Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሊዲያ ታፈሰ የአፍሪካ ዋንጫን ትመራለች

ሊዲያ ታፈሰ የአፍሪካ ዋንጫን ትመራለች

ቀን:

በርካታ አኅጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን መምራት የቻለችው ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የዘንድሮውን የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን ትመራለች።

ከሰኔ 25 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የ አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ጨዋታ ከሚመሩት ዳኞች ውስጥ የኢትዮጵያዊቷ ዳኛ ሊዲያ ስም ይፋ ሆኗል፡፡

ለሦስት ሳምንታት በሞሮኮ የሚከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በ12 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል እንደሚደረግ ይታወቃል። ዓርብ ሰኔ 10 ቀን የዳኞችን ስም ይፋ ያደረገው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬስን (ካፍ) በራባትና ካዛብላንካ የሚከናወኑትን ጨዋታዎችን የሚመሩ ዋና ዳኛና ረዳት ዳኞችን ስም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በውድድሩ 16 ዋና፣ 16 ረዳት እንዲሁም ስምንት የምሥል ዕገዛ የሚሰጡ ዳኞች ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች መመረጣቸው ታውቋል። በዋና ዳኝነት ዝርዝር ከተቀመጡት ስሞች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ዋና  ዳኛ ሊዲያ ስም ተጠቅሷል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ከአንደኛ እስከ አራተኛ የሚወጡ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጣዩ ዓመት በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ አዘጋጅነት በሚከናወነው የዓለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

ሊዲያ ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ከመመረጧ አስቀድሞ በፈረንሣይ እግር ኳስ ማኅበር አዘጋጅነት የተከናወነውን የማውሪስ ሪቪሎ ውድድር ለመምራት ለቀናት ፈረንሣይ እንደነበረች ታውቋል፡፡

ሊዲያ በደቡብ ፈረንሣይ በአሥራ ሁለት አገሮች መካከል ሲደረግ በነበረው ውድድር ጃፓን ከአልጄሪያ እንዲሁም ከአርጀንቲና ጋር ያደረገችውን ጨዋታ የመራች ሲሆን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...