Sunday, October 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ ጣሪያ ዝቅ እንዲል ወሰነ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች ከዚህ ቀደም ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱበትን የመጠባበቂያ ገንዘብ መጠን ጣሪያ ከአሥር በመቶ ወደ ሰባት በመቶ ዝቅ እንዲል ወሰነ፡፡

ከነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱትን የመጠባበቂያ ገንዘብ መጠን፣ ቀድሞ ከነበረበት አምስት በመቶ ወደ አሥር በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ያወጣው መመርያ፣ የባንኮች የመጠባበቂያ ተቀማጭ ምጣኔ ከዚህ ቀደም ከነበረበት አሥር በመቶ ወደ ሰባት በመቶ ዝቅ እንዲል የሚያዝ ነው፡፡

በአዲሱ መመርያ መሠረት ባንኮች ከሚሰበስቡት ቁጠባ ሰባት በመቶ ያህሉን በየወሩ መጨረሻ በብሔራዊ ባንክ እንዲያስቀምጡ ይገደዳሉ፡፡

በዚህ ወቅት በተሻሻለው መመርያ የተቀማጭ ገንዘብ ጣሪያው እንዲወርድ መደረጉ፣ ምናልባትም ባንኮች እያጋጠማቸው ያለውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት በተወሰነ ደረጃ እንዲቀረፍ ሊያግዛቸው ይችላል የሚል ዕምነት እንዳላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ባንኮች በተወሰነ ደረጃ ለደንበኞች ብድር ለማቅረብ ዕድል እንደሚሰጣቸው፣ ውሳኔውም በመልካምነቱ የሚወሳ መሆኑን ባለሙያዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከአሥር ወራት በፊት የወሰደው የገንዘብ ፖሊሲ ዕርምጃ እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመግታት አዎንታዊ ሚና የሚጫወት፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅዕኖ የማያስከትል መሆኑን ቢገልጽም፣ በአንፃሩ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባንክ ኃላፊዎች የመጠባበቂያ ገንዘቡ በእጥፍ መጨመሩ በባንኮች ላይ ጫና ይፈጥራል ብለው ያምናሉ፡፡

የመጠባበቂያ ገንዘብ ብሔራዊ ባንክ ያለ ምንም ወለድ የሚቀመጥ በመሆኑ ለባንኮቹ ፈታኝ እንደሆነ፣ ወለድ የሚከፍሉበት ገንዘብ ያለ ወለድ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲሆን መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን የባንክ ኃላፊዎች በወቅቱ ገልጸው ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች