም?
 • የተገደፈው ከላይ ነዋ፡፡
 • ቢሆንስ?
 • እርማቱም ከላይ መምጣት አለበት !

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...

[ክቡር ሚኒስትሩ አገር ለመጎብኘት ከመጡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር እየተወያዩ ነው]

ባደረጋችሁት ጉብኝት አገራችሁ ያለችበትን ትክክለኛ ገጽታ ለመመልከት እንደቻላችሁ እርግጠኛ ነኝ። ልክ ነዎት ክቡር ሚኒስትር። ታዲያ ጉብኝቱን እንዴት አገኛችሁት? አንዳንድ ጉዳዮች በጥንቃቄ ከተያዙ አገራችን ተስፋ እንዳላት ተገንዝበናል። እስኪ በጥንቃቄ...